በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ክፍል አስተባባነት በክፍለ ከተማው ሥር ለሚገኙ አገልጋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተሰጠ!!

መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም የክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅ መ/ብ ሩፋኤል የማነ ብርሃንን ጨምሮ የክፍለ ከተማው እና የገዳማትና አድባራቱ ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብሰባ አዳራሽ በሁለት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠና መርሐግብሩን በጸሎት የከፈቱት
የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እንደዚህ ዓይነቱ የመተናነፅና እርስ በእርስ የመሳሳል ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር መሰጠቱ በዚህ ዘመን ለምንገኝ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ወሳኝ መሆኑን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎችም ያገኙትን የስልጠና ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙና ወደ ተግባራዊ ሕይወት እንዲለውጡትም አሳስበዋል፡፡
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርስቲ መ/ር
መ/ሰ አባ ጌዴዎን ብርሃነ”ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን”(2ኛተሰ.3:6) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ መነሻ በማድረግ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ሥርዓተ አምልኮ ዙሪያ አጭር ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርስቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአገልጋይነት ሥነ ምግባር ዙሪያ ጊዜ ተኮር የሆነ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የስልጠና መርሐ ግብሩን የመሩትና በበላይነት ያስተባበሩት የክፍለ ከተማው የትምህርትና ስልጠና ክፍል ኃላፊ አባ ገሪማ ተፈራ ይህ ስልጠና እንዲሳካ በገንዘባቸው ድጋፍ ላደረጉ፡
በብዙ ድካም ውስጥ ሆነው ዕውቀታቸውን ላካፈሉ እና ተረጋግተው በመቀመጥ ስልጠናውን ለተካፈሉ በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡ ወደፊትም በተሻለ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
የስልጠናው ታዳሚዎችም በክፍለ ከተማውም ሆነ በሀገረ ስብከቱ ደረጃ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ጅማሬ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን ገልጸው ለአገልግሎት ውጤታማነት ሌሎች አገልጋዮችም በእንደዚህ ዓይነቱ ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ ቢደረግ መልካም መሆኑን አውስተዋል፡፡
በመጨረሻም የክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን የቅድስት
ቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ መጥቷል፡ይህንን ውስብስብ ችግር ለመፍታት ደግሞ በእንዲህ መልኩ መወያየትና መነጋገር እንዲሁም የጋራ መፍትሔ ማስቀመጥ አለብን ለዚህ ደግሞ የእናንተ ድርሻ ዋጋው የማይተመን ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ:-መ/ር ሽፈራው እንደሻው

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *