Entries by

የአ/አ/ሀ/ስ/ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃይለገብርኤል ነጋሽ(ቆሞስ) የ2012 ዓ.ም የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

እንኳን ለ2012 ዓ.ም. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ!!! “ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ።አንተ ወታቦተ መቅደስከ።” “አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥አንተና የመቅደስህ ታቦት።”/መዝ. 132፡8/ ነቢዩ ዳዊት ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት ምሥጢር ተገልጦለት፣ ትንቢት ቀድሞለት የጌታችንንና የእመቤታችንን ትንሣኤ ተናግሯል። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍትና ትንሣኤ ደግሞም ዕርገት እንደ ተራ ነገር የሚታይ ሳይሆን የከበረና ምእመናንም በጾም በጸሎት ሁነው የእናታችንን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎችና የክፍለ ከተማ ሠራተኞች በጋራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ

ሐምሌ 24/2012 ዓ.ም (አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ) ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ዛሬ ሐምሌ 24/ 2012 ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፣ […]

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ በሀገረ ስብከቱ ሥር ከሚገኙ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳዎች ጋር ተወያዩ

ሐምሌ 23 ቀን 2012 የአ.አ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ክቡር አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ: የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች የክፍላተ ከተሞች የሥራ ኃላፊዎችና የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ ጠዋትና ከስአት በተደረገው ውይይት የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ አገልግሎት እና የአድባራትና ገዳማት የደመወዝ እስኬል ማስተካከያን በተመለከተ በሁለት አጃንዳዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል። የውይይት መርሐ ግብሩን […]

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በምዕራፈ ሰማዕት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ

ሐምሌ 19/2012 ዓ.ም (አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ) የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በለምዶ 24 ቀበሌ በሚባለው አካባቢ አዲስ በታነጸው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ድምቀት ተከበረ፡፡ከወራት በፊት ቤተ ክርስቲያን ለመትከል በተደረገ የምእመናን እንቅሰቃሴ፤ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶበት የነበረው ይህ ሥፍራ፤ በአካባቢው ምእመናን ከፍተኛ ጥረት እና በሀገረ ስብከቱ የቅርብ ክትትል በአጭር ጊዜ ውስጥ […]

ሐምሌ 18 ቀን በምዕራፈ ሰማዕት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን የቡራኬ ሥነ ሥርዓት ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ያስተላለፉት መልእክት

“በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፡፡” ምሳ. 27፡18 ብጹዕ አባታችን አቡነ ፊሊጶስየተከበራችሁ በዚህ የተሰበሰባችሁ ምእመናን እና ምእመናት የሁሉ ፈጣሪ፣ የሁሉ መጋቢ የሆነው አምላካችን፤ በዚህ በኀዘንና በጭንቀት ወቅት የምንጽናናበት፣ ቃሉን የምንሰማበትን ቅዱስ ቤቱን እንድናከብር ስለፈቀደልን ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁን!!እንኳን ደስ አለን!!!እንኳን ደስ አላችሁ!!! ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን እግዚአብሔርን ደጅ በመጥናት፣ ትእግስትን ገንዘብ በማድረግ የሚገኘውን ልዩ ጸጋ በምሳሌ ሲገልጽልን “በለሱን […]

በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሃያ አራት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የቅዱስ ገብርኤልና የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ተመረቀ

እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ በፍጥነት ተሠርቶ ያለቀው ይህ ቤተክርስቲያን ብፁእ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ የበላይ ጠባቂ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍሉ ኃላፊዎች፣የቦሌ ክፍለ ከተማ ሠራተኞች፣ካህናትና ዲያቆናት፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና የአከባቢው ምእመናን […]

የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በችግኝ ተከላና ክብካቤ ዙሪያ የቀረበለትን ጥናት ተወያይቶ አጸደቀ

የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በችግኝ ተከላና ክብከቤ ፕሮጀክት ዙሪያ ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ፡፡ በሀገረ ስብከቱ ዕቅድና ልማት ዋና ክፍል በኩል በተጋበዙ ባለሙያ ተዘጋጅቶ የቀረበው “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የችግኝ ተከላ እና ክብካቤ ፕሮጀክት” በከተማችን ባሉ ገዳማትና አድባራት የነበረው ዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ሽፋን በልማትና በተለያዩ ግንባታዎች እየተመናመነ በመምጣቱ የደን ሽፋኑን ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ያለመ ነው፡፡በባለሙያ […]

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ በሚሊኒየም ፓርክ ችግኝ ተከሉ

ሰኔ 10 ቀን 2012 የአ.አ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽና የዋና ክፍል ኃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋም ጉባኤ አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ም/ከንቲባ ተወካይና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ፣ እንዲሁም የየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሠራተኞችና በርካታ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በየካ ተራራ ላይ በሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። […]

“ይኩንኪ በከመ ተአመንኪ” /እንዳመንሽ ይሁንልሽ/ ማቴ.15፥28

ይህ ቃል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለከነናዊት ሴት የተናገረው ቃል ነው፡፡ ታሪኩም /በማቴዎስ ወንጌል ም.15፡21-28/ ላይ ይገኛል፡፡ ታሪኩም እንደሚከተለው ተገልጻል፡፡“ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ፡፡ በዚያም ከነናዊት ሴት ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ ማረኝ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዟታል ብላ ጮኸች፡፡ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም፡፡ ደቀመዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው በኋላችን ትጮኻለችና […]

ለአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ ከአሁን በፊት በሚያስተዳድሩበት ደብር ደማቅ የሽኝት መርሐ ግብር ተደረገላቸው

ሰኔ 7 ቀን 2012 የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃ/ገብርኤል ነጋሽ፤ የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ትፍሥት ግርማ እና ሠራተኞች፤ የደብሩ ማኅበረ ካህናትና የደብሩ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች እንዲሁም በርካታ የአካባቢው ማኅበረ ምእመናን በተገኙበት በጀሞ ምሥራቀ ጸሐይ ቅ/ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በቃለ እግዚአብሔር የታጀበ […]