የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳዲስ የመተግበርያ ሲስተም ሶፍት ዌሮች ሥራ ላይ ሊያውል ነው

 ይህ የቴክኖሎጂ ትግበራ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መ/ር አባ  ሞገስ ኃይለማርያም(ቆሞስ)፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ፣የ7ቱም ክፍለ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች፣  የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ሊቃነ መናብርት፣ዋና ጸሐፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 29/2011 ዓ.ም ተመርቆ በይፋ ሥራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሀገረ ስብከቱ የተሠሩ የቴክኖሎጂ ተግባራት በአጭሩ

 • በቴክኖሎጂ ያልታገዘ አሠራር አዝጋሚ እና አድካሚ ከመሆኑም በላይ የሚፈለገውን ያህል አጥጋቢ ሥራ መሥራት ይቻላል ተብሎ አይገመትም፡፡ ሀገረ ስብከቱም ይህን በመረዳቱ አሠራሩን ለማዘመን ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን 4 ሲስተሞች በአገርኛ ቋንቋ (በአማርኛ) ተሠርተው ሥራ ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡
  • የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Human Resource management system 
  • የንብረትና ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Asset Management System
  •  የመዝገብ ቤት ፋይል አስተዳደር ሲስተም/Archive File Management system እና
  • የእስቶክ አስተዳደር ሲስተም/ Stock Management System ናቸው፡፡
 • ይህ የቴክኖሎጂ አገልግሎት አስፈላጊና ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኖ በመገኘቱ የሀገረ ሰብከቱን ተቋማዊ እንቅስቃሴ በኮምፒውተር የታገዘ፤ዓለም አቀፋዊና ዘመኑን የዋጀ አሠራር እንዲከተል አድርጎታል፡፡
 • በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ያሉትን አጠቃላይ ሠራተኞች ሙሉ የግል መረጃ ተሰብስቦ ወደ መረጃ ቋት/ዳታ ቤዝ/ የማስገባት ሥራ እየተሠራ ይገኛል ፡፡   
 • በሲስተም ሶፍትዌር ያልታገዘ የአሠራር ሂደት ብክነትን ባስወገደ መልኩ ውጤታማ ለመሆን ያስቸግራል። ሀገረ ስብከቱ በስሩ ከሚገኙ ገዳማትና አድባራት ጋር ቀልጣፋ የሆነ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም ወቅታዊ እና ልዩ ልዩ ዳሰሳዎች (ሪፖርቶች) በተፈለገው ጊዜ እና ጥራት ለማግኘት የኢንፎርሜሽን ሲስተም መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል። ይህም የሀገረ ስብከቱ አቅም ግንባታ በማሳደግ የተቀላጠፈ እና ከስህተት የጸዳ አገልግሎት መስጠት ከመቻሉም በላይ ተዘውትሮ የሚታየውን ኋላ ቀር አሠራር ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል፡፡

አራቱም ሲስተሞች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች

1. የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Human Resource management system: –

ይህ ሲስተም የሀገረ ስብከቱ፣የክፍላተ ከተማና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ሙሉ መረጃ መዝግቦ በመያዝ፤ ሥራው የሚመለከታቸው የሀገረ ስብከቱ ሐላፊዎች መረጃዎችን ለማግኘት ቀጥታ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ ሠራተኞች ተመሳሳይ ዶክሜንቶችን በመጠቀም በተፈለገው ሰዓት የምንፈልገውን መረጃ በጥራትና በፍጥነት ለማግኘት ይረዳናል፡፡ይህም የሰው ኃይል፣ጊዜ፣ገንዘብ፣ጉልበት፣ድካም እና የተለያዩ ስጋቶችን ይቀንስልናል፡፡

መረጃ መልሶ ማግኘት ማስቻሉ ተጠቃሚው የፈለገውን መፈለጊያ ቃል በማስገባት የሚፈልገውን መረጃ ማግኝት ያስችላል፡፡ይህም ለተጠቃሚዎች ቀላል የሆኑ ኢንተርፌሶች በመጠቀም መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ወቅታዊና ጥራት ያላቸውን የተደራጁ መረጃዎችና ማመሳከሪያ ሰነዶችን ጥራታቸው ሳይጓል ብዙ ጊዜ በቀላሉ መግኘት ያስችላል፡፡ አጠቃላይ ሲስተሙ፡-

 • የሀገረ ስብከቱ፣የ7ቱም ክፍለ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራ አጠቃላይ የሰው ኃይል ፣መዋቅር  ፣ የሥራ ሂደቶችን ፣ የሥራ መደቦችን …ወዘተ/
 •  የቅጥር ማከናወኛ /የውስጥ እድገት ወይም አዲስ ቅጥር/
 • የእያንዳንዱን ሠራተኛ ማህደር ማደራጀት
 • የግል መረጃ(የሠራተኛው ሙሉ ስም)
 • የትውልድ ዘመን (ወር/ቀን/ዓ.ም.)
 • ፆታ
 • የሥራ መደብ
 • የትምህርት ደረጃ (መንፈሳዊ ትምህርትና ዘመናዊ ትምህርት)
 • አድራሻ(ክ/ከተማ፤ስልክ ቁጥር፣ኢሜል አድራሻ)
 • የቅጥር ዘመን (ወር/ቀን/ዓ.ም.)
 • ወርኃዊ ክፍያ
 • የሠራተኛው ፎቶ
 • የስልጠና መረጃ
 • የተወሰዱ የዲስፕሊን መረጃዎች መመዝገብ
 • የተለያዩ የዓመትእረፍት ማስተዳደር
 • የውሰጡ ስልጠናዎችን ማስተዳደር
 • የሚወሰዱ የዲስፕልን መረጃዎችን ማስተዳደር
 • የደመወዝ እድገት እና የመሳሰሉትን ማስተዳደር
 • የመልቀቂያ ጥያቀዎችን ማስተዳደር
 • የሠራተኞች ዝውውር ማስተዳደር
 • በየደረጃው የሚፈለጉ ሪፖርቶችን ማዘጋጄት …ወዘተ ናቸው፡፡

2.   የንብረትና ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Asset Management System:-

ይህ ሲስተም የሀገረ ስብከቱ፣የክፍላተ ከተማና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ንብረትና ሀብት (ህንፃ፣መሬት፣መኪና፣ኮምፒዩተር፣የቢሮ ዕቃዎችና የተለያዩ የይዞታ ካርታዎች ወዘተ…) ሙሉ መረጃ መዝግቦ የሚይዝ ሲስተም ነው፡፡አጠቃላይ ሲስተሙ፡-

 • የንብረት ምድቦችን /ካታጎሪ/ መመዝገብ እና ማደራጀት
 • ንብረቶችን በምድባቸው መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • ግምጃ ቤቶችን መመዝገብ እና ማደራጀት
 • የንብሬት መጠየቂያ መመዝገብ እና ማስተደዳደር
 • የንብረት ወጪ መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • የግዥ መጠየቂያ መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • የግዥ ማዘዣ መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • የንብረት ገቢ መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • ተመላሽ ንብሬቶችን መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • ከግምጃ ቤት ወደ ሌላ ግምጃ ቤት የሚደረጉ ዝውውሮችን መመዝገብ እና ማስተዳደር
 • በየደረጃው የሚፈለጉ ሪፖርቶችን ማዘጋጀትን ያጠቃልላል፡፡

3.  የመዝገብ ቤት ፋይል አስተዳደር ሲስተም/ File Management system:-

ይህ ሲስተም እስከ አሁን የነበረውን ባህላዊ/manual የሀገረ ስብከቱ ሪከርድ ክፍል አሠራር ወደ computerized system ለመቀየር የሚያስችል ሲሆን ይህም በልምድ ይከናወን የነበረውን አሠራር ከመቅረፉም በላይ ሥራው ከሀሜት በፀዳ መልኩ እንዲሠራ ይረዳል፤በዚህም መሠረት እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ የተሠሩት እና ወደ ፊት የሚሠሩትን ሥራዎች ሁሉ  ወደ አዲሱ መረጃ ቋት/ሲስተም/ከገባ በኋላ የተለያዩ የመፈለጊያ መንገዶችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚያስችለን ሲስተም ነው፡፡

4.  የእስቶክ አስተዳደር ሲስተም/ Stock Management System

አጠቃላይ የሀገረ ስብከቱ አላቂ ዕቃዎች ዝርዝር መዝግቦ የሚይዝ ሲስተም ሲሆን ይህ የቴክኖሎጂ ሲስተም ሀገረ ስብከቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በዘመናዊ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ የታገዘና አንድ ማእከላዊ በሆነ ኮምፒዩተር ላይ ሲስተሙ በመጫን በLocal Area Network IP Address አማካኝነት ሥራው የሚመለከታቸው አካላት በሀገረ ስብከቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው በንብርት ክፍል ያሉትን ኣላቂ እቃዎች ዝርዝር በቀላሉ መቆጣጠር /ማስተዳደር የሚችሉበት ሲስተም ነው፡፡

 • ቀደም ሲል የተሠሩ የቴክኖሎጂ ሥራዎች
  • ሀገረ ስብከቱ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ አፊሻል ድረ-ገፅ በ2 ቋንቋ አዘጋጅቶ በአዲስ መልክ ሙሉ ዲዛይኑ ተሻሽሎ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
  • ድረ ገጹ ከዩትዩብ ቪድዮዎችን እና ፌስቡክ በቀጥታ እንዲገናኝ በመደረጉ በሁሉም ሶሻል ሚዲያዎች በዓለም ላይ በቀላሉ መሰራጭት እንዲችል ተደርጓል፤
  • በጣም የተሻሻለ የፎቶ አቀራረብ ፤የፒዲኤፍ እና ሌሎች ፋይሎችን በቀላሉ መጠቀም እንዲቻል ተደርጓል፤
  • ከማኅበራዊ ድረገጾች ጋር በተጣመረ መልኩ መሥራት በመቻሉ (ፌስቡክ፤ ዩትዮብ ፤ቲዊትር፤ሊንክድ ኢን፤ስካይአይፒ እና ሌሎችም) በብዛት የመነበብ እድሉ አድጓል፡፡
  • ድረ-ገጹ ዘመኑ ባስገኘው ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ ፤ታሪክ እንዲሁም አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለዓለም ሕዝብ በማዳረስ ዓለም አቀፋዊ ሚድያ ሆኖ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት መስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጠይም ሀገረ ስብከቱ ከዚሁ የበለጡ የቴክኖሎጂ ሥራዎችን ለመተግበር በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ 

                                   በሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ክፍል

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *