• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ”

  • እንኳን ወደ ድረገጻችን በደህና መጡ!

  • ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሐላፊ ሆነው ተመደቡ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ሒሳብ ሹም ሆነው ሲሠሩ የቆዩት መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ በቁጥር 1984/0829//2011 በቀን 17/04/2011 ዓ.ም ከሀገረ ስብከቱ በተጻፈ ደብዳቤ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት በሆነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሃላፊነት ተመድበዋል፡፡

መጋቤ ሃይማኖት ግርማይ ሐዲስ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መስኮች በመንበረ ፖ/ቅ/ቅ/ማርያም፤በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ፤በቦሌ ደ/ሳ/መድኃኔዓለምካቴድራልና በላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት በኃላፊነት እየተመደቡ ሲሠሩ የቆዩ ሲሆን በሠሩባቸው የሥራ ቦታዎች ሁሉ መልካም ስም እንዳላቸው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

የትምህርት ዝግጅታቸውን በተመለከተ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሁን…..

ሥርዓተ ጸሎት

ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/

በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
በፍጹም እምነት መጸለይ ይገባል፡፡
በፍጹም እምነት የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል እየተጠራጠርን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ ጥርጥር ትልቅ የሰው ባለጋራ /ጠላት/ ነው፡፡ ጥርጥርን ማስወገድ ያስፈልጋል “አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” /ማቴ. 21፡22/

በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ መጸለይ ይገባል
በቅን ልቡና፣ በንጹሕ ልብ የምንጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይቀበለዋል፡፡ ልባችንን የቂም በቀልና የክፋት ምሽግ አድርገን የምንጸልየውን ጸሎት ግን እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ “ጸሎቱ ለመስተቀይም ከመዘርዕ ዘወድቀ ማእከለ አሥዋክ” /የቂመኛ ሰው ጸሎት …..

ጾም በክርስትና ሕይወት

በዚህ ትምህርታዊ ጹሑፍ ስለ ጾም አራት ነጥቦችን እናያለን
1.የጾም ትርጉም
2. ጾም ያስፈለገበት ምክንያት
3. የጾም ጥቅሞች
4. በምን ዓይነት መንገድ መጾም እንዳለብን፡፡
ከላይ ከ1-4 ተራ ቍጥር የተገለጹትን እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን…

የብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ሐዋርያዊ ጉዞና የሱማሌ ጅግጅጋ አብያተ ክርስቲያናት ፈተናዎች

  የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከጅግጅጋ ከተማ 170 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በደጋ ሀቡር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ብፁዕነታቸው የእሳት ቃጠሎ የደረሰበትን የደጋ ሀቡር ቅዱስ ጊዮርጊስን ፅላት በተዘጋጀው መቃረቢያ ባርከው ያስገቡ ስለሆነ በማግሥቱ ህዳር 8 ቀን 2011 ዓ.ም የቅዳሴ ቤቱ በዓል በላቀ ድምቀት ተከብሯል፡፡
በዚሁ ደብር የቅዱስ ሚካኤል ፅላት በተደራቢነት ገብቶ ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም በዓሉ ተከብሯል፡፡
በጅግጅጋ መልእልተ አድባራት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ በርካታ ምዕማንንና ካህናት በተገኙበት ለብፁዕነታቸው እጅግ የደመቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
በማግሥቱ ሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከጅግጅጋ ከተማ በ70 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የውጫሌ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ጎብኝተዋል፡፡
ማክሰኞ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ ዙሪያ የሚገኙትንና በፀረ ሰላም ኃይሎች የእሳት ቃጠሎ የደረሰባቸውን የአቡነ ተክለሃይማኖትን፣ የቅድስት አርሴማን፣ የቅዱስ ጊዮርጊስንና የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን አብያተ ክርስቲያናት ብፁዕነታቸው እየተዘዋወሩ …

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ ሰባቱ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት አቀረቡ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ይቅርባይ እንዳለ፤ ምክትል ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወ/ሐና እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት በክፍለ ከተማ ሠራተኞች በአዲስ ቅጥር፣ ሽግሽግ፣ ዙሪያ የተደረገው ጥናት ሪፖርት ቀርቧል፡፡ የ7ቱ ክፍለ ከተማ ሠራተኞች በእነርሱ ሥር ያሉትን ገዳማትና አድባራት ላይ ባደረጉት ፍተሻ የተወሰኑት አዲስ ቅጥርን ፣ ሽግሽግን እንደፈፀሙ ገልፀዋል፡፡ እነዚህም አብዛኛው በኢ-ሕጋዊ መልክ እንደተፈፀመ ነው የተረጋገጠው፡፡ በተለይ ደግሞ በአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት በሚደረግ ቅጥር በጣም ውስብስብና ሥርዓት አልባ እየሆነ የሚሄደበት ሂደት ስላለ በደንብ ታይቶ  ጠንከር ያለ አሠራር እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል፡፡ በአንዳንድ አብያተ  ክርስቲያናት ያሉት ሠራተኞች ብንናገራቸውም የሚሰጡን መልስ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በአንዳንድ አጥቢያ ላይ በተመሣሣይ ሥራ ላይ ሁለትና ከሁለት በላ የሆኑ ሰዎች መቀመጣቸው ሌላ ችግር መሆኑም…

©2019 Copyright - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት