ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ!

የአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በጉራጌ ሀገረ ስብከት በቅርቡ በተከፈተው በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ” ለሦስት ወራት የሚቆይ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ብፁዕነታቸውን ጨምሮ በሌሎች አሰልጣኝ መምህራንየሚሰጠው ስልጠና በጉራጌ ሀገረ ስብከት አጥቢያ አብያተክርስቲያናት በልዩ ልዪ አገልግሎት የሚያገለግሉ አገልጋይ ካህናትን፣የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የሀገረ ስብከት ልዩ ልዪ የሥራ ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን እንዲሁም የአጎራባች ወረዳዎችና አህጉረ ስብከት አገልጋዮችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
በቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ”ለሦስት ወራት ያክል እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና ትምህርተ ሃይማኖት(ዶግማ)፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ የስብከት ዘዴ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትን
የሚያጠቃልል እንደሆነም ተረጋግጧል።
በብፁዕነታቸው አሰልጣኝነት “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በሚል ርዕስ ሐሙስና ቅዳሜ በሳምንት ሁለት ቀናት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የትምህርት ተቋም (መንፈሳዊ ኮሌጅ) ከመመሥረት ጀምሮ በተቋቋመው የትምህርት ተቋም በየክፍሉ ተገኝቶ በማስተማር ረገድ ከቀዳማዊ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቀጥሎ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መሆናቸውም ተወስቷል።
በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አርቆ አሳቢነትና ጠንካራ አመራር እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ በብፁዓን አባቶች ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቆ የተከፈተው “ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ” መሥፈርቱን የሚያሟሉ ደቀ መዛሙርትን ከየአህጉረ ስብከቱ ተቀብሎ በወርኃ መስከረም መደበኛ ትምህርት ማስተማር እንደሚጀምር
ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published.