“እንደ አብነት ትምህርት ቤቱ ከሰ/ት/ቤትም ጳጳስና ፓትርያርክ መውጣት አለበት…ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ

የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ሁለገብ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ በአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ተጥሏል።

ብፁዕነታቸው አንተ አለት ነህ በዚች ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን  እመሠርታለሁ  የሚለውን ቃለ ወንጌል ጠቅሰው ጥዑም ትምርህት ሰጥተዋል።

በሃይማኖት ጸንቶ ማደግ የአሁን ጊዜ ወጣቶች መለያ  እየሆነ መምጣቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀው  የደብሩ አስተዳደር እና ሰበካ ጉባእ እንዲሁም የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ያላቸውን አንድነትም አድንቀዋል።

እናት እና አባቱን የሚያከብር ትውልድ እና በሦነ ምግባር የታነጹ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች መኖራቸው ለሌሎች አንዳንድ አድመኛና ስም አጥፊ ቡድኖች አርዓያ ናችሁ በርቱ ብለዋል።

ለቤተክርስቲያን መሠረት የሆነው የአብነት ትምህርት ቤት ብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ እንደሆነ ሁሉ ከሰንበት ትምህርት ቤቶችም ሊቃውንት፣ ጳጳሳትና ፓትርያኮችም መውጣት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ሁለገብ ህንጻ  G+3 ምሰለ ንድፉን በ/ት/ ቤቱ ባለሙያዎች በነጻ የተሠራ  መሆኑ እንዳስደሰታቸው እና ቤተ ክርስቲያንን የሚያንጿት የቤተክርስቲያን ልጆች መሆናቸው ኩራት ነው ብለዋል።

ሁለገብ ህንጻው ለካህናት ልጆች መዋያ የሚሆን መዋዕለ ህጻናትን ጨምሮ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ እና በ2500 ካሬ ላይ ያረፈ በ49 ሚሊዮን ብር የሚገነባ እንደሆነ ከመድረኩ ተነግሯል።

ከሃያ ዓመታት በፊት ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕነታቸው ይመጡ እንደነበር ጠቅሰው ያኔ በብዛት ይገነባ የነበረው ለሙታን የሚሆን መቃብር ቤት እንደ ነበር እና አሁን ለህያዋን የሚሆን የሰንበት ትምህርት ቤት ሁለገብ ህንጻ መገንባቱ ይበል ነው ብለዋል።

የፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የደብሩን አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ አባ ገብረሥላሴ ጠባይን እና የደብሩን ዋና ጸሐፊ መምህር ሰሎሞን ዳዊትን በአንድ ዓመት ውስጥ ያመጡትን ልማት አድንቀው በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በኩል ሽልማት አበርክተዋል።

በመሠረት ድንጋይ መጣል መርሐ ግብሩ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የልማትና እቅድ ዋና ክፍል ሃለፊ መልአከ ምህረት አምሃ መኮንን የተገኙ ሲሆን መድረኩን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ መዊዕ አባ ገብረ ሥላሴ ጠባይ እየመሩት ብፁዕነታቸውም የመሠረት ድንጋይ እንደጣልነው ግንባታው ተጠናቆ ለምርቃቱ ያብቃን በሚል ንግግር ተጠናቋል።

    በተክለሃይማኖት አዳነ ጋዜጠኛ
         ፎቶ በዋሲሁን ተሾመ

18 replies
  1. antalin a precio asequible says:

    You really make it seem so easy with your presentation but I find this matter to be really something that I think I would never understand.
    It seems too complicated and very broad for me.
    I am looking forward for your next post, I will try to get the hang of it!

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *