ገብር ኄር =ቸር አገልጋይ (ማቴ. 25፥ 21-23)

በቅዱስ ያሬድ ስያሜ መሠረት በዓቢይ ጾም የሚገኝ 6ኛው ሳምንት እሑድ ገብር ኄር እየተባለ ይጠራል። ገብር ኄር ማለት ቸር አገልጋይ ማለት ነው፤ ቀኑ ወይም ሳምንቱ ቸር፣ ቅን እና ታማኝ አገልጋዮች የሚዘከሩበት፣  የቸርነቱ ባለቤት ርኅሩህ አምላካችን የቸርነቱና ምኅረቱ ብዛት በማሰብ በቅን አገልጋዮች  የሚዘመርበት፣ የሚመሰገንበትና የሚመለክበት ጊዜ ነው፡፡

ወቅቱ ስለ አገልጋይና በባለቤቱ ለአገልጋዮች ስለሚከፈል ዋጋ፣ ታማኝ አገልጋዮች ስለሚያገኙት ሽልማት እና ተማኝ አገልጋዮች ሆነን ሽልማትን ለመውሰድ እንድንዘጋጅ የሚነገርበት ጊዜ ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያዘዘንን ቃል አክብረን ሠርተን የተገኘን እንደሆነ  ሕያው የደስታ ሽልማት እንደሚሰጠን በምሳሌ አስተምሮናል። (ማቴ. 25፥ 21፣23)። በአንጻሩ ደግሞ የተሰጠንን ኃላፊነትም ሆነ ትእዛዝ ሳናከብር ስንቀር የማይጠቅም አገልጋይ ተብለን ከፍርድ ማምለጥ እንደማንችል  በምሳሌው ተነግሯል (ማቴ. 25፥ 30)።

በዚህ መልክ ሁላችንም ውስጣች መመርመር አለብን። በመጀመሪያ ደረጃ የተሰጠን ለይተን ማወቅ አለብን፣ በመቀጠል ታማኝ ባሪያ ሊያስብል ሕይወት አለን ወይ?  የሚጠብቀኝ ሽልማቱ ወይስ ፍርዱ ብለን በቃሉ ሚዛን ሕይወታችን መመዘን ያስፈልጋል።

ለምሳሌ የያዝነው ጾም መሠረተ ሓሳቡ 40 ቀንና 40 ሌሊትን በመጾም በመጨረሻም ስለ እኛ ሕማማቱንና ስቃዩን ታግሶ በሞቱ ሕይወት የሆነል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ማሰብ፣ መዘከር፣ መተባበርና ትእዛዙን በማክበር  በፍቅር እየተመላለስን አምላካችንን ማመስገን እና ማምለክ ነው።

ይህ ሁሉ የሚሆነው ደግሞ  ከስጦታዎች ሁሉ የከበረ የፍቅር ስጦታ  እንደ ተሰጠን ካልዘነጋን ነው። ይህም በነብዩ አንደበት “ወልድ ተውህበ ለነ፤ ወንድ ልጅ ተሰጠን” (ኢሳ 9፡6) በሚል ወርቃማ ቃል ተገልጿል። 
ወልድ የተባለ ከላይ ስሙ የጠቀስነው ስለ እኛ የጾመ (የተራበና የተጠማ) እርሱ ፈጣሪ ሲሆን ስለ እኛ በኃጥአን በፍጡራን አንደበት የተሰደበ፣ ምራቅ የተተፋበት፣ የተገረፈ፣ የተሰቀለና በሞቱ ሕይወት የሆነልን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ዕዳችን የከፈለ፣ ነውራችን ያራቀ፣ ኃጢአታችን ያስወገደ  ዘለዓለማዊ ሕይወታችን መድኃኒታችን ነው።

ሐዋርያትም ታማኝ አገልጋዮች በመሆን በእርሱ ሕይወትና መድኃኒትነት  ብዙ ተአምራትን በመስራት የተሰጣቸውን መክሊት በአግባቡ ተጠቅመውበታል።
ይኸውም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ በምኩራብ ተገኝተው በስሙ ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ ሲያስወግዱ እናያለን።

ሐዋርያቱ ያላቸውን ለይተው በማወቅ ለማን? መቼ እንደሚሰጥ ጠንቅቀው በመረዳት ሲያገለግሉ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው ምስክር ነው። “ጴጥሮስ ግን ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ።”(የሐዋ. ሥራ 3:6)። በማለት ዕድሜ ልካቸውን የቃሉን ባለቤት ትእዛዝ በማክበር አምላካቸውንና ቤተክርስቲያንን በታማኝነት  አገልግለዋል።

የአገልግሎታቸውን ሁሉ ዋጋ ሲጠይቁም ስለ ስሜ ሁሉን የተወና በታማኝነት ያገለገለኝ “መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል” (ማቴ. 19፥29) በማለት ሰማይና ምድር በፈጠረ ቃሉ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።

እኛስ ስጦታውን ተቀብለናል? የተሰጠን ስጦታውስ ለይተን አውቀናል? በታማኝነትስ እያገለገልን ነው?   ነፍሳችን እንመርምር እና ከሽልማት ሁሉ የበለጠ ሽልማት የዘለዓለም ሕይወት እንዳያመልጠን በቃሉ መሠረት እንመላለስ፨

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

በመምህር ኪደ ዜናዊ

6 replies
 1. Medikamente ohne Nebenwirkungen says:

  It’s appropriate time to make a few plans for the future and
  it’s time to be happy. I’ve learn this post and if I may just I want to counsel
  you few attention-grabbing things or tips. Maybe
  you could write next articles regarding this article.

  I desire to read more things about it!

 2. prix du reneuron sans ordonnance says:

  Attractive portion of content. I just stumbled upon your site and
  in accession capital to say that I get in fact enjoyed account your blog posts.
  Any way I will be subscribing for your feeds
  and even I success you access consistently quickly.

 3. Efren says:

  You actually make it seem so easy with your presentation but I find this topic to be really something that I think I would never understand.
  It seems too complicated and very broad for me. I am looking forward for your next post, I will
  try to get the hang of it!

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *