• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ”

  • እንኳን ወደ ድረገጻችን በደህና መጡ!

  • ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2011 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወአሐዱ ዓመተ ምሕረት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ […]

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በአ/ሀ/ስ/የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሀገረ ስብከቱ የሥራ እንቅስቃሴን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ አመራር አደረጃጀትን እና ቀደም ሲል ከሥራና ከደመወዝ የተፈናቀሉ ሠራተኞችን ጉዳይ አስመልክተው ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም  ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ አርዮንታል አብያተ ክርስቲያናት አንዷና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋ […]

የአዲስ አበባሀገረ ስብከት በሱማሌ ክልል በተፈጸመው የጭካኔ ግድያና የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ አስመልክቶ ከገዳማትና አድባራት የሥራ ሓላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ

በሀገራችን በምሥራቃዊ በሱማሌ ክልል በጅግጅጋ እና በሌሎች የአካባቢው ወረዳዎች በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እና አብያተ ክርስቲያናት ላይ ያነጣጠረ አሕዛባዊ ጥቃት ምክንያት ወገኖቻቸውን በሞት ላጡ እና ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ አካላቸውን ለተጎዱት ምዕመናን ወቅታዊ ዕርዳታ ለመለገሥና በጥቃቱ በእሳት የተቃጠሉትን አብያተ ክርስቲያናት መልሶ ለመገንባት አስፈላጊው እርዳታ እንዲደረግ በማሰብ ሀገረ ስብከቱ ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትን የሥራ ሓላፊዎች ጋር ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ለግማሽ ቀን የቆየ የውይይት ሥራ አከናውኗል፡፡

ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንደገለፁት ወገኖቻቸውን በሞት ላጡ እና ጭካኔ በተሞላበት ጭፍጨፋ አካላቸውን ለተጎዱት ምዕመናን ከሀገረ ስብከቱ ካዝና ብር 4 ሚሊዮን ወጭ አድርጎ የሰጠ ሲሆን በተጨማሪም እርዳታውን ከፍ ላመድረግ በማሰብ በሁሉም ገዳማትና አድባራት እንደየገቢያቸው መጠን ከካዝናቸው ወጭ አድርገው እንዲሰጡ በሀገረ ስብከቱ በኩል ስኩላር ድብዳቤ እንተጸፈ ብፁዕነታቸው አክለው ገልጸዋል፡፡የገዳማቱና የአድባራቱ የሥራ ሐላፊዎችም ከሀገረ ስብከቱ የተላለፈውን መመሪያ ተግባራዊ እንደሚደርጉ ስምምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የመንበረ ፓትርያርክ  ጠቅላይ ቤተ ክህነት ካቋቋማቸው የዕርዳታ  አሰባሳቢ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆኑትና የሲኤሚሲ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ዘካርያስ ሐዲስ ሰሞኑን ጅግጅጋ እና በአካባቢው በሚገኙ ወረዳዎች ሂደው በአብያተ ክርስቲያናቱ መቃጠል፣ በምዕመናን የግፍ ግድያና ከባድ የአካል ጉዳት ዙሪያ በዐይናቸው የተመለከቱትን ለጉባኤው

በወቅታዊ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ስለ ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትኖሩ፣ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሆይ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅድመ ታሪክ ዘመን አንሥቶ ህልውናዋ፣ ታሪክዋ፣ ገናናነትዋ፣ ታላቅነትዋና ሥልጣኔዋ በዓለም ዘንድ የታወቀ ታላቅና አኩሪ ሀገር ናት፡፡ ለታላቅነትዋ ዓቢይ አስተዋፅኦ ካበረከቱት መካከል፥ በፈሪሀ እግዚአብሔር እና በአምልኮተ እግዚአብሔር የተገነባ፣ ስለ ሃይማኖቱና ስለ አንድነቱ ፍንክች ሳይል በአንድነትና በጽናት የቆመ ሕዝብ ያላት መኾኑ ነው፡፡

በዚህ የሃይማኖት ሥርዐት፣ የዜጎች የማይበጠስ አንድነትና ማኅበራዊ መስተጋብር ጸጋ፣ ሀገሪቱ ከውጭ ወራሪዎች የሚደርስባትን ማንኛውንም ጥቃት በሚገባ እየመከተች እስከ አኹን በኀያልነት ዘልቃለች፡፡

በዚህም የዓለም ኹሉ ጸሐፍትና ምሁራን፥ ብቸኛ የኾነ አንጸባራቂ ታሪኳን፣ ማንነትዋንና ነጻነትዋን በደማቅ ቀለም ጽፈውላታል፡፡በቀላሉ ተዝቆና ተተንትኖ የማያልቅ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ታሪኳ በዓለምና በአፍሪቃ ጎልቶ ሊወጣ የቻለው ሕዝቦቿ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በቀለም፣ በመልክዐ ምድር፣ በባህልና በጥቃቅን ምክንያቶች ለሚፈጠሩ ልዩነቶች ቦታ ሳይሰጡ ዘላቂና የጋራ ጥቅማቸውን ለሚያረጋግጥ ሀገራዊ አንድነት ከማንም በፊት ቅድሚያ ሰጥተው እንደ ችቦና እንደ ነዶ አንድ ላይ በመቆማቸው እንደኾነ ታሪካችን አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡

በተለይም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ፥ ለምሥራቅ አፍሪቃ አልፎም ለመላው አፍሪቃና ለመላው የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት የሚኾን አንጸባራቂ የልማት፣ የአንድነትና የመልካም አስተዳደር ስኬት ታረጋግጣለች ብሎ የዓለም ሕዝብ ተስፋ በጣለበት ወቅት፣ ዜጎች ለታሪካቸው፣ ለባህላቸውና ለሃይማኖታቸው የማይመጥን ሰብእና እንደዚሁም በዓለም ሕዝብ ፊት ኃፍረትና ጸጸት የሚያስከትል ተግባር እንዳይፈጽሙ በእጅጉ

ጾመ ፍልሰታ

ጾም ምንድነው?

ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ለአንድ የተወሰነ ጊዜ መተው ወይም መከልከልና መቆጠብ  ማለት ሲሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ከእግዚአብሔር ጋር ከሚገናኙባቸው የግንኑነት መስመሮች መካከል አንዱ ነው፡፡የሰው ልጅ ግንኙነቱ የሠመረና በበረከት የተሞላ ደግሞም ለንስሐ የሚያበቃ ሕይወት ይኖረው ዘንድ በማቴ 6÷1-19 የተቀመጡለትን የግንኙነት መስመሮች በአግባቡ መተግበርና በሕይወቱ መተርጎም አለበት፡፡

እነዚህም የግንኙነት መስመሮች ስትመጸውቱ ፤ስትጸልዩ እና ስትጦሙም በማለት ከአሁን በፊት አይሁዳውያን ያደርጉት እንደነበር  ከጠቆመ በኋላ በክርስቲኖች ዘንድ ግን የድርጊት ማስተካከያና አቅጣጫ የሚያስፈልገው በመሆኑ ²እናንተ ግን² በሚል አባታዊ መመሪያ ተስተካክሎ እናገኘዋለን፡፡ ጾም ፤ጸሎትና ምጽዋት የሸፈተውን የሰውን ልብ ወደ መጸጸትና ንስሐ የሚያመጡ ብርቱ መንፈሳዊ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ጾም ያለ ጸሎትና ምጽዋት የረሃብ አድማ እንደሚመስል ሁሉ ጸሎትም ያለ ጾምና ራስን መግዛት ትርፉ    ውጤት አልባ ጩኸት መሆኑ ውስጣችን የሚቀበለው ሐቅ ነው፡፡

ጾም የሥጋ ፈቃድ የምናደርግበት፤ ሠራተኞቻችንን የምናስጨንቅበት፤የግፍ ጡጫ የማንማታበትና ለጥልና ክርክር የምንቆምበት ሳይሆን የበደል እስራት የምንፈታበት ፤የተገፉትን አርነት የምናወጣበት ፤የጭቆና ቀንበሩን የምንስብርበት ፤እንጀራን ለተራበ ቆርስን የምናበላበትና የተራቆተውን የምናለብስበት መሆን እንዳለበት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ከነገረን በኋላ አምላካዊ መልሱንም ብርሃንህ እንደንጋት ኮከብ ይበራል፤ ጽድቅህም በፊትህ ይሔዳል በማለት ያስቀምጣል፡፡ (ኢሳ 58÷1-13)

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

ልዩ ልዩ

በፌስቡክ ያግኙን

©2018 Copyright - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት