ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ በዛት ፆታ ደሞወዝ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ
2 ሪከርድና ማህድር /ዶክሜንቴሽንና ዳታ ቤዝ ሰራተኛ 1 ሴት በስምምነት ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሌጅ በአይቲ፤በላይብረሪ ሳይንስ፤በሴክሬታሪ፤እና በተዛማጅ መስክ በዲፕሎማ /በቴክኒክና ሙያ በሌብል 4/ የተመረቀች፤በፀሐፊት ሥራ 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያላት እና በዘመናዊ የሪከርድና ማህደር አያያዝ ሥርዓት ዕውቀት ያላት፤
2 ኮምፒዩተር ፀሐፊና መጽሔት ዲዛይነር 1 ሴት በስምምነት ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሌጅ በአይቲ/ሴክሬታሪ እና በተዛማጅ መስክ በዲፕሎማ /በቴክኒክና ሙያ በሌብል 4 /የተመረቀችና በፀሐፊትና መጽሔት ዲዛይን ሥራ 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያላት ሆኖ የቪድዮ ኤዲቲንግ ሙያ ያላት፤
3 ኮምፒዩትር ፀሐፊ 1 ሴት በስምምነት ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሌጅ በአይቲ፤በሴክሬታሪ እና በተዛማጅ መስክ በዲፕሎማ/በቴክኒክና ሙያ ደረጃ በሌብል 4 /የተመረቀችና በሙያው 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያላት፤

ከላይ ለሥራ መደቡ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ አመልከቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለሰውን ፎቶ ኮፒ በመያዝ በሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ ቢሮ ቁጥር 217 በመቅረብ አስፈላጊውን ማስረጃና ሲቪ በመያዝ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ
ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መጋቢት 21/2010 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት በሀገረ ስብከቱ ኮምፒዩተር ማእከል፤
አድራሻ፡- 4 ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጀርባ፤
ስልክ ቁጥር፡-011 1 56 32 88/0911 12 68 14