Entries by tc

“ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምእ”(የእስራኤል ጠባቂ ሆይ አድምጥ)

  በመ/ር ሣህሉ አድማሱ በቤተክርስቲያናችን የቃለ እግዚአብሔር አሰጣጥ መሠረት ከብርሃን ቀጥሎ ያለው ሳምንት ኖላዊ ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ኖላዊ ተብሎ  በሚጠራው ሰንበት “ኖላዊ  ዘመጽአ…” የሚለው የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰት በሌሊት  የአገልግሎት ክፍለ ሰዓት በሊቃውንቱ ሲዘመር ያድራል፡፡ በጧቱ በሥርዓተ  ቅዳሴ ወቅት (ዕብ.13÷16)፣ (1ጴ 2÷21)፣ (የሐ.10÷36-43 በዲያቆናትና  በካህኑ  በንባብ ይቀርባል፡፡ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ አድምጥ፣ዮሴፍን እንደመንጋ  የምትመራ፣ በኪሩቤል  ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ […]

“እውነተኛው የዓለም ብርሃን”

በመምህር ኪዱ ዜናዊ ብርሃን÷ ብርሃን የጨለማ ተቃራኒ ነው፤ ለዚያም ነው ብርሃን የሌለበት ጨለማ ተብሎ የሚጠራው። ጨለማ መኖሩ የሚታወቀው ብርሃን ሳይኖር ሲቀር ነው። ብርሃን በሁለት መልኩ ልንገልጸው እንችላለን÷ ውጫዊ(ዓለማዊ) እና መንፈሳዊ(ውስጣዊ)፤ የመጀመርያው ከተፈጥሮአዊው(ፀሐይ) ወይም ከሰው ሰራሽ የሚገኝ ሲሆን ያንን ብርሃን ወደ ዓይናችን ሲያንጸባርቅ ነገሮችን ማየት እንችላለን፤ ዓይናችን ያ ብርሃን ካላገኘ ግን ጨለማ ነው ምንም ማየት አይችልም። […]

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የዘመናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከትና በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ በተደረገ የጋራ ዝግጅት የዘመናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተግዳሮቶችና  የመፍትሔ ሃሳቦች በሚል ርእስ የተጠና ጥናታዊ ጽሑፍ የሃገረ ስብከቱ ሥራ አስክያጅ መ/ር ጎይትኦም ያይኑ፤የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣የየአድባራቱ ሰባክያነ ወንጌል ሐላፊዎች፣ ሊቃነ መናብርትና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሃ/ስብከት አዳራሽ ታህሣሥ 14/2010 ዓ.ም […]

“እውነተኛው የዓለም ብርሃን”

ብርሃን ሁሉን የሚያሳይና ለፍጡራን ሁሉ የሚጠቅም የተፈጥሮ ፀጋ ስለሆነ መልካሙ ነገር ሁሉ በብርሃን ይመሰላል፡፡ ይሁን እንጂ ከስነ ፍጥረት የሚገኝ ብርሃን ተቃራኒ ስላለው ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂና አስተማማኝ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፡ – ከፀሐይ፣ ከጨረቃና ከክዋክብት እንዲሁም ከእሳት ወይም ከኤሌክትሪክና ከመሳሰሉ የተፈጥሮ ውጤቶች የሚገኝ ብርሃን ጊዜያዊ እንጂ ቋሚና አስተማማኝ ስላልሆነ አንድ ጊዜ ይበራል ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጠፋል፡፡ ምክንያቱም የፀሐይ […]

የሚዘራና የሚያጭድ አብረው ደስ ይላቸዋል

ጠቢቡ ሰሎሞን “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሎ እንደተናገረው የዘርና የመከር ወቅቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ በግብርና ሥራ ተመድበው የሚሠሩ ገበሬዎች በዘመነ ክረምት ይዘራሉ፡፡ በዘመነ መፀው ደግሞ በክረምት የዘሩትን ሰብል ያጭዳሉ፣ ይሰበስባሉ፣ ይከምራሉ፣ ይወቃሉ፡፡ ገለባውን ከፍሬው ለይተው በጎተራ ሲያከማቹ ገለባውን በእሳት ያቃጥላሉ በዚህም ሥራቸው ራሳቸውን ችለው በልተው፣ ጠግበው ለሌላውም ይተርፋሉ፡፡ የመዝሪያ የማጨጃና የመሰብሰቢያ ጊዜያት የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የሠራተኞችም የዕለት […]

ስብከት

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከቀደምት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ እንደመሆኗ መጠን የተመሰረተችበት መሠረተ እምነት፤የተለያዩ ውሳኔዎችንና ሥርዓቶችን ያሳለፈችበትና የደነገገችበት ቀኖና እንዲሁም ከቀደሙት አባቶች የተረከበችው መንፈሳዊ ትውፊቷ  ምልከታዋን የሚያሰፉ  የማንነት መነጽሮቿ ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጡ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ተደራሽነታቸውን ለማስፋትና የአማንያኑን መንፈሳዊ ህይወት ለመገንባት በዓላትንና አፅዋማትን አስመርኩዞ ዘመኑን የሚዋጅና ወቅቱንም የሚዘክር አስተምህሮ በማዘጋጀት፤ተከታዮቿንም በመመገብና […]

የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ዓመታዊ በዓልና የገዳሙን መቶኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በታላቅ ድምቀት አከበረ

በመ/ር ሣህሉ አድማሱ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓተ ቤተ መቅደስ በዓል እና የዳግማዊ አፄ ምኒልክን የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ታህሳስ  3 ቀን ሲአከብር መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዘንድሮውም ዓመት ታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም ባከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓተ ቤተ መቅደስ  እና የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የዕረፍት መታሰቢያ […]

መፃጉእ

በመ/ር ወንድምአገኝ ደጀኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ ሥርዓተ አምልኮና ደንብ ያላት ቤተ-ክርስቲያን ናት፡፡ ሥርዓተ አምልኮዋን ከምትፈፅምባቸው መንፈሳዊ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ፆም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በአዋጅ ከደነገገቻቸው አፅዋማት መካከል አሁን እየፆምን የምንገኘው የነቢያት ፆም አንዱ ነው፡፡ ይህ ፆም ነቢያት የጌታን መወለድ በታላቅ ፍቅርና በጉጉት ሲጠባበቁ የፆሙት ፆም ነው፡፡ ሲጠበቅ የነበረውም የዓለም መድኃኒት […]

“ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲአድነን የእግዚብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ አሉ፡፡”

                                                                                                          በመ/ር ሣህሉ አድማሱ ታቦት ታቦት የሚለው ቃል ቤተ አደረ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሴ ታቦትን ከግራር እንጨት እንዲሠራ ከእግዚአብሔር ታዘዘ (ዘፀ.25፥1) የመጀመሪያው የታቦት አሠራር አራት ማዕዘን ያለው ሣጥን የሚመስል ሲሆን ርዝመቱ 125 ወርዱ 75 ቁመቱ 75 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው፡፡ ታቦቱ በወርቅ የተለበጠ፣ መክደኛውም ከወርቅ የተሠራ ነበር፡፡ በላዩም የሁለት ኪሩቤል ስዕል ተቀርጿል፡፡  የታቦቱም […]

የየካ አባዶ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል እና 24 ካህናተ ሰማይ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ!!

በመ/ር ሣህሉ አድማሱ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት  ሥር የሚገኘው እና ለአስራ አራት ተከታታይ ዓመታት ያህል ሲገነባ የቆየው የየካ አባዶ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤል እና አርባእቱ እንስሳ ብፁዕወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና […]