• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ”

  • እንኳን ወደ ድረገጻችን በደህና መጡ!

  • ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡት መ/ር አባ ሞገስ ኃይለ ማርያም በሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሐላፊዎችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ ዛሬ የካቲት 2011ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሥራ ሐላፊዎች ተመደቡለት

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክያን መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤ/ክህነት መዋቅራዊ አስተዳደር ሥር ከሚገኙት አህጉረ ስብከቶች መካከል አንዱና አንጋፋው እንዲሁም የቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካሉበት ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተነሣ ብጥብጥና ትርምስ የማያጣው ተቋም እየሆነ ከመምጣቱም በላይ በርካታ የሥራ ሐላፊዎችን ያፈራረቀ ነው፡፡ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና ብቻ […]

በዓለ አስተርእዮ

አስተርእዮ፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ አስተርእዮ ማለትም መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው፡፡
በግሪክ ቋንቋ ኤጲፋንያ ይባላል ኤጲፋንያ ማለት መገለጥ፤ መታየት ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል የመገለጥ፣ የመታየት ዘመን ማለት ነው፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆኖ የተገለጠበት ዘመን ስለሆነ እና እንዲሁም በጥምቀቱ አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠበት ዘመን …

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለ ልደትን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የ2011 ዓ/ ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትን አስመልክቶ በርካታ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትና የሚድያ አካላት በተገኙበት በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። ጋዜጣዊ መግለጫውም “ሰላምን ሻት ተከተላትም” በሚል የመነሻ ሐሳብ የሰላም ዋጋ ምን ያክል ውድ እንደ ሆነና ሰላም ካልተጠበቀ በቀር ሊወሰድ የሚችል መለኮታዊ ስጦታ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዝህም ጋር ተያይዞ ወቅታዊውን የሀገራችን የሰላም ችግርና የህዝብ እንግልት […]

ሰበር ዜና ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊነት ተመለሱ

ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በተላለፈ መመሪያ ወደሓላፊነታቸው የተመለሱት ሊቀ ጠበብቱ ቀደም ሲል የመደባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ስልጣን መከበር እንዳለበት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የተላለፈው የእግድ ማንሻ ደብዳቤ ይገልጻል::ዝርዝር ዜናውን…..

ለእድገትእንነሣ

አዲስ አበባ ሃ/ስብከት ከአሁን በፊት ያስመዘገባቸው በርካታ ዕድገት ቢኖሩትም አሁን ደግሞ ለእድገት መሰናክል የሆኑበትን አሰራሮችና ክፍተቶች ጊዜ ወስዶ በመመርመርና በማጤን የእድገት ግብዓት የሚሆኑ አዳዲስ አስራሮችንና አመለካከቶችን በሥራ ላይ ለማዋል በሂደት ላይ ይገኛል

ማስታወቂያ

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል

©2019 Copyright - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት