በቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት የተገኘው 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመናገሻ ገ/ጽ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ዋለ

ዛሬ የካቲት 23/2013 ዓ/ም በልዳው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት የተገኘው 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመናገሻ ገ/ጽ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በበዓሉ አቡነ መቃሬዎስ የምስራቅ ሀረርጌና ሱማሌ ሊቀ ጳጳስ፥ ክቡር መ/ር አካለወልድ ተሰማ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፥ ሊቀ ሊቃውንት ኀ/ሥላሴ ዘማርያም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፥ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ፣ መ/ምሕረት አምኃ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ኃላፊ፣ የገዳሙ አስተዳዳሪ መ/ገነት ክብሩ ገብረጻድቅ፥ የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፥ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ክፍል ኃላፊዎች፥ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና እጅግ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በመናገሻ ገ/ጽ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በዓሉ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ዕለቱን በተመለከተ በሊቃውት ዝማሬ፥ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙርና ትእይንት ቀርቧል።
መ/ር አካለወልድ ተሰማ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ “አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም” (መዝ 25:3) በሚል መነሻነት ዕለቱን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል።
እግዚአብሔርን ከተውን ጠላት ያጠቃናል። በእግዚአብሔር ስንተማመን፥ በእርሱ ተስፋ ተደግፈን ስንኖርና ስንንቀሳቀስ ግን አያሳፍረንም ብለዋል። አያይዘውም ዛሬ የምናስታውሰው የዓድዋ ድል የተገኘው በእግዚአብሔር ኃይልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት መሆኑን አውስተዋል።
በመጨረሻም አባቶቻችንን የረዳና ያላሳፈረ አምላክ እኛም ይርዳን፥ የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን በማለት ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
የገዳሙ አስተዳዳሪ መ/ገነት ክብሩ ገብረጻድቅም ንጉሥ ምንሊክን የረዳ አምላክ እኛም ይርዳን ብለው ቤተ ክርስቲያን የዚህ ታሪካዊ በዓል ባለቤት ስለሆነች ከዚህ በላይ ደመቆ እንደኪበር የራስዋን አስተዋጽኦ ታደርጋለች ብለዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ መቃሬዎስ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ቀን አባቶቻችን በእዚአብሔር ኃይልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት ድል ላደረጉበት ታላቅ በዓል በሰላም አደረሰን ብለው በመጀመር ለህዝበ ክርስቲያኑ ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል። በመጨረሻም በዓሉ በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቡራኬ ፍጻሜ ሆኗል።

ፎቶ ግራፍ በመ/ር ዋሲሁን ተሾመ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *