በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት በጽርሐ ንግሥት ሐና ማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተሠሩ ያሉ መሠረተ ልማቶችን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ጉብኝት ተደረገ

የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህናት ሥር በምትገኘው ጥንታዊቷ የፅርሐ ንግሥት ሐና ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሠራትላይ የሚገኙትን መሠረተ ልማቶችና ልማቶቹን ለማፋጠንና በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ እየተደረገ ያለውን የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት መዝገቡ
ላቀው በጉብኝት መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ገለጻ በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም በደባልነት ትኖር የነበረውን ጽላት በንግሥት እቴጌ መነን አሳሳቢነትና መልካም ፈቃድ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ተሠርቶ ወደቦታው
እንደገባችና በዚህ ዓመትም የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ 100ኛ ዓመት እንደሚከበርም አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም በደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤትና ሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ ከፍተኛ ትብብር”የገንዘብ ምንጮቹም እኛው ሰሪዎቹም እኛው”በሚል መሪ ቃል ለአራት ቀናት ያክል የተዘጋጀው የቴሌቶን መርሐ ግብር ዋና ዓላማው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችንና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ የሚያስችለውን ገቢ ለማሰባሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ክቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማ የቦታውን ታሪካዊነት ገልጸው በዚህ ቦታ ላይ የነበረው የመድኃኔዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለባለቤቱ የማይመጥን ነበረ፡ አሁን ግን ያንን ታሪክ ልታደርጉና ባለቤቱን ልታከብሩ የጋራ ርብርብ ጀምራችኀል፡ የሕዝበ ክርስቲያኑም ቁጥርና የልማት ሥራዎቹ ፍጥነት የከተማ ጫፍ አንደመሆኑ አይደለም፡ እና ልትመሰገኑ ይገባችኀል ብለዋል፡፡
ብፁዕነታቸውም ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ ዓይነት መርሐግብር በማዘጋጀቷ የምዕመናኗን ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ያስችላታል፡መሬት ላይ ከወደቀው የልማት ሥራዎች ባሻገር በሰው ልብና አእምሮ ላይ በእጅጉ የወንጌሉን ልማትም መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡ቃለ ምዕዳንና አባታዊ መልእክትም አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- መ/ር ሽፈራው እንደሻው
ፎቶ:- መ/ር ዋሲሁን ተሾመ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *