የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ የሚፈጅ የአልባሳት፥ የምግብና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት ጽ/ቤት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ተወካዮች እና የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት በተገኙበት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ርክክብ ተደርጓል።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያው ጃንደረባ ትውልድ መንፈሳዊ ማኅበር ሥራው ከመጀመሩ አስቀድሞ ዕቅዱንና ዓላማው ወደ ሀገረ ስብከታችን አቅርቦ በማስገምገም፥  በሀገረ ስብከቱ ይሁንታና መመሪያ መሠረት እውቅና አግኝቶ መንፈሳዊ ማኅበሩ  እንደተመሠረተ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው አያይዘውም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅርና ሥርዓት ጠብቀው ቤተ ክርስቲያኒቱ ማገልገል ለሚፈልጉ ሁሉ ከልክላ እንደማታውቅ በመግለጽ እንዲህ ዓይነት የበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚያበረታቱ ተናግረዋል።

ማህበሩ ያደረገው የተቀደሰ ተግባር እጅግ የሚያስመሠግን ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ከበጎ ሥራ ጋራ ተባበሩ በማለት በዚህ ሰዓት ሁሉም እንዲተጋገዝና ለመልካም ሥራ እጁን እንዲዘረጋ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድጋፉ ለሁለተኛ ዙር በተደረገ የበጎ አድራጎት ዘመቻ ከምእመናን የተሰበሰበ መሆኑን የተነገረ ሲሆን ማኅበሩ ለወደፊትም ቢሆን እንዲህ ዓይነት መልካም ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት በማኅበሩ ተወካይ ተገልጿል።

ዘገባ በመ/ር ኪደ ዜናዊ
ፎቶ በመ/ር ዋሲሁን ተሾመ

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese
4. ትዊተር :-www.Twitter.com/AddisDiocese

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *