Entries by

አ/አ/ሀ/ስብከት“የሕጋዊነት መርሕ”በሚል ርእስ ለገዳማትና አድባራት የሥራ መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥናታዊ ውይይት አካሄደ

ሀገረ ስብከቱ ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሒሳብ ሹሞች ጋር የሕጋዊነት መርሕ በሚል ርእስ ለግማሽ ቀን የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጥናታዊ ውይይት አድርጓል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶኦም ያይኑ በውይይቱ መክፈቻ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት በአሁኑ ጊዜ ሀገረ ስብከቱ ሆስፒታል ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ሆስፒታል በየቀኑ በሽተኞች ይታዩበታል እና ነው፡፡ ባለ ጉዳዮቹ ሥራ አስኪያጁን ማግኘት አልቻልንም በማለት ያማርራሉ፡፡ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሐላፊዎች ባለጉዳዮችን በአግባቡ ማስተናገድ አለባቸው፡፡ ጉዳዩንም በወቅቱ መፈጸም አለባቸው በማለት አብራርተዋል፡፡  
የመወያያ ጥናቱን ያቀረቡት የሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ሐላፊ መምህር ባሕሩ ተፈራ ባቀረቡት የመወያያ ጥናታዊ

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የኢትዮጵያና የሩሲያን ግንኙት ለማጠናከር እንደምትሰራ ገለፀች

በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገለፀች። ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለኃይማኖት በሩሲያ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ተመልሰዋል። ፓትርያርኩ በጉብኝታቸው ከመላው ሩሲያ ቅዱስ ፓትርያርክ ክሪል ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ወቅትም ቅዱስ ክሪል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአባቶችና በእናቶች ጥንካሬ ተጠብቃ […]

“በገድል የተፈተነ ሰማዕት”

“መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያት በተናገረው ቃል መሠረት በሃይማኖት ምክንያት መከራ እየተቀበለና ስለክርስቶስ እየመሰከረ በግፍ የተገደለ ሰው ሰማዕት ተብሎ ይጠራል፡፡ ቃሉ ከግእዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ሰማዕት ማለት ምስክር ማለት ነው፡፡ ይህ የቅድስናና የክብር ስም የሚገኘውም እንዲሁ በከንቱ ሳይሆን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ከብዙ ተጋድሎና ፈተና በኋላ ነው፡፡ (የሐ. ሥራ 1÷8፤ 22÷26)

የሚድያ አገልግሎትን እናጠናክር!!

በዘመኑ የአነጋገር ዘይቤ ሚድያ እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት በዓለማችን ዙሪያ የንግዱም፣ የማኅበራዊውም፣   የፖለቲካውም፣ የመንፈሳዊ ዓለሙም የሚጠቀምበትና የሚገለገልበት ቢሆንም እንኳን የዚህ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያዋ መሥራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች የታሪክ መዛግብት ይስማማሉ፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ ሚድያ በሁለት ዐበይት ነጥቦች ሊመደብ ይችላል፡፡ አንደኛው በሥነ ጽሑፍ የሚገለጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በስዕልና በድምፅ የሚገለጥ ነው፡፡ ሥነ ጽሑፍ ሥነ ጽሑፍ በተለያዩ […]

21ኛው ክፍለ ዘመን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቤተ ክርስቲያን የሚዲያ አጠቃቀም

እንደየ ዘመኑ አጠራርና አተገባበር ይለያይ እንጂ የሚዲያ አጠቃቀም ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ነው ለማለት ባያስደፍርም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት አንፃር ሲታይ ሚዲያው ምን ያህል እንገለገልበታለን የሚለው ጉዳይ ግን አነጋጋሪ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀደም ሲል በፕሪንትሚዲያ(ጋዜጣና መጽሔት…) በኋላም በተወሰነመልኩ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ(ሬድዮ) ትጠቀም እንደነበር የታሪክ መዛገብት ያስረዳሉ፡፡ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ /ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(ማኅበራዊ ድረ-ገፅ፤ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) በተደራሽነቱ፤በዓለም አቀፍ ስርጭቱ፤በዋጋ ቅናሽነቱ እና ዓለምን ወደ አንድ መንደር በማምጣት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል::