• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

  • "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ የሥራ መመሪያ ሰጡ!

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ አእላፍ በላይ ፀጋዬ ጋር በመሆን ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር ትውውቅ በማድረግ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እኛ መልእክተኞች ነን፣ ከላይ ተልከን ቤተ ክርስቲያንን እንድናገለግል መጥተናል ስለዚህ በሀገረ ስብከቱ የነበረው መልካም ገጽታ በማስቀጠል ስህተቱን ደግሞ በማረም እንሠራለን ብለዋል። […]

የማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን (Lideta-EPMS) የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ (Software) አበልጽጎ አስመረቀ!!

በአዲሰ አበባ ሀገረ ስብከት በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ የIct ባለሙያዎች የተዘጋጀው የሠራተኞች እና የምዕመናን አጠቃላይ መረጃ መመዝገቢያ እና ማስተዳደሪያ Lideta Employee & Parishioners Management System (Lideta-EPMS) የተሰኘ ሶፍትዌር አበልጽጎ በዛሬው ዕለት አስመረቀ። የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲና የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ […]

የሕግ መጻሕፍት ትሩፋት

የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን (Lideta-EPMS) የተሰኘ መተግበሪያ አበልጽጎ በሥራ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ!!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን Lideta Employee & Parishioners Management System (LEPMS) የተሰኘ መተግበሪያ አበልጽጎ በአዲሱ በጀት ዓመት ሥራ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። በደብሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የማኑዋል ሥራዎችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለመቀየር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዕቅድ የተደገፈ እንቅስቃሴ ተጀምሮ አስፈላጊ ሶፍትዌሮችንና የቴክኖሎጂ መንገዶችን […]

ማኅበረ- ቅዱሳን ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እና ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የእንኳን አደረሳችሁ መርሐግብር አደረገ!!

ሚያዝያ 4 2014 ዓ.ም በሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል  በተዘጋጀው የእራት ፕሮግራም ላይ ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ  አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለክቡር ሊቀጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ ቆሞስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የእንኳን አደረሳችሁ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ  ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። በመርሐ ግብሩም ማኀበሩ ለሚያዘጋጀው ሐዊረ ፍኖት መርሐ ግብር በአጋርነት አብረው ለሰሩ የግልና የመንግሥት […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ተካሄደ!

ለአዲስ አበባና ለጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለ2014 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ፣ የቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነትና የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በርካታ ሊቃውንትና ጥሪየተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት […]

ሕያዉንከሙታንመካከልስለምንትፈልጋላችሁ?/ሉቃ. 24፡5/

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደሚነሣ ቅዱሳን ነቢያት አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ከትንቢቶቹም አንዱ (ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፡፡ ወከመ ኃይል ወኅዳገ ወይን፡፡ ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ፡፡( /የተኛ ሰው ከእንቅልፍ እንደሚነቃ እግዚአብሔር ከሙታን ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ በኋላው በተተከለ መስቀል ጠላቱን ድል አደረገ/ /መዝ. 77፡65/ስለ ጌታችን ትንሣኤ አራቱም ወንጌላውያን ጽፈዋል፡፡ ይህም /ማቴ. 28፡1-15/ […]

“ኒቆዲሞስ “

የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል። ስያሜውን ያገኘው እውነተኛ እውቀትንና ሕይወትን ፈልጎ ነገር ግን ምድራዊ ሥልጣኑን በአይሁድ ሸንጎ እንዳይነጠቅ ፈርቶ በሌሊት ወደ ጌታ  እየሄደ ይማር ከነበረው ከአይሁድ አለቃ ከኒቆዲሞስ ነው። ዳግም ልደትን በተመለከተ ኒቆዲሞስ የጠየቀው ጥያቄና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመለሰው መልስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይ በሰፊው ተብራርቶ ተጽፏል። ኒቆዲሞስ በፍርሃት ተውጦ እየተደበቀ በሌሊት ብቻ […]

“እንደ አብነት ትምህርት ቤቱ ከሰ/ት/ቤትም ጳጳስና ፓትርያርክ መውጣት አለበት…ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ

የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ሁለገብ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ በአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ተጥሏል። ብፁዕነታቸው አንተ አለት ነህ በዚች ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን  እመሠርታለሁ  የሚለውን ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ጥዑም ትምርህት ሰጥተዋል። በሃይማኖት ጸንቶ ማደግ የአሁን ጊዜ ወጣቶች መለያ  እየሆነ መምጣቱ […]

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ!

የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በጉራጌ ሀገረ ስብከት በቅርቡ በተከፈተው በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ” ለሦስት ወራት የሚቆይ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ።ብፁዕነታቸውን ጨምሮ በሌሎች አሰልጣኝ መምህራንየሚሰጠው ስልጠና በጉራጌ ሀገረ ስብከት አጥቢያ አብያተክርስቲያናት በልዩ ልዪ አገልግሎት የሚያገለግሉ አገልጋይ ካህናትን፣የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የሀገረ ስብከት […]

የሕግ መጻሕፍት ትሩፋት

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቀለ መጠይቅ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ የሀገረ ስብከቱ አሰራርን አስመልክተው ከምኒልክ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቀለ መጠይቅ ይመልከቱ ሌሎችም እንዲያዩት በፌስ ቡክ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ….. ሼር ያድርጉ!!!

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዐብይ ጾም መግቢያን አስመልክተው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት

መልካም አስተዳደር ለቤተክርስቲያን አገልግሎትና ልማት በሚል ርዕስ በሊ/ት በድሉ አሰፋ ዓለማየሁ በሀገረ ስብከቱ በተዘጋጀው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተካደው ጉባኤ ላይ ተሳታፊዎች የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ

መ/ር አካለወልድ ተሰማ የአ/አ/ሀ/ስ/ ዋና ስራ አስኪያጅ የከተራ እና ጥምቀት በዓል በዓለም ምን እንደሚመስል ሃይማኖታዊ እንድምታ እና ሥርዓቱ ምንድን ነው ? በሚል ርዕስ የሰጡትን ማብራሪያ ይከታተሉ

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል

ማስታወቂያ

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል

በፌስቡክ ያግኙን

© Copyright - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት | Website by atbiya.com