የኮሮና በሽታ መከላከልን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሚገኘው ተላላፊ በሽታ ለአገራችን ኢትዮጵያም ከፍተኛ ስጋት መሆኑን በመጠቆም ወረርሽኙን ለመቋቋም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ያሬድ እንዳሉት፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ባሉባት ሕዝባዊ ኃላፊነት የተነሳ ለዚሁ የመከላከል ሥራ ራሱን የቻለ የተስፋ ግብረ ኃይል በማቋቋም ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቅ ለማድረግ በክፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች።

አሁንም ከብሽታው ራስን መጠበቅና መከላከል እንዲቻል ቋሚ ሲኖዶስ በጊዜያዊነት መዘጋት የሚገባቸው የሥራ ክፍሎች ይፋ አድርጓል።

ሙሉ መግለጫን ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ያንብቡ

መጋቢት 16ቀን 2012 ዓ/ም
ወቅታዊውን ኮሮና በሽታ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፡-
በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሰው ልጆችን ሕይወት በሞት እየቀጠፈ ያለው ተላላፊ በሽታ ለአገራችን ኢትዮጵያም ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱ ታምኖበት ወረርሽኙን ለመቋቋም ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደምንገኝ ይታወቃል፡፡


በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ባሉባት ሕዝባዊ ኃላፊነት የተነሳ ለዚሁ የመከላከል ሥራ ራሱን የቻለ የተስፋ ግብረ ኃይል በማቋቋም ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቅ ለማድረግ በክፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ ትግኛለች፡፡ በቀጣይም ከብሽታው ራስን በተገቢው መንገድ መጠበቅ እንዲቻል ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ በሰፊው በመነጋገር በጊዜያዊነት መዘጋት በሚገባቸው የሥራ ክፍሎች ላይ የሚከተለውን ውስኗል፡፡
ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የተዘጉ መምሪያዎች
ሀ.የመንበረፓትርያርክ ቅርሳቅርስ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር
ጉብኝት
የንባብ አገልግሎት
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር ከአዲስ አበባ እስከ አህጉረ ስብከት ያሉ
ሀ. መንፈሳዊ ዮንቨርስቲዎች
ለ. መንፈሳዊ ኮሌጆች
ሐ. ስልጠና ያልጀመሩ የካህናት ማስልጠኛዎች
መ. መዋዕለ ሕፃናት
ረ. የአብነት ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ የመማር ማስተማሩ ሥራ ቁሞ ደቀመዛሙርቱና ተማሪዎች በእየቤታታቸው የተማሩትን እየቀጸሉና እያጠኑ እንዲቆዩ፡-
በከፊል እንዲዘጉ የተደረጉ፡-
ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እስከ መላው አህጉረ ስብከት ጽ/ቤቱች ለአስቸኳይ ሥራ ከሚፈለጉና ተለይተው እንዲቆዩ ከሚደረጉ ሠራተኞች በስተቀር መላው ሠራተኞች በየቤታቸው ሥራቸውን እንዲያከናውኑና ሲፈለጉና ጥሪ ሲደረግላቸው ከሚመጡ በስተቀር ቤቤታችው እንዲቆዩ፡፡


‹‹ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝባችንን ከሕማም ሞት ሀገራችንን ከልዩ ልዩ መቅሰፍትና ደዌ ይጠብቅልን፡፡
ብፁዕ አቡነ ያሬድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ዋና ሥራ አስኪያጅና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *