ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B+ G+15 ሕንጻ ግንባታ ባርከው አስጀመሩ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ሊገነባው ያቀደው ባለ 3B + G+ 15 ሕንጻ ግንባታው በጸሎት ባርከው አስጀምረዋል።
ብፁዕነታቸው ሕንጻው ለቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና በብዙ ምእመናን በጉጉት የሚጠበቅ መሆኑን በመጥቀስ ግንባታው እንዲፋጠን ትእዛዝ ሰጥተዋል።
ሕንጻው ተጠናቅቆ ሥራውን ጀምሮ ማየት የሚናፍቅ ብዙ ነው ያሉት ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ይህን እውን ለማድረግ የግንባታው ቁፋሮ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ሕንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሥራው ያለ ምንም መቋረጥ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የሚገነባው ሕንጻ ከ70 በላይ ፓርክ ያለው ሲሆን ብፁዕነታቸው ግንባታው ሲጠናቀቅ በሕጻው ጫፍ የምትገኘው ባለ ሁለት ወለል ፔንት ሀውስ ለሀገረ ሰብከቱ መንበረ ጵጵስና ሆኖ እንደሚያገለግልና ሀገረ ስብከቱ ከፐርሰት ውጪ የራሱ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑን ባለፈው ወር መግለጻቸው የሚታወስ ነው ።
የሕንጻው መሠረተ ድንጋይ ባለ 10 ፎቆ ( G+ 10) ሁለገብ ሕንጻ በሚል በግንቦት 2010 ዓ/ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተጣለ መሆኑን ይታወሳል።
በመርሐ ግብሩ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መ/ር ታዴዎስ ሽፈራው የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ፣ መጋቤ ሐዲስ ለማ በየነ የሀገረ ስብከቱ የሥነ-ምግባር ዋና ክፍል ኃላፊ እና ሌሎች ሠራተኞች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ
ፎቶ በመ/ር ዋሲሁን ተሾመ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *