Entries by AAD

“ችግኝን መትከልና መንከባከብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ “ችግኝን መትከልና መንከባከብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው” ሲሉ መልእክት አስተላለፉ።ብፁዕነታቸው መልእክቱን ያስተላለፉት በጉለሌ የእፅዋት ማዕከል በመገኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ባካሄዱበት ነው።የችግኝ ተከላ መርሐግብሩን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጋር በመተባበር ነው።“አብሮነትን […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ በአገና ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ዑራኤል አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ በመጠናቀቁ በብፁአን አባቶች ተባርኮ ተመረቀ

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ በአገና ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ዑራኤል አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ በመጠናቀቁ በግንቦት 21 ቀን በአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርንያ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ተባርኮ ተመርቋል፡፡ አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረተ ድንጋዩ ከተጣለ ከ9 ዓመታት በኋላ ተጠናቅቆ በግንቦት […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ከተጋባዥ እግዶቻቸው ጋር በጉራጌ ሀገረ ስብከት እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርንያ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ከሌሎች እግዶች ጋር በጉራጌ ሀገረ ስብከት እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዊችን ጎብኝተዋል ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳስቱና እንግዶቹ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኝ ብዙ መናንያንና መናንያት ያሉበትን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ልዩ ድጋፍና ክትትል […]

ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያካሄድ በቆየው ጉባኤ ላይ መግለጫ ሰጠ

ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 17ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ግንቦት 20/2013 ዓ.ም ድረስ ሲያካሄድ የቆየውን ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ የቤተክርስቲያንና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ማህበራዊና መንፈሳዊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል። መግለጫው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተሰጥቷል። […]

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የግንቦት 21 ክብረ በዓል በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል ብፁዕነታቸው እመቤታችን “ናሁ እምይእዜሰ ያስተበጽኡኒ ኲሉ ትውልድ ፤” እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤”(ሉቃ 1:48)” እንዳለች ቃሉን እየተተገበረ ነው፤ የቅ/ድንግል ማርያም ማንነትና የማን እናት መሆኗን […]

“በዛሬው ዕለት ያሳያችሁን ተግባር ያላችሁን መንፈሳዊ ጥንካሬና ክርስቲያናዊ አንድነት የሚያሳይ ነው“….ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ብፁዕነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት በ2000 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ተጀምሮ ከ13 ዓመታት የግንባታ ቆይታ በኃላ ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን በጸሎተ ቡራኬ በመረቁ ወቅት ነው፡፡ የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ይህ ድንቅ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ዛሬ በቦታው ተገኝተን ስንባርክና ስንመርቅ ከእናንተ ያልተናነሰ ደስታ ተሰምቶናል፡ምክንያቱም ከበርካታ […]

በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅ/ ድንግል ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተጠናቀቀ አዲሱ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ጸሎትና ቡራኬ ተባረከ

በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅ/ ድንግል ማርያም እና ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በ2005 ዓ/ም የመሠረተ ድንጋዩ ተጥሎ ለ8 ዓመታት በግንባታ ላይ የቆየ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በዛሬ ዕለት በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተባርኳል። በክቡር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪጅ መ/ር ኣካለ ወልድ ተሰማ ጋባዥነት ለምእመናኑ ቃለ ቡራኬና ትምህርት የሰጡት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ […]

“ምእመናን ልጆቻችን በዚህ ጉባኤ ላይ አመኔታ እንዳያጡ በጣም መጠንቀቅ አለብን” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

ምእመናን ልጆቻችን በዚህ ጉባኤ ላይ አመኔታ እንዳያጡ በጣም መጠንቀቅ አለብን ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ገለጹ። ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት በዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው። በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን፣ በሕዝባችንና በደመ ክርስቶስ በተቀደሱ ክርስቲያን ልጆቻችን ላይ ከበድ […]

የአዲስ አበባ ከተማ ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት በቦሌ ደ/ ሳሌም ካቴድራል መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን በጥምቀተ ባሕር ለታቦት ማደሪያ የሚሆን 41ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የቦታ ካርታ ለአዲስ አበባ ሀ/ሰብከት ጽ/ቤት ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አስረከበ

የአዲስ አበባ ከተማ ልማት አስተዳደር ተወካዮች በቦሌ ክ/ከተማ ሥር የሚገኘው የቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጥምቀተ ባሕር ለታቦት ማደሪያ የሚሆን 41 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የቦታ ካርታ በሀገረ ስብከታቸው ጽ/ቤት ተገኝተው ለቡፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አስረክበዋል። ብፁዕነታቸው የከተማ ልማት አስተዳደር ተወካዮችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩአቸው ሲሆን ቦታውን ከታቦት ማደሪያነቱ በተጨማሪ ለልዩ ልዩ የገቢ […]

በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፍ ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎች ተመረቁ

በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም በብሉይ ኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳን፣ በሊቃውንት፣ በቅኔ፣ በድጓ፣ በቅዳሴ፣ በአቋቋምና በኆኅተ ስብከት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች በዛሬ ዕለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽረሐ ተዋሕዶ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተመርቀዋል:: ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለተመራቂ ደቀ መዛሙርት […]