007

ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሰሜን እና የምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ

የብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሰሜን እና የምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልዕክት

አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፡፡ 1ኛ ቆሮ 15.20

007
ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የሰሜን እና የምስራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ለክብርና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ እንዲኖር የተፈጠረው የሰው ልጅ በአዳምና በሔዋን የእግ/ርን ትዕዛዝ መጣስ የተነሳ ከሕይወት ወደ ሞት፣ ከክብር ወደ ውርደት ወርደው የሞት ሞት ተፈርዶባቸው 5500 ዘመን በፍዳ በመከራ ኑረዋል፡፡ ሞትም የሰው ልጆችን እንዲገዛ ስልጣን ተሰጥቶት 5ሺ ዘመን ከዘለቀ በኋላ በደጋግ ነቢያቱ ፀሎት እና ልመና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም በመወለድ 33 ዓመት ከ3 ወር በምድር ላይ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አይሁድ በምቀኝነት ተነሳስተው በመወንጀል ለስቅለት እንዲበቃ አድርገውታል፡፡

የማይስማማውም አካል ለክፉ ነገር ይስማማልና ክርስቶስን ለመግደል የማይስማሙ ጥል የነበሩት ፈሪሳዊያንና ሳዱቃዊያን ጴላጦስና ሄሮድስ ተስማምተዋል፡፡ ክርስቶስም ሲሰቀል የእርሱ ተከታዮች እጅግ ደነገጡ፡፡ ጠላቶቹም የማይነሳ መስሎአቸው ደስ አላቸው፡፡ ከላይ በጠቀስነው በቆሮንቶስ መልዕክት 1ኛ ምዕ 15 ላይ ሞት ዓለምን እንዲገዛ በሁሉም ላይ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር ይላል፡፡ እስከ ክርስቶስም ድረስ በሁሉም ላይ በስልጣን ገዝቷል፡፡

የኋለኛው ጠላት የሚሻር ሞት ነውና፡፡ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛ፡፡ ገዥ እንዲሆን ከሾመው በቀር ሁሉም ተገዥ ሆኖለታል፡፡ ነገር ግን ይህን ገዥ ለመሻር ለማሸነፍ ገዥ እንዲሆን ያደረገው ራሱ ለዚህ ሞት ተገዝቶ አሸንፎታል፡፡ ለዚህ ነው ክርስቲያን የትንሣኤን በዓል በተለየ ሁኔታ የሚያከብረው ክርስቶስ እንደሞተ ቀርቶ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ቀና ብለው በማሳፈር የት አለ አምላካችሁ ያሸነፈው ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሙታን በመነሳቱ የድል ቀን አድርጎታል፡፡ መጽሐፍም በመዝሙር 77፣ 65 ላይ እግ/ር ከእንቅልፉ እንደሚቃ ተነሣ ይላል፣ ክርስቶስም ከሙታን በመነሳቱ ጨለማ የነበረው ዓለም ብርሀን ሆኖአል ሮሜ 6. 5 ፡፡

የተወደዳችሁ ልጆቻችን ማንም ሰው ሰዎችን በመደገፍ የሰዎችን ደግነት በጎነት ሊመሰከር ሊናገር ይችላል፡፡ ነገር ግን እናትም ብትሆን ስለ ልጂ ራሷ ለመሞት ፈቃደኛ አትሆንም፡፡ ያውም ለደግ ልጂ ፡፡ ክርስቶስ ግን ደግ ሆነን በመገኘታችን ሳይሆን ሊሞትልን ለማይገባው ለእኛ ወንጀለኞች ለሆን በሕይወት ለማኖር የራሱን ሕይወት አሳልፎ ሰጥቶልናል፡፡ ሮሜ 5፣ በትንቢተ ሆሴዕ ምዕ 6 እንደተጠቀሰውም በአዳም ኃጤያት ምክንያት ራሱ እንደሰበረን ራሱ ጠግኖናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፡፡ በሦስተኛውም ቀን ያስነሳል በፊቱም በሕይወት እንኖራለን በማለት ስለ ትንሣኤውና ስለሕይወታችን እንደተናገረው ሁሉ እኛ በትንሣኤው ሕይወት አግኝተናል፡፡ እርሱም ለትንሣኤው በኩር ሆኖ እንደተነሳ እኛም እንነሳለን፡፡

ለዚሁም ደግሞ በትንሣኤው ልናምን ይገባል፡፡ በትንሣኤው አምነን ስናከብር ደግሞ እርሱ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠልን፣ ትህትናን እና ራስን ዝቅ ማድረግን እንዳስተማረን እኛም ትህትናን ገንዘብ በማድረግ በጎ በማድረግ ለሥጋ ወደሙ በመቅረብ፣ አቅም የሌላቸውን በመርዳት፣ አብሮአችሁ እንዲፈስኩ እንድታደርጉ እያልኩ በዓሉ የሰላም የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

እግዚአብሔር ሁላችንንም ይባርክ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ፡፡

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን

በዓቢይ ኃይል ወስልጣን

አሠሮ ለሰይጣን

አግዓዞ ለአዳም ሰላም

እምይእዜሰ ኮነ ፍስሃ ወሰላም

{flike}{plusone}

4

የሰሜን አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ

ቃለ እግዚአብሔር ተንሥአ ወሥጋሁኒ ኢማሰነ

የእግዚአብሔር ቃል ተነሣ ሥጋውም ጥፋት አላገኘውም፤ መበስበስም አልገጠመውም ሥ.ቅዳሴ 256

4
መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መልዕክት

ከዘመናት ቁጥር ልኬት በአፍአ የሚኖር ዘመን እና ዘመናት የማይወስኑት መጀመሪያ በሌለው ቅድምና የነበረ ቃል፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ፤ እርሱ እግዚአብሔር፤ አካላዊ ቃል በተለየ አካሉ ከድንግል ማርያም ሥጋን ተዋሃደ፤ ከኃጢአት በቀር በሁሉ እኛን መሰለ፤ እኛንም ስለማዳን ለመሰቀል ሞት እንኳን ታዘዘ፤ ድካማችንን ተቀበለ፣ ሕማማችንን ታመመ፤ ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለበደላችንም ደቀቀ፤ ከመነገር በላይ የሆነውን ፍቅሩን አሳየን፡፡

እርሱ አምላካችን መስማት ላልቻሉት የመስሚያ ጆሮ፣ የረሃብተኞች መጋቢ፣ ለተጠሉት እና ለተረሱት የቅርብ ወዳጅ፤ የዕውራን ብርሃን፤ የአንካሶች መጽናኛ የሆነ አዳኛችን በእኛ ስለእኛ ተናቀ፣ ተጠላ፣ እንደተቸገረ ቆጠርነው እንኳን ሊጨክኑበት አትኩረው ሊያዩት የሚያሳሳውን በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ አሳራፊውን አንገላቱት፤ አሳላፊውን አሳልፈው ሰጡት፤ የዘመናት የአዳም ዘር ጥያቄ የ5500 ዘመን አደናጋሪ እንቆቅልሽ ይፈታ ዘንድ፤ ከሞት ቀንበር ከኃጢአት ማዕሰር ከሲኦል ሀገር፤ ከመጨካኙ መንደር፤ ነፃ ያወጣን ዘንድ ኤፍታህ ብሎ የፈታ ስለ እኛ ታሰረ በቁጣ ሲጎትቱት በፍቅር ተከተለ፤ ቀንበርን ሊሰብር አመፃን ጥሎ ጽድቅን ሊጨምር ከወንበዴዎች ጋር ተደመረ፡፡

ክብር ይግባውና የኃጢአታችን ዋጋ የሆነውን ዕዳ ከፈለልን እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ ቀድሞ በነቢያት እንዳናገረው ከመቃብራችን ሊያወጣን በመቃብር አደረ የሞትን ኃይል ይሰብር ዘንድ የኃያላን ኃያል በስጋ ሞተ፡፡ አስጨናቂያችን የሆነውን ሞትን ይገድል ዘንድ ሞተ፤ መቃብርን ባዶውን አስቀርቶ ሞትን ያሳፍረው ዘንድ እኛም አፋችንን ሞልተን እንዝትበት ደግሞም እንሳለቅበት ዘንድ ሞትን ቅስሙን ሰብሮ፤ ቈዬውን መዝብሮ፤ ነፍሳትን ማርኮ፤ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በቃሉ እንደተናገረ በሥራውም ብርቱ የሆነ አዳኝና ነፃ አውጪ ስለ መንጋዎች ነፍሱን እንዳኖረ ሁሉ ነፍሱን ያነሣ ዘንድ ሰዓቱ ሆነና በእግዚአብሔርነት ኃይሉ በኀቱም ድንግልና የተወለደ ከኀቱም መቃብር በክብር ተነሳ፡፡ ዮሐ. 10፣17-18 ወተንሣእኩ በሥልጣነ ባኀትትየ ስለዚህ የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን የዘመናት ዋይታችን ጥያቄ ተመልሷል፡፡

እንደወጣን አልቀረን፤ እንደናፈቀን አልተተውንም፤ እንደራበንና እንደጠማን አልቀረንም፤ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ሰጠን ሞት ድል በመነሳት ተዋጠ የተባለው ቃል ተፈፀመ፡፡ ኢሳ 25፣8 የድል ነሺው ልጆች ነንና እንደ ቅዱስ ዳዊት በአምላካችን ኃይል በጠላታችን በአጋንንት ላይ ተራመድን እንግዲህ ሁሉ ይስማ ለቀረቡት ብቻ አይደለም ለራቁትም ሰላም ሆኗል፡፡ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ተነስቷል፤ የሲዖል ደጆች ተከፍተዋል፤ ነፍሳት አርነት ወተዋል፤ ንጉሳችን በክብር ከፍ ከፍ ብሏል፤ በጨለማ ለሚኖር ህዝብ ታላቅ ብርሃን ሆኗል፤ ብርሃንን የሚጎናፀፈው ተነስቷልና፡፡ አሁንስ ይሁን ይደረግልንና በትንሣኤው ኃይል እንድንነሳ ክብሩን እንድናገኝ እንትጋ፡፡ ፊል. 3

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡

መልካም የትንሣኤ በዓል

መ/ሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ

004

ዕለታተ ሰሙነ ሕማማት

ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው?

ከዕለተ ሆሣዕና ሰርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ሐመ ማለት ታመመ ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡

004

ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት፤ ኃጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን፣ ሕማሙን፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡ መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም እግዚአብሔር ይፍታህ አይሉም የሳምንቱ ሥርዓተ ፍትሐት አይደረግም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመሆኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምጽ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መሆናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡

በሰሙነ ሕማማት የሚገኙ ዕለታትና ስያሜያት

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/ ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ …»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡

ዕለተ ሠሉስ /ማክሰኞ/ ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ጥያቄውም ጌታ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር፡፡ /ማቴ.21-23-27/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ «ወይቤሎሙ ኢየሱስ አማን እብለክሙ ከመ መጸብሓውያን ወዘማውያት ይቀድሙክሙ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር»፤ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነት እላችኋለሁ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል ሲል አስተምሯል፡፡ /ማቴ.21-28/

ዕለተ ረቡዕ ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕለቱ የምክር ቀን በመባል ይጠራል፡፡

006

ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትና ፍቅር መታዘዝ እንዲሁም የአገልግሎትን ትርጉም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ሕጽበተ ሐሙስ በመባልም እንደሚጠራ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም «ወሶበ ኀፀቦሙ እገሪሆሙ ነሥአ አልባሲሁ ወረፈቀ ካዕበ ወይቤሎሙ አእመርክሙኑ ዘገበርኩ ለክሙ … ወሶበ አነ እንከ ሊቅክሙ ወእግዚእክሙ ኀፀብኩክሙ እገሪክሙ ከማሁኬ አንትሙኒ ይደልወክሙ ትኅፅቡ እግረ ቢጽክሙ፡፡»፤ «እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንዲህም አላቸው ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?… እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ሲል ተናግሯል፡፡ /ዮሐ.13-12-20/፡፡ ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ወይም ራሱ ምስጢረ ቁርባንን የጀመረበት ቀን በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ /ማቴ.26-26-29/፡፡ አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጐት ቀስ ብለው መጥተው የያዙበት ቀን ስለሆነ በዚህ ዕለት በለሆሳስ /ብዙ የድምጽ ጩኸት ሳይሰማ/ የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ ስለሆነም መላው ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ የሕጽበት፣ የምስጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሓ ታጥበው ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአጽንኦት ታስተምራለች፡፡

ዕለተ ዐርብ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡

ቀዳሜ ስዑር ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዘፍ.1፡3፡፡ ዕለተ ቀዳሚት /ሰንበት ዐባይ/ በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ሁሉ የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ አምላክ በመቃብር አርፎባታል፡፡ ማቴ.27፡61፡፡ በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሜ ስዑር » ትሰኛለች፡፡ ስዑር ቀዳሜ የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡

የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ «ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፡-በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» የምሥራች እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን ቄጠማ ይታደላል ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡

«ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

{flike}{plusone}

የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ቱፊታዊ ክንዋኔዎች

በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈፃፀም መዛግብት አገላብጠን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

{flike}{plusone}

 

አለመሳሳም፡

በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክረቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንሰቀለው ፤እንግለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ስላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሳምንት የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ አይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ እኔ የምስመው እርሱ ነው ያዙት ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም ተንኮል የተሞለበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን ስላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት የይሁዳም ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኽው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ስርወ መሰረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል፡፡ ይቀጥላልም፡፡

ሕፅበተ እግር፡-

ጌታ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ህይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ እለተ እናንተ ለወንድማችሁ እንዲሁ አድርጎ ለማለት የደቀ መዛሙርቱን አግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረኩ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብጹዓን ናችሁ፡፡ ዮሐ 13፡16-17 በማለት ትህትናውን አሳይቷል ጌታ በዚህ እለተ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ አርአዬን ሰጥቻችኋለሁ እናንተም የወንድማችሁን እግር ታጥቡ ዘንድ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል አለ ደቀ መዛሙርቱም ማንይሆን አሉ፡፡ ጌታም ህብስት ቆርሼ፣ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ደንግጠዋል ይሁዳን ማመልከቱ ነበር ለጊዜው አልገባቸውም፡፡ ጌታችን መዳኃኒታችን የሐዋርያቶቹን እግር በማጠብ ትሕትናን ካስተማረቸው በኋላ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሰጣቸው የኦሪትን መስዋዕት የሻረው እና መስዋዕተ ሐዲስን የሠራው በዚሁ እለት ነው፡፡

አክፍሎት፡-

በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ በዓል/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከዓርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታቸን ያዕቆብ እና ዩሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡ ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዋስ አውሳብዩስ የተባሉ ጸሀፍተ ሐዋርያት በስሙነ ህማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደ ማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኽው ነው፡፡ ቅዳሜ ይበላል ማለት ግን ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ በልቶ እንደ ማስቀደስ እና በልቶ እንደመቁረብ ይቆጠራል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮችም ይህንኑ ትውፊት ሲከውኑ አያሌ ዘመናት ተቆጥሯል፡፡

ጉልባን እና ቄጠማ፡-

ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጀና የጸሎት ሐመስ እለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብጽ ተሰደው በሚነጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካው ሊጥ እያጋገሩ ቂጣ መብላት ንፎሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን እንዲሁም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውሃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ስርዓት በእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹን የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ስርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡

ጥብጠባ፡-

በሰሙነ ሕማማት እለተ የዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ቀን ከስገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጠባው የሚደረግለት ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸማ በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ

ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ህዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኃላ ሰርሆተ ህዝብ (የህዝብ መሰነባበቻ) ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል እያንዳንዱን ምዕመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ የጌታን ግርፋት ያስተውሳል፡፡ ማቴ 26፡26 ማቴ 19፡1-3

ቄጠማ(ቀጤማ)፡-

በቀዳም ስዑር ቀሳውቱን ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ አዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመኑም ለቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ እለት ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

 ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡

«ቄጠማ» ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡

የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡

መጽሐፈ ግብረ ሕማማት ታሪኩ ይዘቱና አገልግሎቱ

ግብረ ሕማማት የሚለው የቃሉ ፍቺ የሕማም የመከራ የስቃይ ሥራ ማለት ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለዘሩ ደኅነት የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ በእለትና በሰዓት ከፍሎ የሚናገር የሚያሳስብ መጽሐፍ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያን በሰሙነ ሕማማት የሚደርሱ የምንባብትና የጸሎታትን ዝርዝር በምን ዓይነት ሁኔታና በማን ሊከናውኑ እንዲገባ የሚበይን /የሚናገር/ በመሆኑ ‹‹ግብረ ሕማማት›› ተብሏል፡፡

ታሪኩ፡-

የመጽሐፊ ግብረ ሕማማት መቅድም እንደሚገልጸው ‹‹ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል በሚፋጠኑበት ጊዜ ስለ እርሱ ስለጌታችን ታሪኩንና ተአምራቱን ይከታተሉ ከነበሩት መካካል የተከበሩትና የታወቁ ሊቃውንት በኢንፎስና በገማልያል እጅ ተጽፎ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በክብር ቦታ ተቀመጦ የተገኝ ነው›› ይላል ይኸው መጽሐፈ ግብረ ሕማማት የመጽሐፉን የትመጣ ታሪክ ሲተነትን በየትኛው ገብርኤል እነደነበር አይታወቅ እንጂ ገብርኤል በሚባል የእስክንድርያ ፓትርያርክ የፕትርክና ዘመን የአባ መቃርዮስ ገዳም ሊቃውንት በነበረው ይዘቱና አገልግሎቱ ላይ የማሻሻያ /የማሟያ/ ሥራ እንደተሠራለት ያትታል፡፡/የግብረ ሕማማት መግቢያ/ መፅሐፍ ግብረ ሕማማት በወርቃማው የኢትዮጵያ የስነ ጸሑፍ ዘመን በካልዕ ሰላማ ወደ ልሳነ ግእዝ ተተርጎመ ከ 1340-1380 ግብረ ሕማማት ዘእሁድ ገጽ 466 ለዘመናት ከብራና ወደ ብራና በብዙ ድካም ሲገለበጥ የኖረው ‹‹መጽሐፈ ግብረ ሕማማት›› በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዘመን ፕትርክና ታትሞ ተሰራጭቷል፡፡

ይዘቱ፡- የመጽሐፍ ግብረ ሕማማት ይዘት እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ሥራዎች መድበልም ነው የነገረ ሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የተአምራት፣ የሥርዓትና የህገ መጽሐፍ ነው፡፡ ወይም እኒህን ሁሉ በይዘቱ አካቷል፡፡ የመጽሐፉን ይዘት የሚመረምር ሰው ብሉይንና ሐዲስን ነቢያትና ሐዋርያትን ሊቃውንትን አዋልድ መጻሕፍትን በብዛት ያገኛል፡፡ ይኸውም በዕለት እና በሰዓት ተከፍሎ በሥርዓት የተዘጋጀ የትምህርትና የጸሎት መዝገበ መጻሕፍት ነው፡፡ ለምሳሌ ወቅቱን የሚመለከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን፣ኦሪትን፣ ነቢያትን፣ ሐዲሳትን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ተግሳጽን፣ ተአምረ ኢየሱስን ተአምረ ማርያምን፣ ወዘተ የያዘ መጽሐፍ ነው፡ ለመፅሐፈ ግበረ ሕማማት ይዘት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ፈርጥ የሆኑት ቅዱስ ያሬድና አባ ጊዮርጊስም የድሻቸውን በዜማ የሚጸልዩትን አካትተውልናል፡፡

አገልግሎቱ፡- መፅሐፍ ግብረ ሕማም የስርዓት የምንባብና የጸሎት መጽሐፍ ነው፡፡ ከሆሳዕና ዋዜማ እስከ ትንሳኤ መንፈቀ ሌሊት በእለትና በሰዓት ከፍሎ፣ የቅድመ ተከተሉን መሰረት በማን ምን መባል እልዳለበት እንደ መጽሐፈ ቅዳሴ ሁሉ ይበል ካህን፣ ይበል ዲያቆን እያለ እንዴት ሊፈጸም እንደሚገባ ጽና ይያዙ፣ ጥቁር ይልበሱ፣ በዚህ በኩል ይግቡ፣ በዚህኛው ይውጡ የሚለውን ሥርዓታዊ መመሪያ ለመስጠት ለካህናትና ለምእመናን የሚገባውን ለይቶ የሚተነትን የምስጢርና የትምህርት መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፈ ግብረ ሕማማት ሕማማተ እግዚእነ ከመንገር ባሻገር ለእንባና ለተመስጦ፣ ለትምህርትና ለተግሳፅ ያገለግላል የልሳነ ግእዝ አንባብያንም በስሙነ ሕማማት ሳይገድፉ በማንበብ ተግባራቸውን በጥንቃቄ የሚፈጽሙበትን የንብብ ችሎታቸውን የሚያሳዩበትም ነው፡፡

በብዙ ጥንታዉያን ገዳማትና አድባራት የብራና ቅጂ ያለው መጽሐፈ ግበረ ህማማተ በስሙነ ሕማማት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለጥናትና ምርመር ምእመናንን በብዙ መልኩ ሊጠቅም የሚችል ይዘት ያለው ነው፡፡

ቁጥር

ቁጥር

{flike}{plusone}

002

በዓለ ሆሳዕና እና ታሪኩ

            እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ!!

002

የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩስአሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይም አእሩግ እና ህጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም “ በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው።

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና  ከረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል።

 በዚሁ በዓለ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርአየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካሪያስ እንደተነገረው ‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’ ዘካ.9፣9። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናግሮ ነበር።

ሲመጣም ‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።’’ በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። 2ኛ ነገ. 9፣13 ። የሆሣዕና በዓል በቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡርክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር – በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ መዝ.117፣26 በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ታድላለች ። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚመለከቱ የቅዱስ ማቴዎስ (ማቴ. 21፣1-17)፤ የቅዱስ ማርቆስ፣(ማር.11፣1-10)፤ የቅዱስ ሉቃስና (ሉቃ.19፣29-38)፤ የቅዱስ ዮሐንስ (ዮሐ.12፣12-15) ወንጌላት ይነበባሉ ።

ታዲያ አኛ ይህን ዐቢይ በዓል የምናከብረው እንዴት ነው? በነቢያቱ ከላይ እንደተገለጠው በወንጌላቱም እንደተፈጸመው እርሱ ወደ እኛ የሚመጣበት ጊዜ መቼ ነው? ሲመጣስ ምን እናድርግ? የእግዚአብሔርን መምጫ ጊዜ ማሰብና መዘጋጀት ያለብን እንዴት ነው? ምክንያቱም በዓሉ ከምንም በላይ የሚጠቅመን ለእኛ ነውና ። ስለዚህ ይህን በዓል ስናከብር ሰላምንና ፍቅርን የእርሱን የክብር አመጣጥ እያሰብን ልንተገብረው ይገባል። ለጌታ የማያስፈልግ ፍጥረት የለም ይልቁንም የክብር ዘውድ አድርጎ በመልኩ የፈጠረው ሰው ያስፈልገዋል።ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጠረ ማንም የለም።እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ዓላማና ዕቅድ የተፈጠርን እንደመሆናችን መጠን እግዚአብሔር የሚከብርበትን ሥራ ልንሠራ ይገባል።አህያ በሰው ሰውኛ ሲታይ የንቀትና የውርደት ሊመስል ይችላል ።የአህያን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመለከት ግን

  1. በለዓም በሥጋዊ ገንዘብ መንፈሳዊ ዓይኑ ታውሮ እግዚአብሔር ያልረገማቸውን እስራኤላውያንን ሊራገም ሲሄድ እስራኤላውያንን እንዳይራገም ለመንገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው መልአክ በሚሄድበት መንገድ ላይ ቆሞ ሳለ ከበለዓም ይልቅ ያየችው የበለዓም አህያ ነበረች ። አህያይቱም መልአኩን አክብራ መንገዱን እንደለቀቀችለት ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ዘኅ.22፣23።
  2.  በትንቢተ ኢሳያስ 1፣3 ‘ሰማይ ስሚ ምድርም አድምጪ በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ እሥራኤል ግን አላወቀም’’ እንደተባለው ጌታ በተወለደ ጊዜ ትንቢቱን ምሳሌውን የሚያውቁ እሥራኤላውያን ባላወቁ ባለተቀበሉ ሰዓት በዚያ በብርድ ወራት እናቱ የምታለብሰው ልብስ አጥታ ቅጠል አልብሳው በነበረ ጊዜ ለጌታ ሙቀት የገበሩለት እረኞቻቸውን ተከትለው የመጡ ከበቶች ላሞችና አህዮች ናቸው። ‘ወአስተማወቅዎ አድግ ወላህም’’ እንዲል አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም።።
  3.  በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም ለከብር የተሸከመችው አህያ ናት። ጌታን የተሸከመችው አህያ ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጉላታል። አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ እንደበድባት ነበር፡ ነውም። ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ።

ስለዚህ ክርስቶስ በአህያይቱ ላይ እንዲቀመጥባት ልብስም እንደ ተጎዘጎዘላት እኛም ጌታ በፀጋውና በረድኤቱ እንዲያድርብን ልባችንን ከኃጢአትና ከተንኮል አንጽተን ፍቅርንና ትሕትና ልንጎዘጎዝ ይገባል።

ጌታ በኛ ላይ በፀጋው ሲያድር በእርሱና በቅዱሳኑ ዘንድ ያለን ክብርና ፀጋ ታላቅ ነው። በነገር ሁሉ መከናወን ይሆንልናል።ክርስቶስን በመሸከሟ የአህያይቱ ታሪክ እንደተለወጠ ሁሉ በክርስቶስ ማደሪያነታችን ያለፈው መጥፎ ታሪካችን ይለወጣል።እንግዲህ በእለተ ሆሣዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ በዝማሬ እንደ ንጉሰ እንደተቀበሉት እኛም ሀሴትን አድርገን ‘ሆሣዕና እምርት እንተ አቡነ ዳዊት…’’ በማለት እናመሰግናለን።

              ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን።

ታድላለች

{flike}{plusone}

በሃይማኖት ሽፋን ቅ/ኤልያስ መጥቷል ብለው በኤልያስ ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ንፁሀን ዜጎችን ሲያስደበድቡና ሁከት ሲፈጥሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታሰሩ

ቀደም ሲል በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች የተፃፉትን ጽሑፎች በአህጉረ ስብከታችን ዌብ ሳይት ስናስነብብ መቆየታችን አይዘነጋም፡፡ ምንም እንኳን ጉዳዩ ዘግይቶ በተለያዩ ሚዲያዎች መሰራጨት የጀመረ ቢሆንም ቀደም ሲል ከሁለት ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጀርባ በተለምዶ ቆሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው መንደር ቤተክርስቲያኑንና ህብረተሰቡን ሲረብሹ የቆዩ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤት ጉዳዩን እየባሰ ሲሄድ በመስከረም ወር 2ዐዐ5 ዓ.ም ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ክስ መስርቶ በፍ/ቤት ትእዛዝ ግለሰቦቹ ከተከራዩት ቤት እንዲወጡና አከራዮችም ተከራዮቹ በአስቸኳይ እንዲያስወጡ ውሳኔ ተወስኖ ነበር፡፡

ይሁንና ግን በአፈፃፀም ሂደት የሚመለከታቸው አካላት እስከ አሁን ድረስ እልባት ባለማግኘቱ ካቴድራሉንና በካቴድራሉ ጀርባ ያሉ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡ ግለሰቦቹ መኖሪያ ቤታቸው የት እንደሆነ በእርግጠኛነት ማወቅ ባይቻልም ሁሉም የሚገናኙት ከሥላሴ ጀርባ በተከራዩት ቤት ነው የመገናኛ ሰዓታቸውም ከቀኑ በ11 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡3ዐ ነው፡፡ የተከራዩት ቤት መጠኗ አነስተኛ ብትሆንም እስከ 4ዐዐ የሚደርሱ ሰዎች ኃይማኖትን ይሁን ፖለቲካ፣ እብደት ይሁን ስካር ባልታወቀ ሁኔታ ከበሮ እየመቱ እጣን እያጨሱና መጠጥ እየጠጡ እንደሚያመሹ የሰፈሩ ሰዎች በግልጽ ከመናገራቸውም በላይ ከቅዳሜ በስተቀር ሁልጊዜ እዛው ቦታ ላይ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቤቱ ጎን ያሉ ነዋሪዎች ማለፍ አትችሉም፣ ጫማችሁን አውልቁ ወዘተ እያሉ በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን በሰላም የመኖር መብት ሲያሳጧቸው የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ ይባስ ብሎ በ15/ዐ8/2ዐዐ5 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡3ዐ ላይ እንደ ሰፈሩ ሰዎች አባባል ቁጥራቸው ከ5ዐ – 1ዐዐ የሚሆኑ በሰፈሩ ሰዎች ላይ ለማድረስ ጀምረውት የነበረውን የድብደባ ጥቃት በአካባቢ ባሉት የፖሊስና የመከላከያ ኃይል አማካይነት ጉዳቱ ሊቀንስ ቢችልም በዚሁ ዕለት ጉዳዩን በዋናነት ሲመሩ የተገኙት (የነበሩት)እጅ ከፍንጅ ተይዘው 4 ኪሎ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡

ቦታው ድረስ በአካል ሄደን ለማረጋገጥ እንደቻልነው 3 ሰዎች ተመትተው እቤታቸው ተኝተው አይተናል፡፡ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ቦታው ድረስ በመሄድ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እያደረጉ ሲሆን የካቴድራሉ ጽ/ቤትም ከአሁን ቀደም ከቤቱ እንዲወጡ ፍ/ቤቱ የወሰነበትን ውሳኔ አያይዞ ለፖሊስ ጣቢያው ልኳል፡፡

የአካባቢው ማኀበረሰብም ፖሊስ ጣቢያው ድረስ በመሄድ ለዓመታት በዚሁ ችግር ሲኖሩ መቆየታቸውንና አሁን የደረሰባቸውን ችግር ገልፀው ክስ መስርተውባቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ ባለድርሻ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የቤተክርስቲኒቷን ስም በማጥፋታቸው በህግ ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡

4

የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

4
መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ መልዕክት

ክቡር መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የስብከተ ወንጌልን እንቅስቃሴ አስመል ክተው ለኆኅተ ጥበብ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሙሉ ማብራሪያውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

“ማዕረሩሰ ብዙኀ ወገባሩ ኀዳጥ ሰአልዎ እንከ ለበዓለ ማዕረር ከመ ይዌስክ ገባረ ለማዕረሩ” መከሩ ብዙ ነው ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው እንግዲህ ለመከሩ ሠራተ ኞችን ይጨምር ዘንድ ባለመከሩን ለምኑት /ሉቃ. 10÷2) ለአንድ ባለ አዝመራ ግለሰብ የሚያ ርስ፣ የሚዘራ፣ የተክል፣ የሚኮተኩት፣ የሚያርም፣ ከአራዊት የሚጠብቅ፣ ፍሬውን የሚለቅም /የሚያጭድ የሚወቃ) እንደሚያስፈልገው ሁሉ፡ የእግዚአብሔር አዝመራም እንዲሁ የምእመናንን ልብ በወንጌል የሚያለሰልስ፣ የሚያስተምር፣ የሚያጠምቅ ሕዝብን አሕዛብን ህያዋንና ሙታንን የሚያገለግል ከገቢረ ኃጢአት ጠብቆ ወደ ገቢረ ጽድቅ የሚመልስ ከመጨረሻው ግብ ለንስሐና ለቅዱስ ሥጋው ለክቡር ደሙ አብቅቶ የመንግሥተ ሰማያት ዜጎች የሚያደርጉ፣ የቤተ እግዚ አብሔር መገልገያ የሚሆኑ ንዋያተ ቤተ መቅደስን ሀብትና ንብረትን ዐፀደ ቤተ እግዚአብሔርን ቅጽረ ቤተክርስቲያንን የሚሰበስብ፣ የሚጠብቅ፣ የሚያስጠብቅ፣ የሚያስተዳድር፣ የሚያስተነትን እውነተኛ የእግዚአብሔር አዝመራ ሰብሳቢ ጠባቂ ሠራተኛ ያስፈልጋል፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ኃይለ ቃል እንደተ ገለጸው የዚህ ዓለም አዝመራ ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ማርያም ተገልጦ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጠብ መጋረጃ ለመግለጥ ወደዚህ ዓለም በመጣበት ጊዜ በመዋዕለ ትምህርቱ ከላይ በተጠቀሰው ኃይለ ቃል መከሩ ካህናት ምእመናን ምእመናት ወጣቶች እየበዙ የመከሩ ሠራተኞች ሐዋርያት ካህናት ጻድቃን ሰማዕታት ባነሱበት በመጀመሪያው የክርስትና ዘመን መከር አምላካችን ለብዙ ጊዜ የመከሩ ሠራተኞች እንዳያንሱ ራሱን የመከሩን ባለቤት የታመኑ ሐዋርያትን ካህናትን ልዩ ልዩ ሠራተ ኞችን በየዘመኑ ይሰጥ ዘንድ መለመን እንደሚገባ ለማረጋገጥ ነው፡፡

ወንጌላዊ ቅ/ሉቃስ የጻፈው ቢሆንም ሀሳቡ የእግዚአብሔር መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ወቅት ድርጊት የተነገረ ሳይሆን ዛሬም ቢሆን በገጠር በከተማ በበረሀ በደጋ የእግዚአብሔር መከሩ ብዙ ነውና ይህንን መከር የሚሰ በስብ ሰራተኛ ዛሬም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዘመናችን የአሠራር መርህ ከላይ እስከ ታች ከታች እስከ ላይራሱን የመከሩን ባለቤት የታመኑ ሐዋርያትን ካህናትን ልዩ ልዩ ሠራተ ኞችን በየዘመኑ ይሰጥ ዘንድ መለመን እንደሚገባ ለማረጋገጥ ነው፡፡ ወንጌላዊ ቅ/ሉቃስ የጻፈው ቢሆንም ሀሳቡ የእግዚአብሔር መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ወቅት ድርጊት የተነገረ ሳይሆን ዛሬም ቢሆን በገጠር በከተማ በበረሀ በደጋ የእግዚአብሔር መከሩ ብዙ ነውና ይህንን መከር የሚሰ በስብ ሰራተኛ ዛሬም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በዘመናችን የአሠራር መርህ ከላይ እስከ ታች ከታች እስከ ላይ በተዘረጋው መዋቅር /ከመንበረ ፓትር ያርክ እስከ አጥቢያ፣ ከአጥቢያ እስከ መንበረ ፓትርያርክ የተሰማራ የእዚአ ብሔር ሠራዊት የእግዚአብሔርን አዝመራ ለመጠበቅ ለማስጠበቅ ቀን ከሌሊት ተግተው በየሥራ ዘርፉ ተሰል ፈዋል፡፡

የአዝመራውን አዘገጃጀት ለማሳ መር ነው ቅ/ሲኖዶሰ በቅርቡ አዲስ አበባን በ4 አህጉረ ስብከት እንዲዋቀር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የወሰነው፣ የመዲናችን አንዱ ማእዘን ሰሜን አዲስ አበባ ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ሲፈቀድ፣ ሊቀ ጳጳስ፣ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ 13 የመምሪያ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በድምሩ 24 ገባረ ማዕረር ተሠልፈዋል፡፡ መከሩ እንደ መብዛቱ መጠን በባለ መከሩ በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አዲስ አበባን በ4/አራት/ አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ሲወስን ከአራቱ አንዱ 25 አብያተ ቤተክርስቲያናትን ያቀፈውን የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው፡፡

የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል እና ማቴርያል አደረጃጀትን በተመለከተ

ከላይ እንደገለጥነው በ24 የሰው ኃይል፣ በቀድሞው ሕንጻ በ10 ቢሮ፣ በ2 ተሽከርካሪና ሹፌሮች፣ በ3 ኮምፒውተር ከሌሎቹ አህጉረ ስብከት ጋር በጋራ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌፎን አግልገሎት ተደራጅቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ በልማት የነበሩ የልማት ተቋማት ተደራ ጅተው እንዲቀጥሉ በሰው ኃይል ልማት የተለያዩ የግንዛቤ መልእክቶች ተላል ፈዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በተመለከተ

ቤተክርስቲያኗ ከክርስቶስ በተቀ በለችው አደራ መሠረት የሰው ልጆች የዘር፣ የቀለም፣ የጎሳ፣ የሀብት ልዩነት ሳይደ ረግባቸው በእኩልነት መንፈስ በፍትሐዊ መንገድ “ወይኩን ነገርክሙ እመኒ እወ ወእመኒ አልቦ” ነገራችሁ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ደግሞ ሐሰት ማለት ይሁን እንደተባለው ሕግና መመሪያ የሚፈቅደውን በአጭር ሰዓት መፍትሔ መስጠት ሕግና መመሪያ የማይፈቅደውን በማስገንዘብ መልስ መስጠት በመቻሉ በውይይት ፍትሐዊ አሠራር እንዲነግሥና በሀ/ስ/ፍጹም ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ለማድረግ ተችሏል፡፡ ለአብነት በመንበረ መንግስት ቅ/ ገብርኤል ገዳም፣ በእንጦጦ ደ/ኃ/ቅ/ ራጉኤል ቤተክርስቲያን የነበረውን ችግ ርና የተሰጠውን አመርቂ ስልታዊ መፍትሔ መጥቀ ስ ይቻላል፡፡

ሐዋርያዊ አግልገሎትን በተመለከተ

በሀገረ ስብከቱ በአዲስ አበባ በቀደም ትነታቸው በታሪካዊነታቸው የሚጠቀሱ ገዳማትና አድባራት የሚገኙበት ከመሆኑ አንጻር እስከአሁን በዘወትር ከሚሠሩ የወንጌል አገልግሎት በተጨማሪ ቀደም ሲል በብዙ ምዕናን ዘንድ አድናቆትን አትርፎ የነበረውና በመሀል ተቋርጦ የነበረው የስብከተ ወንጌል የአንድነት ጉባዔ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

በወር 3 ጊዜና በዓመታዊ በዓላት በጥም ቀትና በመሳሰሉ በዓላት በቤተክርስቲያኑ ከሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት በተ ጨማሪ እጅግ ትልቅ ትርጉም ሊሰጠው የሚችል የወንጌል አግልግሎት ለምእ መናን ለማድረስ ተችሏል፡፡

ያጋጠሙ ችግሮች

የሥራና ሠራተኛ አለመገናኘት፣ የበጀት በማዕከል መያዝና ሥራዎችን በተገ ቢው ቅልጥፍና ለማከናወን አለመቻል፣ የቢሮ እጥረት፣ የቢሮ ፈርኒቸርና ኮምፒ ውተር ችግር ዋና ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የወደፊት ዕቅድ

  1.   ሐዋርያው ቅ/ያዕቆብ በመልእክቱ እግዚ አብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ይህንና ያንን እናደርጋለን እንዳለ ያዕ.4÷15
  2.  እግዚአብሔር ወዶና ፈቅዶ በሰጠን ጊዜ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዲ ፈቱ ጥረት ማድረግ፣
  3.  በቅጥርና ዕድገት ዙሪያ ኮሚቴ በማቋ ቋም የቅጥር ሥራ በውድድር እንዲ ከናወን ማድረግ፣
  4. ለአስተዳደር ሠራተኞች የአቅም ግን ባታ ሥልጠና መስጠት፣ ለሰባክያንና ለካህናት ሥልጠና በመስጠት የሰለጠነ የሰው ኃይል ክፍተትን መሙላት፣
  5. የባለ ጉዳይ የመስተንግዶ ቀን በመ ወሰን ተገቢውን መስተንግዶ መስጠት፡፡

በልማት

በየአድባራቱ የተጀመሩ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮግራሞች እንዲፈጸሙ አዳዲስ የልማት አውታሮች በየዘርፉ እንዲሠሩ በሀገረ ስብከቱ ቢሮ የተጠና ልማት እንዲጀመር ማድረግ በማለት የሀገረ ስብ ከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አብራርተዋል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም በበኩሉ የሀገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደነቀ ሁሉም የዚህ ልማታዊ እንቅስቃሴ ተፎ ካካሪ በመሆን የየራሱን የሥራ ውጤት ለያስመዘግብ ይገባል እንላለን፡፡

ምንጭ ኆኅተ ጥበብ መጽሔት

ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲቆም ብፁእ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

ብ ፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደቡብ ሀገረ ስብከት በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የቅዱስ ያሬድ 1500 የልደት በዓል ባከበሩበት ወቅት ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፡፡

‹‹ለዛሬው በዓል ያደ ረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን›› የታላቁን ሊቅ የቅዱስ ያሬድን በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በረድኤት ይጠብቀናል፡፡ ታላቁ የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የደረ ሰውን የዜማ ድርስት ከአእዋፍና ከመላእክት የተማረ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ቅዱስ ያሬድ ባስተላለፈው የዜማ ትምህርት ዛሬ እልፍ አእላፋትን ሊቃውንት እናያለን፡፡ ለቅዱስ ያሬድ የተሰጠው ፀጋ እጥፍና ድርብ ነው፡፡ በደረሰው የዕዝል፣ የአራራይና የግእዝ የዜማ ድርስት ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ ሰማያዊ ሀብት አስተላልፏል፡፡ ይህ አንድ ሺ አምስት መቶ ያስቆጠረው ትም ህርት በአሁኑ ጊዜ የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ይታያል ትውልዱ በዜማው ልቡ እየተመሰጠ ነው ያለው፡፡

የሰማይ ሥርዓት በምድር ተሠርቷልና፡፡ ይህ የሰማይ ሥርዓት የመላ እክት ምስጋና ነው፡፡ እግዚአብሔር በደቂቀ አዳም መመስገን ፈልጎ ነው ይህን የመላእክት ሥርአት ወደ ሰው ያስተላለፈው በዚህ ሰማያዊ ሥርአት የቤተ ክርስቲያን ክብር ተጠብቆ ይኖራል፡፡ ይህም ለምድረ ኢትዮጵያ ብቻ የተሰጠ ሀብት ነው፡፡ በዚህ ሥርአት ቤተ ክርስቲያን ደምቃ እና አሸብርቃ ትታያለች፡፡ በሌ ላው ዓለም የቅዱስ ያሬድ ዜማ ስለሌለ ዜማቸው እኛን አያስደስትም ምን አልባት እነሱን ያስደስት ይሆናል፡፡ የፈረንጆቹ ዜማ ቅጥ የሌለው ዜማ ነው፡፡ የያሬድ ዜማ ለዜማው ብቻ ሳይሆን ሙዚቃውም ከዚህ ዜማ ውጭ አይደለም፡፡ ዛሬ እልፍ አእላፋት ውሉደ ያሬድ አሉ፡፡ አሁን ከፊታችን ያለችሁት ሊቃውንት መከራ አይታችሁ ውሻ ጮሆባችሁ ውሻ ነክሷችሁ የተማረችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ወደፊትም እንደ ዘመኑ ስልጣኔ ዜማው እየተሻሻለ ይመጣል፡፡ ይህ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ትምህርት በአዳሪ ትምህርት ቤት እንዲሰጥ እንመኛለን፡፡ አሁንም ቢሆን ከወትሮው የተሻለ ፍንጭ እየታየ ነው ያለው፡፡ ቤተክርሰቲያን ለዚህ ሥርዓት መሻሻል ብርቱ ጥረት ታደርጋለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ርህራሄ ናት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ቅድስት መሆን አለባት፡፡

አሁን እንደምናየው ግን መልኳን እየለወጠች ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ መልካቸውን እየለወጡ ናቸው፡፡ ቅድስናችን እየተሸራረፈ ነው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጥሩ ያልኑ ነገሮች ይሰ ማሉ፡፡ አደራችሁን እንጠንቀቅ፡፡ ዓላማ ችንንም አንልቀቅ ዓለም እንደሆነች አስቸ ጋሪ ናት፡፡ ብዙ የሚያብረቅርቅ ነገር አለ፡፡ ተገቢ ያልሆነ የሀብት ክምችት አለ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያልተያያዘ ድርጊት ይታያል፡፡ ቤተክርስቲያን የሀቅ፣ የጽድቅ እና የእምነት ቦታ ናት፡፡ አሁን ግን ይህ ቅዱስ ሀብት እየተጓደለ ነው ያለው ማህበረ ምዕመናን ግን ያላቸውን እና የሌላቸውን እየሰጡ ናቸው፡፡ ገንዘባችሁን በእውነተኛው ቦታ ማዋል አለባችሁ፡፡ እምነቱ፣ ሀቀኝቱ፣ መል ካም አስተዳደሩ ከቤተ ክርስቲያን መገኘት አለበት ፡፡ ለትውልዱ መልካም ምሳሌ መሆን አለባት፡፡ ቤተ ክርስቲያን መሸራረፍ የለባትም በመሠረቱ ሰው በባህርዩ ደካማ ነው፡፡ ድካምም ይሰማዋል እግዚአብሔር አምላክ ሁላችሁንም ይባርካችሁ ከታላቁ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ በረከት ያሳትፋችሁ ዘመኑን የሰላም ዘመን ያድርግልን፡፡ ፆሙ ለሀገር የሚጠቅም የሀገርን አንድነት የሚአስጠብቅ ያደርግልን ለብርሃነ ትንሳ ኤው በሰላም ያድርሰን በማለት ሰፋ ያለ አባታዊ ትምህርትና ቃል ምዕዳን አድር ገዋል፡፡

በመጨረሻም የዝግጅት ክፍላችን በቅዱስነታቸው አባታዊ መልእክት በመመራት ከላይ እስከ ታች ከታች እስከ ላይ ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሁሉ ከሙስና እና ከብልሹ አሠራር በመላቀቅ፡፡ መል ካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ልማት እንዲ ስፋፋ ጥረት ማድረግ ይገባል እንላለን፡

ምንጭ ኆኅተ ጥበብ መጽሔት

በሃይማኖት ሽፋን “ተረፈ አይሁዳዊነት በኤልያሳዊነት ስም ሲበቅል”

ሰሞኑን በከተማችን አዲስ አበባ ““የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቷል፤ የአለም ፍጻሜ ቀርቧል” የሚሉ አካላት ተነስተዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ነብዩ ኤልያስ መጥቶ አዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ቤተመንግሥቱንና ቤተክህነቱን ለማጥራት ተዘጋጅቷል ፡፡

ከሚያጠራቸው የቤተክህነት ጉዳዮችም ሦስቱ ትኩረት አግኝተዋል ይላሉ፡፡ “የመጀመሪያው ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ስህተት ነው ፤ ስማችን ተዋህዶ ነው ፤ መለበስ ያለበት ልብስ ነጭ ብቻ ነው ፤ እሱም ቢሆን ጥለቱ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መሆን መቻል አለበት ፤ አሁን ያሰርነውን ክር በመበጠስ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ክር ማሰር አለብን” የሚል ነው፡፡

በየአጋጣሚው ቤተክህነቱንና ቤተ መንግሥትን በመንቀፍ አሁን የሚታዩትን ችግሮች መሰረት አድርጎ ህዝቡ መጥቷል የተባለው ኤልያስን መከተል እንጂ ወደ ቤተክርስቲያን መሄዱ ጥቅም እንደሌለው እየተነገረ ነው፡፡

ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ውስጥ አንዲት ሴት ”መሲህን ልወልድ ነው” እያለች ሰዎችን ታስከትል ነበር፡፡ ይህቺ ሴት አስገራሚ በሆነ ሁኔታ በየገዳማቱ እየዞረች ካህናቱን ሁሉ ለማንበርከክ ተንቀሳቅሳለች፡፡ ለዚህም ወንጪ ቂርቆስ ላይ ያደረገችውን ማስታወስ በቂ ነው፡፡

የዚህች ሴት አካሔድ አነጋጋሪ የሚሆነው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በደሙ በመሠረታት፣ ሥጋውና ደሙም በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአይሁድ ወገኖች አስተምህሮ የሚመስል ሰበካ ይዛ መገኘቷ ነው፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክርስቶስ ገና እንደሚወለድ ያለ አስተምህሮ ሲነገር መስማት ማሳፈሩ ብቻ ሳይሆን በጊዜው ቤተ ክርስቲያን ትንሹም ትልቁም በወደደ ጊዜ የሚሻውን የሚፈጽምባት፣ የሚናገርባት ተቋም አይደለችም፡፡

ሴቲቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊታሰብ የማይችል በማሰቧ፣ ሊነገር የማይችል በመናገሯ በአብዛኛው የክርስቲያን ወገን ይታሰብ የነበረው የአንዲት ሴት ከንቱ ቅዠት ተደርጎ ነው፡፡ ከዚህ አልፎ ተመሳሳይ ዝንባሌዎች ያቆጠቁጣሉ ብሎ ያሰበ የለም፡፡

እነሆ ዛሬ ደግሞ ሌላ የአይሁዳዊነት ዝንባሌ ያለው አስተምህሮ በኤልያስ ስም በተደራጀ ቡድን አማካኝነት ማብቀል ጀምሮ እስከ አራት መቶ ተከታዮች እንዳሉት እየተነገረ ነው፡፡ አስገራሚው ይኸው አስተምህሮ ተለጥፎ የመጣው በዚህችው በመከራ ውስጥ በምትጓዝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ነው፡፡ ስሙንም በተዋሕዶነት ሰይሞ ሲጓዝ አላፈረም፡፡ መከፋፈል፣ ማሰለፍ የሚፈልገውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ነው፡፡ አስተምህሮው የተደበላለቀና ወጥ ያልሆነ ዘርፍ፣ መልክ፣ መነሻም መድረሻም የሌለው ክርስትና ይሁን አይሁዳዊነት ፖለቲካ ይሁን ሃይማኖት ጥንቆላ ይሁን እብደት ያለየለት እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይህ ቡድን አውቆም ሆነ ሳያውቅ ጥለን ወደመጣነው እርሾ ወደ አይሁዳዊነት ያዘነበለ አስተምህሮ ይዞ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል አንዱን አንሥቶ ሌላውን ለመጣል የሚሞክር አፍራሽ አካሔድም የያዘ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ባለፉት ዘመናት ከተወረወሩት ፍላጻዎች ተከትሎ የመጣ በአቅሙ ፍላጻ ሆኖ ለማደግ የሚተጋ ነው፡፡

በዚህች ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ዘመናት በብሕትውና ስም በአጥማቂነት ስም ብዙዎች የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን ለማስተጋባት ምእመናንን ግራ በማጋባት ተሰልፈው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሁሉም እየታዩ መጥፋታቸው እንዳለ ሆኖ ያጠፉት፣ ተስፋ ያስቆረጡት ያሰናከሉት መንጋ እንዳለም አይረሳም፡፡ በአብዛኛው ግን አሁን አሁን እንደሚታዩት መሠረት የለሽ ከክርስትና ሃይማኖት እሳቤ ፍጹም የወጣ ጽንፍ ይዘው ግን ታይተዋል ማለት አይቻልም፡፡ አብዛኛውም ምእመናን እርካታ ሊሰጣቸው ያልቻለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በመንቀፍ ስለሚመሠረቱ ተከታዮችን በቀላሉ ለማግኘት አስችሏቸው ነበር፡፡ በአብዛኛው የባሕታውያኑና የአጥማቂዎቹ ትኩረት አስተዳደሩን፣ አገልጋይ ማኅበራትን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን፣ ግለሰቦችን መንቀፍ ላይ የሚያተኩርና ከዚያ አለፍ ሲል የራሳቸውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለመደንገግ ሲጥሩ መታየታቸው ነው፡፡

እነዚህ የአሁኖቹ የአይሁዳዊነት ዝንባሌ ያላቸው እንቅስቃሴዎች ግን የተናቁ ቢመስሉም የአካሔድ ሚዛኑ ፍጹም ፀረ ክርስትና ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚሠሩ እንደሆነ ይናገሩ እንጂ የሚያሳስባቸው የስብከተ ወንጌል ሥርጭት አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት አቅም ስለማደግ አለማደጉ አይደለም፡፡ አስተዳደራዊ መሻሻል ስለማምጣት አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ ለውስጥ ለማዳከምና ለመከ ፋፈል ስለሚሠራው የተሐድሶ ቡድን አይደለም፡፡ ወይም በሀገሪቱ እየተስፋፋ ስላለው ዓለማዊነት አይደለም፡፡ በሀገሪቱ እየተስፋፋ እንደሆነ ስለሚነገርለት ግብረሰዶምና እጅግ የከፋ የኃጢአት ሥራ አይደለም፡፡ ስለ ሰላም ስለ ዕርቅ አይደለም፡፡ እነዚህ ወገኖች የሚያሳስቧቸው ነገሮች ሲመረመሩ የጸሐፍት ፈሪሳውያን እርሾ ከቤተ ክርስቲያን የመወገዱ ጉዳይ ያንገበገባቸውና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ሊያሳድጉ ሊያሰፉ ሊያጠናክሩ የሚችሉ ፍንጮች መታየታቸው ያበሳጫቸው መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡ እነዚህ ወገኖች ነግቶ በመሸ ቁጥር የሚናገሯችው የተደበላለቁ ያልሰከኑ ገና እየተደራጁ ያሉ ዝብርቅርቅ ሐሳቦች ያሏቸው ስለሆኑ በሚያነሡት ነጥብ ላይ መልስ በመስጠት ጊዜን ማጥፋት ለጊዜው አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ነገር ግን ይህን የሚወዛወዝ አስተምህሯቸውን ዝንባሌ መጠቆም አግባብ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ መባል የለባትም

እነዚህ ወገኖች ክርስትና ማለት ሀበሾች ብቻ ተጠምቀው ይዘውት የሚገኙ ሃይማኖት አድርገው የማሰብ ያህል አጥብበው ያያሉ፡፡ የአሐቲ ቤተ ክርስቲያን እሳቤ የሌላቸውና ለሁሉም ወገን የተሰጠች መሆኗን በመዘንጋት “ተዋሕዶ ብቻ ነን” ይላሉ፡፡ ኦርቶዶክስ መባልን ሲኮንኑ ከኒቅያ ጉባኤ ጀምሮ ያሉ ሊቃው ንትን ከዚያም ለብዙ ምዕተ ዓመታት የነበሩ ሊቃውንትና ምእመናንን አኀት አብያተ ክርስቲያናትን ወዘተ እየኮነኑ መሆኑን እንኳ አላስተዋሉም፡፡ ሃይማኖታችን አንዲት/one/ ኩላዊት/catholic/ ሐዋርያዊት /apostolic/ ቅድስት /holy/ መሆኗን አያውቁም ወይም ብለን እንደምናስተምር ስናስተምርም እንደኖርን ረስተዋል፡፡

የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ተቀብ ለው የቅዱሳን ሐዋርያትን ትምህርትና ትውፊት የተቀበሉ፣ ያቆዩ፣ ያጸኑ፣ በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ፣ በኤፌሶን የተደረጉ መንፈ ሳዊ ጉባኤያትን የተቀበሉ፣ ሐዋርያዊ ውርስ ያላቸው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረውን ምስጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ሥጋዌ፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ቁርባንና ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ትምህርትን እነርሱም የሚያስተምሩ አኅት አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ ኦርቶዶክስ እንደሚባሉ ማወቅ መረዳት ያለመቻልና ክርስትናን ከብሔርተኛ ስሜት /nationalism/ አስተሳሰብ ጋር አቆራኝተው ማየታቸው ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች ይህን ለማለት እንደመነሻ የሚያሳብቡት “የቅባት እምነት ተከታይ የሆኑ ካህናት በጎጃም አሉ፤ ዘጠኝ መለኮት የሚሉ በዋልድባ አሉ የሚልና ተሸፍነው የሚኖሩት በኦርቶዶክስ ስም ነውና ኦርቶዶክስ የሚለውን አንቀበልም” የሚል ነው፡፡ እነዚህን አለመቀበላቸው መልካም ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲታገሏቸው እንደኖሩ አሁንም ያንንኑ መንገድ ተከትለው ቢታገሉ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ያ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትጠራበት ስም በራሱ ከእነዚህ የኑፋቄ ወገኖች የተለየች ሆና “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን” ተብላ እንደሆነ እያወቁ “ተዋሕዶ” መባል አለብን የሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ያነሣሉ፡፡ “ተዋሕዶ” የሆነውን እኛን መልሰው “ተዋሕዶ እንሁን” ሲሉን ነገር እንዳለው ሁሉም ወገን መገንዘብ ይገባዋል፡፡ “ተዋሕዶ ነን” ብለን በይፋ የምንጠራበት ስም ካለን፣ ቅባትና ዘጠኝ መለኮትን የሚያነሣ መጠሪያ ከሌለን፣ በእምነትም ተዋሕዶ እምነትን እንደ ምንከተል ከታወቀ የሚፈለገው ምንድነው፡፡ ከዚህ ከሚያነሡት ክርክር ጋር ኦርቶዶክስ መባልንስ የሚያስጥል ምን መነሻ አለ፡፡

ኦርቶዶክሳዊነት እጅግ በስፋት ተተንትኖ መታየት የሚችል ለእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የተገባ ስም መሆኑን ማሳየት ቢቻልም በዚህ ጽሑፍ ማሳወቅ የተፈለገው ግን የእነዚህ ወገኖች የአለማወቅ ደረጃ በዚህ ላይ ያለ መሆኑን ነው፡፡ ኦርቶዶክስ መባልን ደባ ነው፣ ሸክም ነው ወዘተ እያሉ መለፈፋቸው ብዙ እርምጃ የማያስኬድ መሆኑን አውቀው ሊታረሙበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ቃል መለካውያን ተጠቅመውበታል ይላሉ፡፡ እነርሱ በመጠቀማቸውም እኛ እንድንጥለው ይመክሩናል፡፡ እነርሱ ክርስቲያን ተብለው እንደሚጠሩ ቤተክርስቲያን ብለው እንደሚጠሩም መገንዘብ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ቆይተው ደግሞ እነርሱ ክርስቲያን ተብለው ተጠርተዋልና እኛ ክርስቲያን መባልን እንድንተው፣ ቤተ ክርስቲያን መባልን እንድናስቀር ሊመክሩን ይነሣሉ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ሐሳባቸው የአይሁዳዊነት እርሾ አለው የምንለው፡፡

ስም አጠራራችን “አይሁዳዊ” የሚል ነው

እነዚህ ወገኖች ኦርቶዶክሳዊ መባልን ኮንነው ሲያበቁ ሊያሻግሩን የሚጥሩት አይሁዳዊ ወደሚለው መጠሪያ ነው፡፡ ለማስተማር ብለው በበተኑት ወረቀት ላይ ”አይሁዳዊ የሚለውን የጌታን የእመቤታችንን የንጹሐን ኢትዮጵያውያንን የከበረ ስም አጠራር ለዐመፀኛ አሕዛብ አሳልፎ መስጠት ፈጽሞ አይገባም ነበር” ይላሉ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ከሚለው የክርስቲያኖች ስም ሲነጥሉን ያልራሩ ሰዎች በስያሜ ከአይሁድ ጋር ተቀራረቡ በማለት ጭካኔያቸው ሲያይል ያሳዩናል፡፡ ኦርቶዶክሳዊነት የክርስትና ስም ነው፡፡ አይሁዳዊ፣ ግሪክ፣ ኢትዮጵያዊ ወዘተ የሚለው ግን የወገን፣ የብሔር ስም መሆኑን እንኳን አላስተዋሉም፡፡ ለዚህ ነው ዝንባሌው ወደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን እርሾ ነው የምንለው፡፡

ሰንበተ አይሁድ እንጂ ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ የሚባል የለም

እነዚህ ወገኖች የተረፈ አይሁዳውያን ትምህርት አላቸው ስንል ለዝንባሌያቸው ሌላው መነሻ ስለ ሰንበተ ክርስቲያን መስማት አለመፈለጋቸውና ሰንበተ አይሁድ እንድትነግሥ ማነሣሣታቸው ነው፡፡ “ብዙዎች በየዋሕነት ጌታ ያዘዘው ሐዋርያት የደነገጉት ነው ብለው ዕለተ እሑድን ሰንበት ነች እያሉ እንደሚያስቡ ይታወቃል፤ ነገር ግን እሑድ መቼ እነማን ለምን ዓላማ ሰንበት ተብላ ልትሰየም ቻለች ብለን ስንመረምር የሰይጣንን ተንኮል እናስተውላለን…” እያሉ እሑድ ሰንበት መባሏን የሰይጣን ሥራ ያደርጉታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበተ አይሁድን ቀዳሚት ሰንበት ብላ እንደ ክርስትናው ሕግና ሥርዓት ተገቢውን ክብር እንደምትሰጥ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ እስከ አሁን የክርስቲያን ወገን ሁሉ ሲቀድሳት የነበረችን ሰንበተ ክርስቲያንን ግን ገናና፣ ክብርት፣ ልዕልት ሆና የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ ሲዘከርባት የኖረችና የምትኖር ናት፡፡ እነዚህ ወገኖች ግን የተረፈ አይሁድን ሐሳብ ዳግም ለማራገብ በመነሣት መከራከሪያ እንድትሆን ጥረት ማድረጋቸው ወደ ኋላ የሚስባቸውን አሮጌ እርሾ ያሳያል፡፡

የዳዊት ኮከብ መሠረቱ የሆነ ትእምርተ መስቀል መለያችን ይሁን

የዳዊት ኮከብ የአይሁድ ምኩራቦች መለያ ምልክት ነው፡፡ የዳዊት ኮከብ ሰሎሞናዊ እንደሆኑ በሚነገርላቸው በኢትዮጵያ ነገሥታት ዘንድ የቤተ መንግሥቱ ትእምርት ሆኖ እንደኖረ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መንግሥትና በዩኒቨርሲቲዎቻችን አጥሮች በሚታዩት ምልክቶች እንረዳለን፡፡ ይሁን እንጂ ክርስትናውን አሽቀንጥሮ ለመጣል መሠረቱን ለመናድ ያዋሉት ሳይሆን የቤተ መንግሥቱ ምልክት ሆኖ የመንግሥቱን የትመጣ ለማጠየቅ የተገለገሉበት ትእምርት ነው፤ ከዚህ ባለፈ ግን እኛ ሁላችን ከዳንበት ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀሉ ትእምርት ጋር ቁርኝት የምንፈጥርበት አይደለም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወገኖች አሁንም ክርስትናችንን ከአይሁዳዊነት ጋር የመቀላቀል አሳብ ወይም ሌላ በሃይማኖት ስም ሊተክሉ የሚፈልጉት የፖለቲካ ርእዮት አለ ማለት ነው፡፡ እኛ ሃይማኖታችን ትእምርት የሚያደርገው የዳዊትን ኮከብ ሳይሆን ዳዊትን ጨምሮ ሰዎች ሁሉ የዳኑበትን የክርስቶስን መስቀል መሆኑን በመረዳት ሊታረሙ ይገባል፡፡

በሌላም በኩል “ቶ” እንደ ብቸኛ የመስቀል ምልክት አድርጎ ለመጠቀምና በዳዊት ኮከብ ምልክት ላይ ተቀጽሎ እንዲቀርብ ይሰብካሉ፡፡ በአልባሳቶቻቸው አትመው ወይም ቀርጸው ያሳያሉ፡፡ የ “ቶ” ቅርጽ በተለያዩ ዘመናት በተለያዩ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች እንደሚታየው በሆነ ዘመንና ሁኔታ ወስጥ የመስቀል ምልክት ሆኖ አገልግሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያ በመለስ ግን የሆነ የቤተ ክርስቲያናችን መለያ እንዲሆን አድርጎ የመቀሰቀስ ሥልጣን ግን ለዚህ ቡድን የሰጠው የለም፡፡ ካልሆነ ግን የሚኖረው ፋይዳ በእነ ዴርቶጋዳ፣ ራማቶሐራ፣ ዣንቶዣራ ከሚነገረን ልቦለዳዊ የርእዮተ ዓለም መግባቢያነት ያለፈ አይሆንም፡፡ በዚያም ልቦለዳዊ ታሪክ እንኳ ቢሆን ይህን የምስጢር መልእክት መቀባበያ አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረው ገጸ ባህርይ በቤተ ክርስቲያን ስም የሚኖር አባ ፊንሐንስ የተባለ የይሁዲ እምነት ተከታይ ነበር፡፡ ታሪኩን ስናነብ የሌላዋን ገጸ ባሕርይ የልጁን የሲጳራን ክርስቲያናዊ ሕይወት ለማስጣል የአንገቷን መስቀል ለመበጠስ ሲታገል የነበረ አስመሳይ መነኩሴ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ወስጥ ታዲያ “ቶ” የዚህ አስመሳይ መጠቀሚያ ነበር፡፡ ታዲያ እነዚህ በእውኑ ዓለም ያሉ ወገኖች “ቶ”ን ካልተጠቀመን ሞተን እንገኛለን ሲሉ በክርስትና ስም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ የራሳቸውን ተልእኮ ለማሳካት የሚሮጡ ተረፈ አይሁዳውያን ናቸው አያስብል ይሆን!

ዮዲት ጉዲት ስሟ ታሪኳ ተዛብቷል

“ደቂቀ ኤልያስ” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት እነዚህ ወገኖች አይሁዳዊ እንደሆነች ታሪክ የጻፈላትን ዮዲት ወይም ጉዲት ወይም እሳቶ የሠራችውን ሥራ እንደበጎ ተቆጥሮ ታሪክ እንዲገለበጥ ይሠራሉ፡፡ ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታጠፋ ክርስቲያኖችን ስታርድ መኖሯን ታሪክ እየመሰከረ ነቢዩ ኤልያስ ነገረን በሚል ማስረጃ እውነታው ተገልብጦ ጠንቋዮችን ዐመፀኛ ካህናትን ወዘተ እንዳጠፋች እንዲታሰብ ሊያግባቡን ይጥራሉ፡፡ ሰልፋቸው የአይሁድን ገጽታ የመገንባት ከተቻለም ከይሁዲነት የሃይማኖት እሳቤዎች እየሸራረፉ ለማጉረስ በመሆኑ እንቅስቃሴው የተረፈ አይሁድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መዋቅር በአውሬው መንፈስ የሚመራ ነው

እነዚህ ወገኖች ያዘሉት ጭፍንነት የተሞላበት አካሔድ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደሚጠሏት ያሳብቃል፡፡ በታሪክ ረገድ ከንግሥተ ሳባ እስከ ደቂቀ እስጢፋ፣ በአስተዳደር ዘማዊና መናፍቅ ከሚሏቸው ጳጳሳት እስከ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት ከኦርቶዶክስ አይደለንም እስከ ሰንበተ ክርስቲያንን መሻር ድረስ የተመሰቃቀለ መሠረት የለሽ ቅዠትን ይዘው ተከታይ ለማፍራት መንቀሳቀሳቸው፣ ሊያውም በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ መሆኑ ለሃይማኖት ቤተሰቡ ያላቸውን ንቀትና የድፍረት አሠራራቸውን ያስረዳል፡፡ ስለዚህ ሲቀሰቅሱም ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደፈረሰች አደርገው ነው፡፡ ለዚህም “የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተባለው መዋቅር ማንንም ሊደግፍና ሊጠልል ቀርቶ እራሱን እንኳን ማቆም ያልቻለ በገዛ ራሱ የፈረሰ የእንቧይ ካብ መሆኑን እንረዳለን” ይሉናል፡፡ ተስፋ ማስቆረጥ ይፈልጋሉ፤ መንጋውን መበተን ይሻሉ፤ ለማን ሊሰጡት እንደሆነ አይታወቅም፤ ግን ምእመኑ እንዲሸሽ ይመክራሉ፡፡ የሆነውም ያልሆነውም በካህናትና መነኮሳት ተሠሩ የሚሏቸውን የሥነ ምግባር ችግሮች መቀስቀሻ ያደርጉታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን የሃይማኖታዊ አስተምህሮ ችግር ያህል አድርገው ይሰብካሉ፡፡ በእነርሱ እሳቤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዲያቆናት ቀሳውስት ጳጳሳትም ሁሉ የቅባት፣ የዘጠኝ መለኮት ወልድ ፍጡር የሚሉ አሪዮሳውያን ወዘተ ኑፋቄ ተከታዮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ መስቀል መሳለም፣ በእነርሱ እጅ መቁ ረብ የማይገባ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክህነቱ መንጋውን እንዲሰበስብ አይፈልጉም፡፡

ቤተ ክህነቱ መንጋውን መሰብሰብ እንዳይችል ሆነ ማለት የክህነትን ሥልጣን እንደሌሎች መናፍቃን ካድን ማለት ነው፡፡ እንደውም በኢትዮጵያዊው መልከጼዴቅ ሥርዓተ ክህነት የሆነ አዲስ ሊቀካህን ይኖርና ክህነት እንደ አዲስ ኤልያስ ለመረጣቸው ይሰጣል፤ ይላሉ፡፡ ልብ በሉ “ሊቀ ካህን” የሚለው እሳቤ ዳግም ወደ አይሁድ ዓለም የሚስብ ነው፡፡ ለአንዳንዶችም መስቀል ከሰማይ እንደተላከ ሆኖ ሲሰጣቸው የታየበት መድረክም አለ፡፡ ስለዚህ በእነሱ እሳቤ ሐዋርያዊ ውርስ የሚባል ነገር በክህነት አይታሰብም፡፡ ስለዚህ ክህነቱ ተክዷል፡፡ ይህንን ካላመንን ደግሞ የሚያጠምቀን የሚያቆርበን የሚናዝዘን የሚያመነኩሰን የሚያጋባን የሚፈውሰን በቅብዐ ሜሮን ለእግዚአብሔር የሚለየን ማን ይሆናል፡፡ እንዳትቆርቡ ብለው ሲቀሰቅሱ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እየለዩን ነው፡፡ ስለዚህ እርሱን እንዳንቀበል የሚሠ ሩትስ ለምንድነው፡፡ ካህን ከግብጽ ይመጣል እንዳይሉን ግብፆችም ለእነዚህ ወገኖች መሰሪና ተንኮለኞች ናቸው፡፡

“ካህናቱ የበኣል የጣዖት ካህናት ሆነዋልና አትቀበሏቸው” በሚለው በእነዚህ ሰዎች ልፈፋ የሚከሰሰው ሁሉም ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችው ከእነማን ጋር ነው፡፡ ማኅበራቱ፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶቹ ሁሉ በዚህ ቡድን እሳቤ የአውሬው ወገኖች ናቸውና፡፡ ታዲያ ያለክህነት እና ካህናት ያለ አገልጋይ መምህራን ሰባክያነ ወንጌል የምትኖር የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት፡፡ ስለዚህ ያላችሁት ያለሰብሳቢ ነው እያሉን ነው፡፡ ታዲያ የሚፈልጉት እንድንበተን ብቻ ከሆነ “ደቀ መዛሙርቱ ሰርቀውታል እንጂ አልተነሣም” እያሉ በክርስቶስ አምነው የነበሩትን ክርስቲያኖች ተስፋ አስቆርጠው ሊበትኑ ከተነሡት አይሁድ አሠራር በምን ይለያል፡፡ መንገዳቸው ቅስቀሳቸው ሁሉ የማፍረስና የጭካኔ ነውና፡፡

ከመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት እንለይ

ለእነዚህ ወገኖች በክርስትና ስም ካሉ ከሁሉም ወገኖች ጋር መጎራበታችንን አይወዱም፡፡ ስለዚህ ከሃምሳ ዓመታት ያላነሰ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ለማድረግ አስተርጉሞ አሳትሞ በማከፋፈል አገልግሎት እየሰጠ ያለውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም በዋናነት ተሳትፎ ከምታደርግበት ማኅበር እንድንርቅ ይመክራል፡፡ ሰዎችን ያነሣሣል፡፡ እነርሱን ጨምሮ ብዙዎች በሀገራችን በአማርኛና በሌሎችም ቋንቋዎች ተተርጉመው የቀረቡ መጻሕፍት በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል ድጋፍ እየሰጠ ያለውን ማኅበር የጥፋት መልእክተኛ ማድረግ ሚዛናዊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ስልታዊ በሆነ መልኩ የማዳከም ፍላጎት ነው፡፡

በመሠረቱ እነዚህ ወገኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርን ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስን የእምነት መሠረት ማድረግን የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ በተንኮልና በአውሬው አሠራር ተለውጧል ብለው ያስባሉ፡፡ የዚህ ምክንያት ግን ግልጽ ነው እነርሱ ለሚነዟቸው ልፍለፋዎች ሁሉ ደጋፊ የሚያደርጉት መጽሐፋዊ መነሻ አለመኖሩ ነው፡፡ ስለዚህ ሲመቻቸው “በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገረው የዓለም የፍጻሜ ዘመን ተቃርቧል” ይላሉ፤ ሳያስፈልጋቸው ደግሞ “መጽሐፍ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርን አትመኑ” እያሉ ይቀሰቅሳሉ፡፡ ለእነርሱ ታማኙ የእምነታቸው መጽሐፍ “የኤልያስ ዐዋጅ ነው” የሚሉት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሠራውን ደባ እያቀነባበረ ያለው የእነርሱ “አባትዬ” ተራ ድርሰት ነው፡፡ እርሱ ለዘመናት ተሻግሮ ከመጣው ቃለ እግዚአብሔር በላይ ታማኝ ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ያስጥላል፡፡

ከዚህም ተሻግሮ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አባል መሆን ገንዘብ መውደድ እንደሆነ አድርጎ አጥብቦ ለማሳሰብ ይሠራሉ፡፡ ከኅብረቱ ወጥቶ እነርሱን መሳብ እንጂ መተባበር ሃይማኖት ያጠፋል ብለው ያስባሉ፡፡ ሃይማኖትን ማስፋፋት ከማይፈቅዱ ወገኖች ጋር ቤተ ክርስቲያን የተባበረች አድርጎ በማሳሰብ የክርስትና ሽታ ካላቸው ኦርቶዶክስ የሚባሉ አኀት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ቤተ ክርስቲያን አጠገባቸው እንድትደርስ አይሹም፡፡ ክርስትናን መሸሹ እንዳለ ሆኖ እንድንጠነቀቅ ከማሳሰብ የሚነሣ ሳይሆን አጠገባቸው እንዳንደርስ በፍርሃትና በጥርጣሬ ተሞልተን፣ ራሳችንን ብቻ አጽድቀን እንድንነሣ ስለሚገፉ አካሔዱ አይሁዳዊ እርሾ የተቆራኘው ነው፡፡ ሌላውን የኃጢአት ጎተራ አድርጎ ከመፍረድ ያልፍና አይሁድ ጌታን በሚከሱበት “የአብሮ በላ አብሮ ጠጣ” ክስ ቤተ ክርስቲያንንም ሊከሱ ይነሣሉ፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤቶች አያስፈልጉም

እነዚህ ወገኖች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለማዳከም የሚሠሩ ሤረኞች መሆናቸውን በቀላሉ የምንረዳው በዚህ ዘመን ያሉ የቤተ ክርስቲያንን የአገልግሎት ምሰሶዎች ለመነቅነቅ መቋመጣቸው ነው፡፡ ለዚህ ማሳያው ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማመስገን ፈንታ ሲወቅሷቸው፣ በማበረታታት ፈንታ ሲሰደቧቸው መታየታቸው ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች በረጩት ጽሑፍ ላይ ያስነበቡንን ስናይ “ሰንበት ትምህርት ቤት አውሬው የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ለማጥመድ የመሠረተው ረቂቅ ስውር ወጥመድ ነው” ይላሉ፡፡ ሴቶችን ከሊቃውንት በላይ አድርጎ ወረብ ያስወርባል፤ የአውሮፓ ባህል ነው፣ አስነዋሪ ሥራዎች ይሠሩበታል…ወዘተ እያሉ ተራና ጽንፈኛ ቅስቀሳ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ክርስትናን ሃይማኖቴ ነው ብሎ ከሚከተል ወገን የሚሰነዘር አይደለም፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤቶች ምእመናንን ከመናፍቃን ለመጠበቅ የሠሩትን፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቤተ ክርስቲያንን እንዲያውቋት፣ የፈጸሙትን አገልግሎትና ቤተ ክርስቲያንም የአገልግሎት ውጤቱን አይታ አንድ መምሪያ ያቋቋመችለት መሆኑን እያወቁ፤ ካላቸው የተረፈ አይሁዳዊነት ስውር ተልእኮ አንጻር ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሠሩት አገልግሎት ተቆጥተው የሚያስተጋቡት ስም ማጥፋት ነው፡፡ አካሔዳቸው ፀረ ስብከተ ወንጌል ነው፤ ስለዚህ ፀረ ክርስትና ነው፤ ስለዚህም የአይሁድ ቅናትን ያዘለ ነው፡፡

ኤልያስ መጥቷል

ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መምጣቱንም ሊያበስሩን ይሞክራሉ፡፡ አስገራሚው ነገር ከላይ የተነሡ ሁሉንም ጉዳዮች የገለጠው ያወጀው የፈረጀው የለወጠው የሻረው ያጸደቀው የኮነነው ነቢዩ ኤልያስ እንደሆነ በየምዕራፉ ይነግሩናል፡፡

ነቢዩ ኤልያስና ሄኖክ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት በምድር ላይ እንደሰው ተመላልሰው በኋላ ግን ሞትን ሳይቀምሱ በማረግና በመሰወር በብሔረ ሕያዋን እስከ አሁን እንደሚኖሩ ይታመናል፡፡ ሰው ሆኖ ተፈጥሮ በለበሱት ሥጋ መሞት ለማንም አይቀርምና ወደዚህ ዓለም መጥተው በሰማዕትነት እንደሚያርፉ የቤተ ክርስቲያናችን ነገረ ሃይማኖት ያትታል፡፡ ከዚያም በመነሣት ስለኤልያስ መምጣት የተነገሩባቸው ሁለት የትንቢት ቃሎች በመጽሐፍ ቅዱሳችን አሉ፡፡ የመጀመሪያው ከመሲሑ ከክርስቶስ መምጣት አስቀድሞ እንደሚመጣ የተነገረው ምጽአት ነው፡፡ ይህም በነቢዩ ሚልክያስ “እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ፡፡ መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል፡፡” ተብሎ የተነገረው ነው /ሚል. 4፥5/፡፡

ሌላው የትንቢት ቃል ደግሞ በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ላይ የተነገረው የሚከተለው የትንቢት ቃል የተተረጎመበት ክፍል ነው፡፡ “ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺሕ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ፡፡ እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፡፡ ማንምም ሊጎዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፡፡ ጠላቶቻ ቸውንም ይበላል፡፡ ማንም ሊጎዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል፡፡ እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳ ይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውኃዎችንም ወደደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሰፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው፡፡ ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል፤ ያሸንፋቸውማል፡፡ ይገድላቸውማል፡፡ በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፡፡ እርሷም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብፅ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት፡፡ ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኩል በድናቸውን ይመለከታሉ፡፡ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም እነዚህ ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሣቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፡፡ በደስታም ይኖራሉ እርስ በእርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ፤ ከሦስት ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፡፡ ታላቅም ፍርሐት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው፤ በሰማይም ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፡፡ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቷቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ፡፡…” /ራእ. 11፥3-03/ በዚህ ቃለ እግዚአብሔር ውስጥ “ሁለቱ ምስክሮቼ”፣ “ሁለቱ ወይራዎች”፣ “ሁለቱ መቅረዞች”፣ “ሁለት ነቢያት” እያለ የሚጠራቸው በዚህ ዓለም ሞትን ያልቀመሱ ሁለቱ የእግዚአብሔር ወዳጆች ሄኖክና ኤልያስ እንደሆኑ ሊቃውንቱ በትርጓሜ ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን የሚገለጹት ከጥልቁ የሚወጣውን አውሬ ሊዋጉ ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ሊዋጉ አይደለም፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ትንቢቶች ትንቢት እንደመሆናቸው መጠን የተፈጸሙበትን ጊዜና ሁኔታ ሊረዱ የሚችሉት ቅዱሳን ናቸው፡፡ “በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም” /2ጴጥ.1፥21/ እንደተባለ በሥጋና ደም ሰዎች የሚረዷቸው አይደሉም፡፡ ይህ አካሔድ አይሁድን ከሃይማኖት መንገድ ያስወጣቸው ነው፡፡

አይሁድ በኤልያስ መምጣት ጉዳይም ስተዋልና፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ለጌታችን “እንግዲህ ጻፎች ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለምን ይላሉ ብለው ጠየቁት” የነቢያት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤ ነገር ግን እላችኋለሁ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም” አላቸው፡፡ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደነገራቸው አስተዋሉ፡፡/ማቴ.17፥11/ አይሁድ ግን በሥጋና ደም ለትንቢቱ ትርጓሜ አበጅተው ይጠባበቁ ነበር፡፡ በግብሩ፣ በመንፈሱ፣ በአኗኗሩ ኤልያስን መስሎ ንስሐ ግቡ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸው ድምፅ ኤልያስ የተባለው ዮሐንስ መሆኑን አላስተዋሉምና እርሱንም መሲሁንም ሳይቀበሉ ቀሩ፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ ያለው አስተሳሰብ የአይሁድ በመሆኑ የአሁኖቹ “ኤልያሳውያን” አካሔድ ተረፈ አይሁዳዊነት ነው የምንለው፡፡

በአንድ በኩል ይህንን የነቢዩ ሚልክያስን ቃል ይዘው እየሞገቱን ከሆነ ዮሐንስ መጥምቅን በኤልያስ መንፈስ መምጣቱን አለመቀበልና ብሎም መሲሁን ኢየሱስ ክርስቶስንም እንዳለመቀበል ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ ከነገወዲያ ባለፉት ዓመታት በየአደባባዩ ስታውከን እንደነበረችው ሴት መሲሁ ተወልዷል ወይም ሊወለድ ነው ሊሉን ተዘጋጅተዋል ማለት ነው፡፡ ይህ በግልፅ የመጣ የይሁዲ እምነት አራማጅነት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በዮሐንስ ራእይ የተቀመጠውን የትንቢት ቃል መነሻ አድርገው እየሞገቱን ከሆነ ደግሞ አስተሳሰቡ አሁንም ትንቢትን ለገዛ ራስ መተርጎም እንዳይሆን ልንጠነቀቅበት የሚገባ ነው፡፡ ለገዛ ራስ መተርጎም የጸሐፍት ፈሪሳውያን እርሾ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች አካሔድ ሃይማኖትን ተራ ጨዋታ ወደ ማድረግ የሚወስድ ነው፡፡ ሃይማኖትን በንቀት እንዲታይ የማራከስ አካሔድ ነው፡፡ ኤልያስ መጥቷልና አጅቡት ተቀበሉት እያሉ በየመንደሩ መቀስቀስ እገሌን ይጥላል እገሌን ያፈርሳል እያሉ በማውራት ለምእመናንን ምልክት ፈላጊነትን ማለማመድ ነው፡፡ ሰዎች ሃይማኖት ከምግባር ይዘው እንዲገኙ ከማስተማር ይልቅ ኤልያስን ፈልጉት እያሉ ማባዘን ተገቢ አይሆንም፡፡ ይህ “የአመንዝራ ትውልድ” ጠባይ ነው፡፡ ምልክትን የሚፈልግ ማኅበረሰብ እምነትን ይዞ ለመገኘት አይቻለውም፡፡

እነዚህ ወገኖች አሳባቸው ሥጋዊ ስለሆነ የትንቢቱን መፈጸም ሊነግሩን የሚቻላቸው አይደሉም ሊባል የሚችልበት ምክንያት አለ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ኤልያስ የሚመጣው የአትዮጵያን ቤተክህነት አፍርሶ ሊያድስ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ቤተ መንግሥት ሊያስተካክል ነው፡፡ ባንዲራውን ከአረንጓዴ ቢጫ ቀይም አልፎ በሰባቱ የቀስተ ደመና ረቂቅ ቀለማት /spectrum/ አስውቦ ሊተክል ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ እየከለሰ ሊያስጠናን ነው፡፡ ስብከተ ወንጌል የሚያካሒዱ ሰንበት ትምህርት ቤቶችና ማኅበራትን ሊያፈርስ ነው፡፡ ሰንበትን ሊሽር ወይም ሊተካ ነው፡፡ ነግሦ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ሊያመጣ ነው፡፡ ይህ ፍጹም ብሔርተኛና ፍጹም ሥጋዊ የሆኑ ሐሳቦች ናቸው፡፡ ካልሆነም የጥንቆላና የመናፍስት ሥራ ነው፡፡ ካልሆነም ለሥጋዊ ጥቅም የሚደረግ ሩጫ ነው፡፡ ካልሆነም ብዙዎች እንደሞከሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመፈታተን የመጣ ሌላ አዲስ የዘመቻ ጽንፍ ነው፡፡ በስሕተትም ቢሆን ግን ስሕተቱ ትንቢትን ለገዛ ራስ የመተርጎም ዝንባሌ ነውና ተረፈ አይሁዳዊነት ነው፡፡

ማጠቃለያ

እነዚህ ወገኖች ያነሧቸው የማሳሰቻ ቅስቀሳዎች በራሳቸው የትም የማያደርሱ የተሰነካከሉ ሐሳቦች ቢሆኑም ፀጉሩን የገመደ፣ ቆዳ የለበሰ፣ ባዶ እግሩን የሚታይ “ባሕታዊ” አንድ መዓዝን ላይ ሲጮኽ አይተው ቆመው ለሚሰሙ የዋሐን ግን ጥርጥርና ማደናገሪያ ማሳቻ መሆኑ አይቀርም፡፡ ቡድኑ ከዚህ አልፎ በሕዝብ ዘንድ ይታወቃሉ የሚላቸውን አንዳንድ የዋሕ አርቲስቶች ቀስቃሽ ለማድረግ እንደ ስልት መያዙ ደግሞ የምር ታስቦበት ለመዝመት እየተሠራ መሆኑን ያሳያል፡፡

እነዚህ ወገኖች በየዓለሙ መዓዝን ዓለም ሊጠፋ ነው ብለው እንደሚቀሰቅሱት ምጽአት ናፋቂዎች ናቸው ብሎ ደፍሮ ለማውራትም የማይመች ነው፡፡ የሚያወሩልን ስለፍፃሜ ዓለምም አይደለም፤ ኢትዮጵያ በኤልያስ ገና ወደ ልዕልና እንደ ምትመጣ፣ በረከት መልካም ዘመን እንደሚቀርብ ሊነግሩን ነው፡፡ ስለዚህ ስለነገረ ምጽአት የሚነግሩን ከሆነ ምጽአት ናፋቂዎች ብለን ልንፈርጃቸው በቻልን፤ ነገር ግን ኤልያስን የሚፈልጉት አይሁድ የክርስቶስን መወለድ ለሚፈልጉበት ለሥጋቸው፣ በዓለሙ ላለ ልዕልናቸው ነው፡፡ የሀገርን ክብርና ልዕልና መመኘት መልካም ነው፤ ነገር ግን በሃይማኖት ስም ሰዎችን እያስጎመጁ እያማለሉ ከመንገዳቸው ማሳት ግን ነውር ነው፡፡

የቅዱሳንን ስም የሚያከብረው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ወገን በቅዱስ ኤልያስ ስም የመጡ እነዚህን ስዱዳን ማንነት እንዲረዳ ያስፈልጋል፡፡ “ደቂቀ የሎስ” ሆነው የደካሞችን ነፍስ ሊነጥቁ መምጣታቸውን ማስገንዘብ አለብን፡፡ ከተቻለ ሁሉንም ማረምና ማስተካከል የቤተ ክርስቲያን ወገኖች ድርሻ ሊሆን ይገባል፡፡ ካልሆነ በዓላማ ለጥፋት እየሠሩ ካሉት ደበኞች የዋሐኑን መለየት ተገቢ ይሆናል፡፡ አስቀድመን በጽሑፉ መግቢያ ያነሣናት አሳች ሴት እንኳ ለረጅም ጊዜ በማሳቷ ጸንታ ምእመናንን ግራ ስታጋባ መቆየቷ ይታወቃል፡፡ ይህም እንቅስቃሴ ይህቺ ሴት ባደረገችው መንገድ የመናፍስትና የጥንቆላ አሠራር አብሮ እየታከለበት ከሔደ ደግሞ ነገሩ ውስብስብ ስለሚሆን ካሁኑ ሁሉም ወገን የድርሻውን ተወጥቶ በእንጭጩ መቅጨት ይገባል፡፡

‹‹ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል›› 1ጴ 4፣8

‹‹ኃጢአት አንዳች የእግዚአብሔር ፀጋ፣ ሰማያዊ በረከት፣ በነፃ የተቸረን የለጋስ አምላክ ሥጦታ የማጣት ትርጉም ያለው ክፉ የመንፈስ ደዌ ነው፡፡ የዘላለሙን አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ዓላማ ለጊዜውም ቢሆን ያደናቀፈ፣ ልዑላዊ ክብር ተችሮት በአምላክ አምሳያ የተፈጠረውን ሰው ያዋረደ፣ የአዳምን ውበት ያጠፋ፣ የሔዋንን ደም ግባት ያረገፈ፣ የልጆቻቸውን ዕድሜ በበርካታ መቶ ዓመታት የቀነሰ ይኸው የሰው ልጆች የዕድሜ ልክ ቀበኛ ‹‹ኃጢአት›› ነው፡፡

ኃጢአት የሚበልጠው የሚሽረው እስኪመጣ ድረስ የሰዎችን ማንነት የመለወጥ ብቃት፣ የህይወት አቅጣጫን የመቀየር ብርታት፣ የዓለምን ጉዞ ወደ ፈቃዱ የማዞር አቅም ነበረው፡፡ ስለሆነም የምድር ፍጥረትን ገዢ አንገቱን አስደፍቶ በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ገዛው፡፡ አዳም ሊነግስባትና ሊረባባት የተሰጠችውን ምድር በምልአት አፍኖ በውስጧ ያሉትን ሁሉ ነገሰባቸው፤ ረባባቸው፡፡ አዋቂውን ፍጡር አሳውሮ በድንቁርናና ባለማስተዋል ጠፍር ተብትቦ የፈጠረውን አምላክ አስረስቶ እንጨት ያስጠረበው፣ ድንጋይ ያስለዘበው፣ ብረት ያስቀለጠው ይኸው ‹‹ኃጢአት›› ነው፡፡ ‹‹በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ›› ሮሜ 5፣12 ተብሎ እንደተፃፈ የኃጢአት ምክንያቱ አንድ ቢሆንም ርባታው ግን በመላው የሰው ልጆች ልብ ተቀፍቆፎ በአንደበታቸው በገፃቸውና በብልቶቻቸው ሁሉ ስለተፈለፈለ ብዛቱ የምድር አሸዋና የሰማይ ከዋክብት ቢባዙና ቢበዙ የማይተካከሉት ኁልቆ መሳፍርት ከ እስከ የሌለው ሆኗል፡፡

ስለሆነም እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ሲጎበኝ ምድርና ፍጡራን ሲመለከት የደስታ አምላክ እስኪከፋው፣ በፍጡሩ እስኪያዝን፣ በሥራው እስኪፀፀት ድረስ የሚጠቀስ ሁነኛ ሰው እንዳጣ ፍርድና ፅድቅንም እንዳላገኘ ተነግሯል ኢ፡ 59፣16፡፡ የዚህን ምክንያቱ ደመና ሰማይን እንደሚሸፍን ውሃም ሸለቆን እንደሚከድን ኃጢአትም ምድርንና ምድራውያንን ውጦአቸዋልና ከፀበሉ ያልደረሰው ከምሬቱ ያልተጎነጨ ባለመኖሩ ነበር፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ፃዲቅ የለም አንድ ስንኳ አስተዋም የለም እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡

ሁሉ ተሳስተዋል በአንድነትም የማይጠቀሙ ሆነዋል፡፡ ሁሉ ኃጢአት ሰርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል›› ተብሎ የተፃፈ በሮሜ፡ 3፡11፣23፡፡ *የሚደንቀው የኃጢአት ብዛቱ ምንም መሥፈሪያና መዘርዘሪያ መመዘኛና መመጠኛ ቢታጣለት የበደል ስፍዓቱ የምድርን ክበብ ዘልቆ የህዋን ክልል ቢሸፍን አምላካዊ ፍቅር ከዚህ እጅግ በዝቶ ያለልክም ተርፎ የብዙ ብዙ የሰፊም ሰፊ የሆነውን ኃጢአት ሊወጠውና ሊሸፍነው መቻሉ ነው፡፡ የአምላካችን ፍቅሩ ከጥልቆቹ ሁሉ የጠለቀ ከአንሰርቶች ሁሉ የረዘመ ለስፋቱም የአድማስ ጥግ የሌለው በመሆኑ በእርግጥ የኃጥያትን ብዛት ይሸፍናል፡፡

የሰው ልጅ የኃጢአት ብዛት ውጦት ድምፁ በማይሰማበት፣ ጩኸቱ በማይደመጥበት ሰዓት፤ የኃጢአት ብርታት አቅም አሳንሶት፣ ጉልበት አሳጥቶች ጌታውን መከተል ባልቻለበት ጊዜያት፤ የኃጢአት ፅልመጽት ህሊናውን ጋርዶት፣ዓይኑን አሳውሮት የአምላኩን ፈቃድ መለየት በተሳነው ወቅት፤ የጭንቅ ቀን ደራሽ የሆነለት በብቃቱና በብርታቱ ከሁሉ የሚልቀው እንዲያው በነፃ የተገለፀው አምላካዊ ፍቅር ነበር፡፡ ይህንኑ ቅጥ ያጣ ማህበራዊ ኑሮ፣ የተበላሸ አስተሳሰብና በኃጢአት ቀንበር የወደወቅን ህብረተሰብ ለመታደግ ምክንያት ሊሆን የሚችል የሰው ወገን ስላልተገኘ የእግዚብሔር የገዛ ክንዱ መድኃኒት እንዳመጣለት ፅድቁም እንዳገዘው ተጠቅሷል፡፡ ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘልዓለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና›› ዮሐ 3፣16፡፡ እንግዲህ የሰዎችን ሕይወት፣ ታሪክ፣ ስምና መንገድ የቀየረ ይህ እንዲው ተብሎ የተገለፀው ምክንያት የሌለው ፍቅር ነበር፡፡ ልጅ ተብሎ የተገለፀው ጌታ ኃያል አምላክ፣ የሰላም አለቃና የዘለዓለም አባት ተብሎም የተጠራ የዘመናት ሽማግሌ እንጂ እንደሰው ዘመንና ወራት የሚቆጠሩለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ለአባቱ የባህርይ ልጅ ነውና ልጅየውም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ‹‹አንድያ›› ተብሎ የተጠራ፡፡ እንደልጅነቱም የራሱም ፈቃድ የሆነውን የአባቱን ፈቃድ ሊፈፅም የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት እንደሰው ተገለፀ፡፡ ‹‹ፍቅር ሰሀቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብፅሆ እስከለሞት›› ኃያል ወልድን ፍቅር ከመንበሩ ሳበው እስከሞትም አደረሰው፡፡ አዎን! ከሰዎች አዕምሮና አቅም በላይ የሆነውን ኃጢአት በፅድቁ ያንበረከከው የእግዚአብሔር ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ለመለኮታዊ ጌታ መገለፅ በእኛ መካከል ማደርና ስለኃጢአታችን መሞት ብቸኛው ምክንያት ወሰን የሌለው ፍቅሩ ነበር፡፡

ይህም አምላካዊ ግብር ለሰው ልጆች የአምላካቸውን ውዴታ የሚያረጋጋጡበት ጽኑ ማስረጃ ነው፡፡ ሐዋርያውም ‹‹ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለእኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል›› ሲል መስክሯል ሮሜ 5፣8 እግዚአብሔር በባህሪው ፍቅር በመሆኑ ፍቅር ወለድ አምላካዊ ሥራዎቹ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ ሰውን ከአለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ በምናብ እንኳ በማይታወቅበት ጊዜ በግዙፍ አካል አቁሞ በሰማይና በምድር እውቅና የሰጠው፣ ህልውና ያገኘው ማንነት የሰማያዊውን አምላክ መልክና ምሳሌ ተላብሶ ወደር ለማይገኝለት ክብር የበቃው በእግዚአብሔር ፍቅር ነበር፡፡ ይኸው ፍቅር አንድ ጊዜ የወደደውን አዳም እስከመጨረሻው በመውደድ ከእርሱ በፊት የተፈጠሩትን ከሰማይ በታች ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ አስገዛለት፡፡ አምላካዊ ፍቅር በጊዜ፣ በቦታና በሁኔታ የማይገደብ በመሆኑ የጌታውን ፍቅር የዘነጋ ሥጦታውን ልብ ያላለው ሰው ትዕዛዝ ተላልፎ እርቃኑን በቀረ ጊዜ ፍርሃቱን በቅጠል ሊጋርድ ሲጥር ቁርበት ያለበሰው፣ ከደስታ ምድር ሲባረር እንደወጣ ላይቀር ተስፋ የሰጠው፣ የተስፋውን ቃልም በዘመን ፍፃሜ አንድ ልጁን በመላክ ያረጋገጠው የፍቅር መገኛ ምንጭ ልዑል አምላክ ነበር፡፡ በሰው ላይ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው የሚገልፀው መለኮታዊ ጥበቃ፣ ለሥጋዊ ምግቡ በሚያገኘው ምድራዊ በረከት፣ ከሀዘኑ ከጭንቀቱና ከፍራቻው በላይ በሚታደለው የሰላምና የመጽናናት መንፈስ የእግዚአብሔር ፍቅር በየጊዜውና በየሰዓቱ ይገለጣል፡፡ ይልቁንም ወሰን በሌለው ትዕግስቱ በኃጢአት ምክንያት ከፈቃዱ ሲጣላ ከሃሳብ ሲጋጭ የሚገኘውን ሰው ዓይኑ እንዳየች ሳይፈርድ ጆሮው እንደሰማ ሳይበይን ለንስሐ ዕድሜ መስጠቱ ሌላው ዓይነተኛ የፍቅሩ መግለጫ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን የፍቅር ሥራ የሕያው አምላክን የፍቅር ስጦታ መዘርዘር የዝናብን ጠብታ የመቁጠር ያህል ነው፡፡

እንዲያው ነቢዩ እንዳለው ‹‹የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች›› መዝ፡ 32፣5 ሐዋርያውም እንደገለፀው ‹‹ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን›› 2ቆሮ 9፣15 ብሎ ማለፉ የሚቀል ይመስላል፡፡ የዚህ ድንቅ ፍቅር ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር በባህሪው ፍቅር ነውና በአርአያው ለፈጠረው ሰው የሰጠው ሕግ የፍቅር ሕግ ነበር፡፡ የተዘረዘሩ በርካታ ህግጋት ቢኖሩም እንኳን ሕግጋት ሁሉ ፍቅረ እግዚአብሔርና እና ፍቅረ ቢፅ በተሰኙ ሁለት ሕግጋት ይጠቀለላሉ፡፡ የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ሰዎች እርስ በርሳቸው አጥብቀው እንዲዋደዱ አዟል፡፡ ፍቅር የክርስትና ሃይማኖት መሠረት፣ የአምላክ ከሰማይ ወደ ምድር የመውረድ ምስጢር፣ የጌታ ልጆች የእምነት ማህተብ፣ የደቀመዝምርነት ልዩ ምልክት ነው፡፡ ስለሆነም ከምንም ነገር በላይ ከየትኛውም ነገር በፊት ክርስቲያኖች ሊሸከሙት የሚገባ መስቀል፣ ሊያነግቡት የሚገባ ዓርማ ሊሆን ይገባል፡፡ ፍቅር የሌለበት እምነት፣ ፍቅር የጎደለው ፀሎት፣ ፍቅር ያልቀደመው ቸርነት፣ በፍቅር ያልታጀበ አገልግሎት እንዲው ባዶ ደምሮ ደምሮ በዜሮ የማባዛት ያህል ነው፡፡

ስለዚህም ወገኖች ልብ እንበል ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን፡፡ ቅድሳት መጻሕፍትን ስንመረምር እንደምናገኘው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው ዓላማው ፍቅር ነው መኃ 2፣4 ለወደዳቸውም ሰዎች የሚያነሳው የመጀመሪያው ጥያቄ ‹‹የዮናስ ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን›› የሚል ነው ዮሐ 21፣16 ፡፡ የጌታ ቀዳሚ ትዕዛዙም ‹‹የኃጢአትን ብዛት ፍቅር ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስበርሳችሁ አጥብቃችው ተዋደዱ›› ይሰኛል፡፡ 1ጴ 4፣8፡፡ የዚህ ትዕዛዝ ዓላማ እርስ በርስ አጥብቆ መዋደድ ሲሆን ግቡም የኃጢአትን ብዛት መሸፈን ነው፡፡ በፍቅር የማይፈጠር ታሪክ፣ የማይለወጥ ተፈጥሮ ሕግ፣ የማይከፈል ባህር፣ የማይናድ ተራራ፣ የማይሞላ ሸለቆ፣ የማይገሰፅ ማዕበል የለም፡፡ ፍቅር ከሌለ ሁሉ ባዶ ዜሮ እንደሚሆን ሁሉ በፍቅርም ሁሉ ይሆናል፡፡ የኀጢአት ብዛትም ይሸፈናል፡፡ እንደደም የቀላው ኃጢአት እንደ ባዘቶ የሚጠራው፣ እንደ አለላ የሆነው በደል እንደ አመዳይ የሚነፃው በፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ካለ የተናጠልም ሆነ የማኅበር ኃጢአት አይኖርም፡፡ ቢኖርም እንኳ የፍቅር ጌታ በክርስቲያኖች ኅብረት መሐል ባለው የፍቅር ሙላት የኃጢአትን ብዛት ይሸፍነዋል፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ቅደም ተከተል እንወቅ፡፡ ቃሉ እንደሚያዘን ከሁሉ በፊት አጥብቀን እንዋደድ፡፡

ብዙ ጊዜ ንፋስን እንደምንጎስም እየሆንን በከንቱ የምንባክነው ፊተኛውን ደረጃ ዘለን በ2ኛውና በ3ኛው ደረጃ ላይ ስለምንቧቸር ነው፡፡ ፍቅር ያለው ሁሉ አለውና በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ብንፀና ተስፋዎች፣ ስጦታዎችና በረከቶችን ሁሉ ወደ እና ይወርዳሉ፡፡ ስለሆነም ቂምና በቀልን፣ ቅሬታንና ቅያሜን፣ መተቻቸትና መነቃቀፍን አስወግደን ያለጥቁረትና ያለፊት መጨማደድ በቅንነትና በየዋህነት መንፈስ አጥብቀን ልንዋደድ ይገባል፡፡ ይህ ከሆነ አፅራረ ፍቅር ሌጌዎን ወደ እርያዎቹና ወደ ባህሩ ይጣደፋል፡፡ የጦቢያና የሰንበለጥ ስላቅ የፈርኦንና የስናክሬም ዛቻ የጎልያድና የናቡከደነፆር ትምክህት እንደምናምን የሚቆጠረው በክርስቲያኖች ፍቅር ነው፡፡ በመሆኑም የፍቅር ጌታ ከሁሉ በፊት ይህንን ያዙ አለን፡፡ ፍቅርን መያዝን፣ በፍቅር መኖርን፣ በፍቅር መፅናትን፣ በፍቅር መሞትን ለሁላችን ያድለን፡፡

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ!

መምህር ጨምር ተፈራ

የሰሜን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ

{flike}{plusone}