ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ

2213

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና አማካሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ፡፡
በዛሬው ዕለት ማለትም ህዳር 19/2006 ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የተሾሙት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ÷ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ለ4 ዓመት ከ2 ወር  ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በመኾን አብረዋቸው ሠርተዋል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፣ በቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በከፍተኛ የአስተዳደር ሓላፊነት/ዲንነት በመሥራት በርካታ ተሞክሮዎች እንዳሏቸው የተገለጸው ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡በአሁኑ ወቅትም  የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን (ኤም.ቢ.ኤ)  በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

በመሆኑም ባላቸው ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ በሀገረ ስብከቱ የተጀመረውን የመልካም አስተዳደር ሥራ ከግብ ያደርሳሉ ተብለው ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡

{flike}{plusone}