ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ በሚል መሪ ቃል በCMC ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ4 ቀናት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በዛሬው ተጠናቀቀ !!!

መጋቢት 14 ቀን /2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳሰ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊ መ/ም በቃሉ ወርቅነህ፡ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽባሕ አባ ጥዑመልሳን አድነውና የደብሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዕዝራ ነዋይ እንዲሁም የደብሩ ካህናትና መምህራን የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት ወርኃዊውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓልና የዐብይ ጾምን የሱባኤጊዜ አስመልክቶ የተዘጋጀው ጉባኤ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ቃለ ምዕዳንና መመሪያ ሰጭነት በዛሬው ዕለት በሰላም ተጠናቋል፡፡
ሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲጠናከርና መንፈሳዊጉባኤያት እንዲዘረጉ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ይህን ለብዙ ሰዎች መጽናኛ የሆነውን የወንጌል መድረክ ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ በሚል መሪ ቃል በደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤትና ልማት ኮሚቴ እንዲሁም በደብሩ ማኅበረ ካህናት፡የሰንበት ት/ቤት ዘማርያንና የአካባቢው ወጣቶች የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ጉባኤ መሆኑን የዕለቱን መርሐ ግብር የመሩት የደብሩ ዋናጸሐፊ መ/ር ዕዝራ ነዋይ አሳውቀዋል፡፡
አያይዘውም የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን ዋና ተልእኮና ዐብይ ተግባር በመሆኑ ከየትኛውም ልማትና አገልግሎት በተለየ መልኩ ሰፊ ትኩረትና በቂ በጀት ተመድቦለት ሊሠራ እንደሚገባው ገልጸው ፡በደብሩ በኩል ወደፊትም ሳምንታዊና ወርኃዊ ጉባኤያትን በማጠናከር ከዚህ በተሻለ መልኩ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
የCMC ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ረቡዕና አርብ በደብሩ የሰብከተ ወንጌል አዳራሽ ለሁሉም ካህናት ስልጠና እየሰጠ ከመሆኑም በላይ ሳምንታዊ ጉባኤ ማክሰኞና እሁድ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁንና ይህንንም አገልግሎት በሁሉም ቦታ ለሚገኙ ምዕመናን ለማዳረስ በደብሩ ስም የFACE BOOk PAGe መክፈቱንም ይፋ አድርጓል፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽባሕ አባ ጥዑመ ልሳን አድነው በበኩላቸው በእነዚህ ተከታታይ አራት ቀናት የእግዚአብሔርን ድምፅ በጋራ ቁጭ ተብሎ የተሰማበትና ንስሐ የተገባበት ሳምንት መሆኑን ገልጸው ብፁዕነታቸውን እንኳን ደህና መጡ ብለዋል፡ለጉባኤው ስኬት ለተሳተፉት አካላት ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሰው በምግብ ብቻ እንደማይኖር ጌታ የተናገረበትን ክፍል ጠቅሰው፡ ከሥጋ በዘለለ ለመንፈስና ነፍስ ምግብ የሚሆነውን የእግዚአብሔር ቃል
ሁሉም እንዲመገብ ይህንን መንፈሳዊ ጉባኤ በማዘጋጀት ለደከማችሁት በሙሉ ምሥጋና ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ቅድሚያ ሰጥተው
ሊሠሩትና ትልቅ በጀትሊመድቡለት የሚገባው ለወንጌል አገልግሎት መሆን እንደሚገባው በጽኑ አሳስበዋል፡፡
ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ የሀገረስብከቱ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል፡ከሰባቱም ክፍላተ ከተሞች የሰብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም ከገዳማትና አድባራቱ ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
ዘጋቢ መ/ር ሽፈራው እንደሻው
ፎቶ በመ/ር ወሲሁን ተሾመ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *