Entries by

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስ መመራቱን ተከትሎ የመጀመሪያውን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሊያካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምሥረታን ታሪካዊ ደኃራ በተመለከተ በሁለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የመሪነት ዘመን እንደተጀመረና የኢትዮጵያው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልትመራና ልትተዳደር የምትችለው በሰበካ አስተዳደር ጉባኤ መሪነት መሆኑን በነበራቸው አርቆ አሳቢነትና አስተዋይነት አስበውና አቅደው አገልጋዮች ካህናትና በእምነቷ ሥር ያሉት ምእመናን የሚመሩበትንና የሚተዳደሩበትን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤን አቋቁመውና የቃለ አዋዲን ሕግ በመንፈሳዊ ምሁራን […]

የእመቤታችን የቅድስት ኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ በእንጠጦ ሐመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በድምቀት ተከበረ

ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፈ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ ፣ የገዳሙ አስተዳዳሪ ጸባቴ አባ ወልደ ማርያም አድማሱ ካሳዬ(ቆሞስ)፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ክፍል ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስለ ተሰበሰበው የሰው ኃይልና የንብረት ሀብት መረጃ አስመልክቶ ገለጻ ተደረገ

በሀገረ ስብከቱ ስለ ተሰበሰበው የሰውና የንብረት ሀብት አስተዳደር ሲስተም፣ የመዝገብ ቤት ፋይል አስተዳደር ሲስተም እና የእስቶክ አስተዳደር ሲስተም አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ገለጻ ተደርጓል::በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፥ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማ ፥ የሀገረ ስብከቱ የየዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት በጽርሐ ንግሥት ሐና ማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተሠሩ ያሉ መሠረተ ልማቶችን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ጉብኝት ተደረገ

የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህናት ሥር በምትገኘው ጥንታዊቷ የፅርሐ ንግሥት ሐና ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሠራትላይ የሚገኙትን መሠረተ ልማቶችና ልማቶቹን ለማፋጠንና በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ እየተደረገ ያለውን የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች […]

ምንዱባንን መደገፍ እና ያዘኑትን ማጽናናት የቤተ ክርስቲያን ዋና ተግባር ሊሆን ይገባል…..ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፡የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፡ የአዲስአበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እንዲሁም የዕርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መግለጫ ተሰጥቷል፡።ይገኛል ተብሎ […]

ሥርዓተ ጸሎት

ጸሎት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና ነው፡፡ ጸሎት ምስጋናም ነው “ይትቀደስ ስምከ” /ስምህ ይቀደስ/ ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” /የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን/ ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14/በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡1.በፍጹም […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በግንባታ ላይ የሚገኘውን ግዙፉን የጀሞ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሕንጻ ቤ/ክ ጎበኙ

በዛሬው ዕለት የካቲት 2/2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን እየተገነባ የሚገኘውን ግዙፉን የጀሞ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ጎብኝተዋል።ብፁዕነታቸው እየተገነባ ያለውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ያደነቁ ሲሆን ግዙፉ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሲጠናቀቅ ለአገልግሎት ምቹ ከመሆኑም ባሻገር ብዙ […]

አዲስ ተሠርቶ የተጠናቀቀው የአንቆርጫ ኮተቤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤ/ክ ብፁዓን ለቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በጸሎት ተባረከ

በዛሬው ዕለት ጥር 29/2013 ዓ.ም የሱማሌና የምሥራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣የሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የየካ ክፍለከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በርካታ ምእመናን በተገኙበት አዲስ ተሠርቶ የተጠናቀቀው የአንቆርጫ ኮተቤ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤ/ክ በጸሎት ተባርኳል።መርሃ ግብሩን የመሩት የአዲስ አበባ […]

በእንጠጦ ሐመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተገነቡ ሕንጻዎች በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተባርከው ተመረቁ

በሐመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም የተገነቡ ባለ አንድ ወለል (G+1) ተግባረ እድ እና (G+5) ሁለገብ ሕንጻ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተባርከው ተመርቀዋልበምርቃቱ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ በምስራቅ ትግራይ የዓዲ ግራት ሊቀ ጳጳስ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ […]

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት በምዕራፈ ሰማዕታት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን የዝክረ ሰማዕታቱ መታሰቢያ በዓል ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ታስቦ ዋለ

ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ሃያ አራት ቀበሌ እየተባለበሚጠራውአካባቢ በምዕራፈ ሰማዕታት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱና የቦሌ ክፍለ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የደብሩ ካህናትና የተጎጅ ቤተሰቦች በተገኙበት የአንደኛ ዓመት ዝክረሰማዕታት በዓል ተከብሮ ውሏል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በሥጋ የተለዩ ምዕመናኗን […]