ማኅበረ- ቅዱሳን ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እና ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የእንኳን አደረሳችሁ መርሐግብር አደረገ!!

ሚያዝያ 4 2014 ዓ.ም በሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል  በተዘጋጀው የእራት ፕሮግራም ላይ ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ  አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለክቡር ሊቀጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ ቆሞስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የእንኳን አደረሳችሁ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ  ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብሩም ማኀበሩ ለሚያዘጋጀው ሐዊረ ፍኖት መርሐ ግብር በአጋርነት አብረው ለሰሩ የግልና የመንግሥት ተቋማት የዕውቅና ሰርተፍኬት በብፁዕነታቸው ተሰጥቷቸዋል።

በመድረኩ ላይ ብፁዕነታቸው ባደረጉት ንግግር ማኅበረ ቅዱሳን አንጋፋ ማኅበር እንደመሆኑ ለአዳዲስ ማኅበራት ልምዱን እና አሠራሩን በማጋራት ቤተ ክርስቲያንን ይበልጥ እንዲያግዝ አደራ እላለሁ ብለዋል።

ማኅበሩ አባቶችን አክብሮ እንዲህ ዓይነት መርሐግብር ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግነው እና ከቤተክርስቲያን ተቀራርቦ ለመሥራት ጥሩ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የሊቀጳጳሱ ፕሮቶኮል ሹም ሊቀ ጉባኤ አባ ኃይሉ እና ታዋቂው ዘማሪ ሊቀመዘምራን ይልማ እንዲሁም የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ ተገኝተዋል።

       በተክለሃይማኖት አዳነ ጋዜጠኛ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *