በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤትና የአ/አ/ሀ/ስ/ ጽ/ቤት ኮሚቴዎች ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ውይይት አደረጉ

መጋቢት 21/2012 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ ዋና ጀነራል እንደሻው ጣሰው እና ምክትል ጀነራል መላኩ ፈንታ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጥር በመገኘት ስለ ወረርሽኙ ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል።
በውይይቱ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ ቤተ ክርስቲያን የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት አስፈላጊውን ውሳኔ ወስናለች የሚቀረን ነገር የተወሰነውን ወሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መልአክ ሕይወት አባ ሀይለ ገብርኤል ነጋሽ ስለ ችግሩ አሳሳቢነት ጠለቅ ያለ ሀሳብ አንስተዋል፣ ሀገረ ስብከቱ መንግስት የሰጠውን አቅጣጫ በመከተል ጽ/ቤቱ ለጊዜው የተዘጋ ሲሆን የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስፈላጊውን ግንዛቤ መፈጠር እንዲቻልና ዘርፍ ብዙ ሥራ መስራት አሰፈላጊ ስለ ሆነ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ኮሚቴ አዋቅሮ ሥራ መጀመሩን በውይይቱ አንስተዋል።

የፌዴራል ፓሊስ ምክትል ኮሚሽን አቶ መላኩ ፈንታ ሁሉም አማኞች ወደ ፈጣሪያቸው መፀለይ አለባቸው በጦር የማናሸንፈዉን ጠላት ከፊታችን ተደቅኗል በሐላፊነት መንፈስ ከተንቀሳቀስን፣ የሚሰጡትን መመሪያዎች ካከበርን በሽታውን እናሸንፈዋለን በየአድባራት ያለው ሁኔታ ትንሽ አሳሳቢ ነው፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከታች ያሉትን የሥራ አላፊዎችን ጠንከር ያለ መመሪያ መስጠት ይገባል፣ ፖሊስ የሕዝቡን ሰላም የመጠበቅ ሁለንተናዊ ደህንነት የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት የሚሰጡትን ቅድመ ጥንቃቄ ችላ በሚሉ አካላት ላይ አስፈላጊውን ነገር ይደርጋል ብለዋል ።

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ጀነራል እንደሻው ጣሰው በበኩላቸው ሰለ ቫይረሱ ሰፊ ግንዛቤ ያሰጨበጡ ሲሆን ሁሉም ሰው አሁን ልባም ሆኖ መንቀሳቀስ አለበት በማለት ቅድመ ጠንቃቄ ያደረጉ ሀገራት የተሻለ ሥራ እንደ ሰሩ እኛም ከእነሱ መማር እንደለብን ተናግረዋል ።

                      በሀገረ ስብከቱ ሕዝብ ግኑኝነት ዋና ክፍል
0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *