የሰንበት ትምህርት ቤት ፎቶዎች

{gallery}pic-sundayschool{/gallery}

ወጣቶችና ልማት

ወጣቶች ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን በቤተ ክርስቲያኒቱ / በሀገረ ስብከቱ ስር በሚተዳደሩ ገዳማትና አድባራት በሚደረገው ሁሉንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱ አንዱ አካል ወጣቶች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በአስፈለገው መንገድ ሁሉ በመላላክ፣ በመዝሙር፣ በሥነጽሁፍ፣ በድራማ፣ በግጥም፣ ልጆችን በማስተማርና ስብከተ ወንጌልን በሚስፋፋት ፣ የቅጽረ ቤ/ክ ጽዳት በማጽዳት፣ የቤተክርስቲንን አልባሳት በማጠብ፣ ንጣፎችን በማንጠፍና በመጎዝጎዝ፣ ሥነ ሥርዓትን በማስከበር ፣ ነዳያን በመርዳት፣ አጽረራ ቤ/ክ በመካላከል ሥራ ዘብ በመቆም በማናቸውም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ሥራ አጋር በመሆን በዐፀዱ ተከላና እንክብካቤ፣በዘመናዊ የጽህፈትና ሒሳብ ሥራ ፣እንዲሆም በተግባረ እዱ ሥራ በጥበበ እዱ፣ በኪነ ጥበቡ ሥዕሉ፣ የስፌትና ጥልፍ ሥራ በመሥራት ለቤተ ክርስቲኒቱ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ወጣቱ/ ሰንበት ት/ቤቱ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን በሁሉም ትላልቅ ገዳማትና አድባራት ሰ/ት ቤቶች አገልግሎቱ አዘውትሮ የሚሰጥና የተለመደ ቢሆንም ለምሳሌ ያህል የመ/ቅ/ሥ/ካቴድራል እና የምስካዬ ሕዙናን ተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤቶች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ብንመለከት፡-  

 1. ያሬዳዊ ዜማን በጥናትና በማስጠናት በቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት በተለይ በቅዳሴ ጊዜ ተሰጥዎ እንዲቀበሉ ከማድረጉም በላይ ጋብቻቸውን በቤ/ክ ለሚፈጽሙ ሙሽሮች መዝሙር በመዘመር፣ በከበሮና በሽብሻቦ በማጀብ ጥሩ መንፈሳዊ አገልግሎት ሰለሚሰጡ ብዙ ሙሽሮች ጋብቻቸውን በካቴድራሉና በገዳሙ እዲፈጽሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡
 2. የድራማና የሥነ ጽሑፍ ክፍሎች በማቋቋም የተለያዩ ድራማዎችን በማዘጋጀትና በታላላቅ በዓላት ለአካባቢው ህብረተሰብ በማሳየት ሥነ ጽሑፎችንም በማቅረብ ሃይማኖታዊና ማህበረሰባዊ እውቀትን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡
 3. በሰበካ ጉባኤና በልማት ኮሚቴ አባልነት በመሳተፍ ወሳኝና ቁልፍ የሆኑ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡
 4. የሰንበት ት/ቤቶች አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን የሞራል እሴቶች ጠብቀው ሕይወታቸው ግብረ ገብነት ባለው መንገድ እንዲመሩ የዲስፕሊን ኮሚቴ በማቋቋም የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ወጣቶች የግብረ ገብነት ችግር ሲገጥማቸው ወደ ዲስፕሊን ኮሚቴው ቀርበው መንፈሳዊና ሥነ-ልቦናዊ ምክር በመቀበል በዚህ ረገድ ላጋጠማቸው ችግር መፍትሄ በማግኘት የቤተክርስቲያንን ሕብረተሰብ የሞራል ደረጃ ጠብቀው በማስጠበቅ አርአያነት ያለው ህይወትና ሥራ ሠርተው እንዲኖሩ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ ሰንበት ት/ቤቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ወጣቶች እንቅስቃሴ በትምህርትም ሆነ በሥራ መስክ ግባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስለሆነም ሰንበት ት/ቤቶቹ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን አዳዲስ የልማት መርሐ ግብሮች በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ ለቤተክርስቲያኗ እና ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል፣ በማበርከት ላይም ይገኛሉ፡፡

የወጣቶች እንቅስቃሴ

ስመ ጥር የሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቀዳማዊትና ጥንታዊት፣ ሰማዊትና ሐዋርዊት፣ ብሔራዊትና ሉዐአላዊት፣ የሥልጣኔና የሥነ ምግባር ምንጭ ፣ የሕግና ሥነ ሥርዓት አውጭ፣ የተቀደሰ ባህልና ሥነ ጽሁፍ ባለቤት፣ የኪነ ጥበብና ተግባረ ዕድ፣ የታሪክና ቅርስ ባለቤት ሆና ለውዲቱ እናት ሀገራችን ጠብቃ አውርሳለች፡፡ስለሆነም የታሪክ አደራ ያለባቸው የዘመኑ ወጣቶች ተተኪዎችን ለማፍራት የአባቶቻቸውን አደራ እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም በ1930ዎቹ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ከአባቶቻቸው የወረሱትን አሰራር ተከትለው በተለያዩ ማህበራት ስም ሲደራጁ የነበራቸው ዋና ዓላማ ትውልዱን አቀራርቦ አንድ ወጥ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ነበር፡፡  ይህን የመሰለ ትውልድ ለማምጣት ሰንበት ት/ቤቶች ባለፉት ዓመታት በአባቶቻቸው ሥር በመታዘዝ፣ ከሀገረ ስብከቱ መመሪያን በመቀበል፣ በሙሉ ዕውቀታቸው፣ ገንዘባቸውና ጊዜቸው መሰዋዕት ከፍሏል እየከፈሉም ይገናሉ በዚህ ተጋድሏቸው ምክንያትም ከመካከለኛው መ.ክ.ዘ በኋላ ቀዝቅዞ የነበረውን የሰብካተ ወንጌል መርሐ ግብር እንቀሳቅሰዋል፣ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ዘመናዊ በሆነ የትምህርት አሰጣጥ መንገድ ለወጣቱ ትውልድ እንዲዳረስ አደርገዋል፣ ልዩ ልዩ የትምህርት መጻህፍትን በማዘጋጀት ፣ ወጣቱ ትውልድ በዝማሬ እና ሰብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲሳተፍ አድርገዋል በማድረግ ላይም ይገናሉ፡፡ ኮርሶችን፣ ሴሚናሮችን ሥልጠናዎችን፣ ጉዞዎችን በማዘጋጀት ምእመናን ትምህርተ ቤተ ክርስቲንን ምቹ በሆነ መንገድ እንዲያገኙ አድርገዋል በማድረግ ላይም ይገኛሉ፡፡

ከዚህ መንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን በቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገረ ስብከቱ ስር በሚተዳደሩ ገዳማትና አድባራት በሚደረገው ሁሉንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱ አንዱ አካል ወጣቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በአስፈለገው መንገድ ሁሉ በመላላክ፣ በመዝሙር፣ በሥነጽሁፍ፣ በድራማ፣ በግጥም፣ ልጆችን በማስተማርና ስብከተ ወንጌልን በሚስፋፋት ፣ የቅጽረ ቤ/ክ ጽዳት በማጽዳት፣ የቤተክርስቲንን አልባሳት በማጠብ፣ ንጣፎችን በማንጠፍና በመጎዝጎዝ፣ ሥነ ሥርዓትን በማስከበር ፣ ነዳያን በመርዳት፣ አጽረራ ቤ/ክ በመካላከል ሥራ ዘብ በመቆም በማናቸውም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ሥራ አጋዥ በመሆን በዐፀዱ ተከላና እንክብካቤ፣በዘመናዊ የጽህፈትና ሒሳብ ሥራ ፣እንዲሆም በተግባረ እዱና  በኪነ ጥበቡ ሥራ  በጥበበ እዱ፣ ሥዕሉ፣ የስፌትና ጥልፍ ሥራ በመሥራት ለቤተ ክርስቲኒቱ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ወጣቱ/ ሰንበት ት/ቤቱ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

ምንም እንኳን በሁሉም ትላልቅ ገዳማትና አድባራት ሰ/ት ቤቶች አገልግሎቱ አዘውትሮ የሚሰጥና የተለመደ ቢሆንም ለምሳሌ ያህል የመ/ቅ/ሥ/ካቴድራል እና የምስካዬ ሕዙናን ተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤቶች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ብንመለከት፡-  

 1. ያሬዳዊ ዜማን በጥናትና በማስጠናት በቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት በተለይ በቅዳሴ ጊዜ ተሰጥዎ እንዲቀበሉ ከማድረጉም በላይ ጋብቻቸውን በቤ/ክ ለሚፈጽሙ ሙሽሮች መዝሙር በመዘመር፣ በከበሮና በሽብሻቦ በማጀብ ጥሩ መንፈሳዊ አገልግሎት ሰለሚሰጡ ብዙ ሙሽሮች ጋብቻቸውን በካቴድራሉና በገዳሙ እዲፈጽሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡
 2. የድራማና የሥነ ጽሑፍ ክፍሎች በማቋቋም የተለያዩ ድራማዎችን በማዘጋጀትና በታላላቅ በዓላት ለአካባቢው ህብረተሰብ በማሳየት ሥነ ጽሑፎችንም በማቅረብ ሃይማኖታዊና ማህበረሰባዊ እውቀትን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡
 3. በሰበካ ጉባኤና በልማት ኮሚቴ አባልነት በመሳተፍ ወሳኝና ቁልፍ የሆኑ የልማት ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡
 4. የሰንበት ት/ቤቶች አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን የሞራል እሴቶች ጠብቀው ሕይወታቸው ግብረ ገብነት ባለው መንገድ እንዲመሩ የዲስፕሊን ኮሚቴ በማቋቋም የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ወጣቶች የግብረ ገብነት ችግር ሲገጥማቸው ወደ ዲስፕሊን ኮሚቴው ቀርበው መንፈሳዊና ሥነ-ልቦናዊ ምክር በመቀበል በዚህ ረገድ ላጋጠማቸው ችግር መፍትሄ በማግኘት የቤተክርስቲያንን ሕብረተሰብ የሞራል ደረጃ ጠብቀው በማስጠበቅ አርአያነት ያለው ህይወትና ሥራ ሠርተው እንዲኖሩ በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ ሰንበት ት/ቤቶች ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ወጣቶች እንቅስቃሴ በትምህርትም ሆነ በሥራ መስክ ግባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስለሆነም ሰንበት ት/ቤቶቹ ብዙ ገጽታ ያላቸው አዳዲስ መርሐ ግብሮች በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ ለቤተክርስቲያኗ እና ለሀገሪቱ በሞራ የተገነባ አስተማማኝ ተከታይ ትውልድ እንዲኖራት የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል፣ በማበርከት ላይም ይገኛሉ፡፡

ትምህርተ ሃይማኖት

በሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዓለማየሁ

ወልድ ዋሕድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት መሠረታዊ እምነት «ተዋሕዶ» ነው። ተዋሕዶን የሚተረጉም ኃይለ ቃልም ፣ «ወልድ ዋሕድ» የሚለው ነው።

ወልድ ዋሕድ ለሚለው ሥያሜ መሠረቱ «ቃል ሥጋ ኮነ» የሚለው ቃለ ወንጌል ነው። ዮሐ ፩፥፲፬። ስለሆነም፣ የዚህ ዝግጅት ዐቢይ ርእስ /ዋና ርእስ/ ወልድ ዋሕድ እንዲባል ተመርጦአል።
በዚህ ዝግጅት የሚቀርቡ ንኡሳን አርእስተ ትምህርት በየርእሳቸው እየታተቱ የሚቀርቡ ሆኖ ጥናቱ በማስረጃ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ አዘጋጁ ተገቢውን ጥረት ያደርጋል። ለወጣቱ ግንዛቤ ይሰጣል ተብሎ የሚታመንበት ዝግጅት እንዲሆንም በቀላል አገላለጽ ለማቅረብ ይሞክራል። የትምህርተ ሃይማኖት ምሥጢራዊ ይዘት ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ሊቃውንት የትርጉም ዘይቤ እየተገናዘበ ይቀርባል።

የዝግጁቱ ዋና ዓላማ፣ ወጣቶች የትምህርተ ሃይማኖት ግንዛቤያቸውን እንዲያሰፉ ማድርግ በመሆኑ፣ የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት ሊያዛቡ ከሚችሉ አዳዲስ አስተሳሰቦችና የግል አስተያየቶች ፍጹም ነፃ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ሆኖ እንዲቀርብ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል። ከአንባቢያን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሁሉ አስፈላጊው ትኩረት እየተሰጣቸው ተገቢውን መልስ እንዲያገኙ ማድረግ የአዘጋጁ ተቀዳሚ ተግባርና ግዴታ ነው። ይህን ዝግጅት የሚከታተሉ አንባብያንም እያንዳንዱን ኃይለ ቃል፣ በማስተዋል መከታተል፣ ምሥጢሩንና ቁም ነገሩንም በጥንቃቄ መቅሰም ይጠበቅባቸዋል። ጥበብና ማስተዋል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ይስጠን። ከእግዚአብሔር አጋዥነትና ረድኤት ውጪ ምንም ምን የሚሆን ነገር ስለሌለ፣ በተለይም ባሕረ ጥበባት የሆነውን ትምህርተ መለኮት ለማቅረብ መሞከር፣ ውቅያኖስን በእንቊላል ቅርፊት… ማለት በመሆኑ፣ የጥበባት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቡንና ማስተዋሉን እንዲሰጠን እንለምነዋለን።

ትምህርተ ሃይማኖት መለኮታዊ ምሥጢርን የሚያስረዳ እንደመሆኑ ትምህርቱ ጥልቅ፣ ረቂቅና ምጡቅ ነው። ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ባጭር ባጭሩ ይቀርባል።

የሃይማኖት ትርጉም 

ሃይማኖት ምንድን ነው?

ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል።

ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ ፲፩፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም፦ «እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው።» ይልና በመቀጠልም «ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን።» ብሎአል። ዕብ ፲፩፥፩-፫። ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም።

የሃይማኖት ኃይል ልዩና ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘው፣ ምድራዊ ባለሥልጣን የማይገዛውን የሚገዛ፣ በዓይነ ሥጋ የማይታየውን የሚያሳይ፣ በእጅ የማይዳሰሰውን የሚዳስስ፣ በሥጋዊ ጥበብ የማይመረመረውን የሚመረምር ምሥጢር መሆኑ ነው። ማቴ ፲፮፥፲፯።

ልዕልና ነፍስ /የነፍስ ልዕልና/ ክብረ ነፍስ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፤ ከሃይማኖት ውጪ የሚሆነው ሁሉ ኃጢአትና በደል ነው። «ወኲሉ ዘይከውን ዘእንበለ አሚን ኃጢአት ወጌጋይ ውእቱ። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአትም፣ በደልም ነው።» ሮሜ ፲፬፥፳፫። የሚታይና የማይታይ፣ ግዙፍና ረቂቅ፣ ሁሉ ከማይታይ እንደሆነ ማለትም በመለኮታዊ ሥልጣን የተገኘ መሆኑን ያሳውቃል።

እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ መገኘት ምክንያት ሳይሻለት በከሃሊነቱ እምሀበአልቦ ፈጥሮታል። ይህን ማወቅ የሚያስችል ከሃይማኖት ውጪ ሌላ ጥበብ ፈጽሞ የለም። የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ የመሆን ዕድል የሚያገኘው በሃይማኖት ብቻ ነው። በዓለም ያለውን ሥርዓት በቀላሉ በምሳሌነት ማየት ይቻላል፤ ይኸውም የአንድን ሰው ሃብትና ንብረት ለመውረስ በቀላሉ ባለመብት መሆን የሚቻለው የባለጸጋው ወይም የባለሀብቱ ልጅ ሆኖ መገኘት ሲቻል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም በሃይማኖት ልጅነትን ካላገኙ የመንግሥቱ ወራሽ መሆን አይቻልም።

«እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።» እንዳለ ጌታ በቅዱስ ወንጌል። ዮሐ ፫፥፭።

«… ስለዚህ ከእንግዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም። ልጅም ከሆንክ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።» ገላ ፬፥፬-፯።
ሃይማኖት በአማኙ ዘንድ ሦስት ነገሮች ተሟልተው እንዲገኙ ግድ ይላል። እነዚህም፦

፩. ትክክለኛ አረዳድ /እውነት/
፪. የልብ ንጽሕና /ቅንነት/
፫. መጥዎተ ርእስ፣ ማለትም ጥብዓት፣ ራስን መካድ፣ ራስን አሳልፎ ለሃይማኖት መገዛት ፈቃደ ሥጋን አሸንፎ መስቀልን መሸከም የሚሉ ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት አማኝ ግብዝ ሃይማኖተኛ ይባላል።

ማስረጃ

«… እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ። አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል። …» ያዕ ፪፥፲፬-፳፪። ማር ፭፥፯። ጌታም በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይለናል። «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።» ማቴ ፯፥፳፩።

«ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ። መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።» ማር ፰፥፴፬። ሉቃ ፱፥፳፫። ማቴ ፲፥፴፰፣ ፲፮፥፳፬።

«ወኅሊናሁሰ ለነፍስትነ ሞተ ያመጽእ ላእሌነ፤ ወሕሊናሁሰ ለመንፈስ ሰላመ ወሕይወተ ይሁብነ። የሥጋችን ፈቃድ ሞትን ያመጣብናል /ያስፈርድብናል/ የነፍሳችን ፈቃዱ ግን ሰላምን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን ድኅነትን ይሰጠናል። እስመ ኅሊናሁ ለነፍስትነ ፀሩ ለእግዚአብሔር ውእቱ። የሥጋችን ፈቃዱ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና ሞትን ያመጣብናል።» ሮሜ ፰፥፭-፰።
የሃይማኖት ዓላማውና ግቡ፣ ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማሳወቅና ፍጡር በፈጣሪው ሕግና ትእዛዝ እየተመራ ዘለዓለማዊ ክብር እንዲያገኝ ማድረግ ነው። ማቴ ፳፭፥፴፬።

ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፈጣሪ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ በመለኮታዊ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር፣ ለመንግሥቱ ሽረት፣ ለሕልውናው ኅልፈት የሌለበት አንድ ፈጣሪ፣ አንድ አምላክ መኖሩን አውቆ ማመን ማለት ነው።

«እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።» ዘዳ ፭፥፬።

የማይታይና የማይመረመር፣ የማይገሰስና የማይዳሰስ፣ ሕያወ ባሕርይ እግዚአብሔር በከሃሊነቱ ሁሉን የፈጠረ፣ በመግቦቱ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ በቸርነቱ ሁሉን የሚጠብቅ አምላክ በመሆኑ ለፍጥረቱ የሚታወቅበት ገጽታ አንዱ ይኸው ነው። ሁሉን የሚገዛ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር በመሆኑ ይቅርታውና መግቦቱ በሁሉም ላይ ነው።

«እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ላዕለ ኲሉ፣ ይሬስየከ ትሣሃል ላዕለ ኲሉ። ማለት በሁሉ ላይ ያለ ሥልጣንህና አገዛዝህ ሁሉን ይቅር እንድትል ያደርግሃል።» እንዲል።

«… እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።» ማቴ ፭፥፵፭።

በከሃሊነቱ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር የማይታይ፣ የማይመረመርና የማይዳሰስ፣ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ባሕርዩ ከሚገለጽባቸው አያሌ መገለጫዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። እነሱም፦

፩. ፈጣሪ
፪. ከሃሊ
፫. ምሉእ
፬. ዘለዓለማዊ
፭. ቅዱስ
፮. ፍጹም
፯. ማእምር /አዋቂ/ ጥበበኛ የሚሉ ናቸው። እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።

እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው

ፈጣሪ ስንል የሌለን ወይም ያልነበረን ነገር በሥልጣኑና በከሃሊነቱ ያስገኘ፣ ዓለምን እምሀበአልቦ /ካለመኖር ወደ መኖር/ የፈጠረ ማለታችን ነው። ዓለምን እምሀበአልቦ ያስገኘ፣ በመለኮታዊ  ሥልጣኑ የሚታየውንና የማይታየውን፣ ግዙፉንና ረቂቁን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔር ዓለምን /ፍጥረቱን/ ለመፍጠር ምክንያት የሆነው መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ነው፤ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑም የፍጥረታት ሁሉ ጌታና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እንዲሁ አልተወውም፤ በመግቦቱ ይጠብቀዋል፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑና በመለኮታዊ ሥልጣኑ መሳይ ተወዳዳሪ ስለሌለውም እግዚአብሔር አንድ አምላክ ይባላል።
 
እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር፣ ይሁን ብሎ በቃሉ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑና በከሃሊነቱ ፈጠረው እንጂ ፍጥረታትን ለማስገኘት ሌላ አፍአዊ ምክንያት አላስፈለገውም። እንደዚህ ያለ መለኮታዊ ሥልጣን በሰማይም በምድርም ስለሌለ፣ እግዚአብሔር ብቻ ፈጣሪ እንዲባል ያደርገዋል። «ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቊጥር የሚያወጣ እርሱ ነው። ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። በኃይሉ ብዛትና በከሃሊነቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።» ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ኢሳ ፵፥፳፮።

በእግዚአብሔር ረቂቅ ሥልጣንና ከሃሊነት የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ሥርዓት ተሠርቶለት፤ ወሰን ተበጅቶለት ይኖራል። ከተሠራለት ሥርዓት አይወጣም፤ ከተደነገገለት ወሰን አያልፍም። ለይኩን ባለው መለኮታዊ ቃሉ እንደተፈጠረ ሁሉ፣ በመለኮታዊ ትእዛዙ ፀንቶ ይኖራል። መዝ ፴፪፥፬-፱፣ ዮሐ ፩፥፫።

«እነሆ ተራሮችን የሠራ ነፋስንም የፈጠረ፣. . . ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፣ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።» አሞ ፬፥፲፫። «ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ፤ ያፀናትም፣ መኖሪያ ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ እንዲህ ይላል። . . . ይናገሩ፤ ይቅረቡም፤ በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም፣ የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም። እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒትም ነኝ ከእኔም በቀር ማንም የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። ኢሳ ፵፭፥፲፰-፳፪።

በዓለም ታላቁ መጽሐፍ በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፉን የሚጀምርልን የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ዘፍ ፩፥፩፣ ዮሐ ፩፥፫፣ መዝ ፴፪፥፮። ሰማይና ምድር ሲባልም፣ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ፣ የሚታየውንና የማይታየውን፣ በሰው ዘንድ የታወቀውንና ገና ያለተደረሰበትን ፍጥረት ሁሉ አጠቃልሎ የያዘ ነው። ለዚህም ሁሉ ፈጣሪውና አስገኚው እግዚአብሔር በመሆኑ ዓለም የእግዚአብሔር ፍጥረት በመባል ይታወቃል። ዮሐ ፩፥፫፣ ቆላ ፩፥፲፮።

ማንኛውም የሥራ ውጤት ያለ ሠራተኛ ሊገኝ እንደማይችል ሁሉ፣ ማንኛውም ፍጡር ያለፈጣሪ አልተገኘም። ምሳሌውን እንመልከት። በባሕር ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፋን መርከቦች፣ ከባዱንና ቀላሉን ሸክም ችለው፣ ሕዋውን እየቀዘፉ በሰማይ የሚበሩ አውሮፕላኖች፣ ውስብስቡን የዓለም ምሥጢር በትንሽ አካሉ አከማችቶ የያዘ ኮምፒውተር፣ በአጠቃላይ ዕፁብ ድንቅ የሚባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ የሰው ልጅ አእምሮ ተጨንቆ ተጠብቦ ያስገኛቸው የጥበብ ውጤቶች እንጂ በራሳቸው የተገኙ አይደለም። ታዲያ ከላይ የተጠቀሱ የሰው ልጅ መገልገያዎች በራሳቸው መገኘት የሚችሉ ካልሆነ እነዚህን ያስገኘ ረቂቅ የሰው ልጅ አእምሮ እንዴት ያለ ፈጣሪ ሊገኝ ይችላል ተብሎ ሊታሰብ ይችላል!!! ፈጽሞ አይታሰብም። ከታሰበም አስተሳሰቡ የስንፍና ውጤት ይሆናል። ለዚሁም ነው፣ «ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል።» ተብሎ የተጻፈው። መዝ ፲፫፥፩፣ ኢሳ ፵፭፥፲፩።

እግዚአብሔር ከሃሊ ነው

ከሃሊ ማለት ሁሉን የሚችል፣ በፍጡር ዘንድ ፈጽሞ የማይቻልን ሁሉ ማድረግ የሚችል፣ ለችሎታው ወሰንና ገደብ የሌለበት፣ ይህን ይችላል ያን ግን አይችልም የማይባል ፍጹም ከሃሊ ማለት ነው። እግዚአብሔር፣ ሁሉም ነገር ከሥልጣኑ በታች በመሆኑ ሁሉም ይቻለዋል።

ይህን አስመልክቶ በዕብራይስጡ ቃል «ኤልሻዳይ» ተብሎ ተሰይሟል፤ ሁሉን የሚችል ማለት ነው። እግዚአብሔር ለአብራም በተገለጠለት ጊዜ፣ ከሃሊነቱን በሚያረጋግጥ ቃል እንደተገለጠለት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ያስተምረናል። «አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ፍጹምም ሁን። ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፤ እጅግም አበዛሃለሁ አለው።» ዘፍ ፲፯፥፩።

ፍጹም ከሃሊነት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን በመሆኑ እግዚአብሔር ፍጹም ከሃሊ ይባላል። «በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት ወደ አንተ እመለሳለሁ ሣራም ልጅን ታገኛለች።» ዘፍ ፲፰፥፲፬። «. . . ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው። ማቴ ፲፱፥፳፭-፳፮። ሉቃ ፩፥፴፭-፴፰።

እግዚአብሔር በሁሉ ምሉእ ነው

ምሉእ ማለት፣ ፍጹም የሆነ፣ ጉድለት /ሕፀፅ/ የሌለበት፣ በጊዜና በቦታ የማይወሰን፣ መቼም መች የነበረ ያለና የሚኖር ማለት ሆኖ የዚህ ባሕርይ ባለቤትም እግዚአብሔር ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ልዕልና ያለው አምላክ በመሆኑ ልዕልናውን ለመግለጽ ሲባል በሰማይ ያለ፣ ሰማያዊ አምላክ፣ ሰማያዊ አባት እየተባለ ይጠራል። ማቴ ፮፥፱-፲፣ ፲፰፥፲።

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ይወስናል እንጂ ሰማይና ምድር እግዚአብሔርን አይወስኑም። ከፍታዎችና ጥልቆች ሁሉ በእግዚአብሔር መዳፍ ናቸው፤

ማስረጃ

«ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ፤ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፤ ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ። እንደ ንሥር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከ ባሕርም መጨረሻ ብበር በዚያ እጅህ ትመራኛለች፤ ቀኝህም ትይዘኛለች። በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፣ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች።» መዝ ፻፴፰፥፯-፲፪።

«እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። ሰው በስውር ቢሸሸግ፤ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።» ኤር ፳፫፥፳፫።

«የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር /ምሥጢር/ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ? ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።» ኢዮ ፲፩፥፯-፱።

«ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማነው?  . . . እነሆ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው። . . . አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው። ከምናምን እንደሚያንሱ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? . . .።» ኢሳ ፵፥፲፪-፲፰።

እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው

ዘለዓለማዊ የሚለው ቃል ከቋንቋነቱ አኳያ ሲታይ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ደካማ ወይም አናሳ ቃል ሆኖ የሚታይ ይመስላል። በእርግጥም የቃሉ ገላጭነት የደከመ ወይም የጠበበ ነው። ይሁንና ሌሎች ቃላት ቢሆኑም የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ባሕርይ በፍጹምነት የመግለጽ ብቃት አላቸው ብሎ መገመት አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም።

የሆነ ሆኖ ግን ዘለዓለማዊ ከሚለው ቃል መረዳት የሚቻለው፣ እግዚአብሔር አምላክ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፍጻሜ /መጨረሻ/ መነሻና መድረሻ የሌለው፣ እርሱ ራሱ መጀመሪያና መጨረሻ፣ የሆነ፣ የነበረ፣ ያለና የሚኖር ኅልፈትና ሽረት የሌለበት አምላክ መሆኑን ነው።

ማስረጃ

«ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም፥ ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ።» መዝ ፹፱፥፪።

«የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፣ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።» ኢሳ ፵፬፥፮።

«ሙሴም አግዚአብሔርን፦ እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናነተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ ስሙስ ማነው ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ? አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው።» ዘጸ ፫፥፲፫።
 
«ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።» ዮሐ ራእ ፩፥፰።

እግዚአብሔር ቅዱስ ነው

ቅዱስ ማለት ልዩ፣ ንጹሕ፣ ጽሩይ፣ ከክፉ ነገር ከረከሰ ነገር ሁሉ የተለየ ማለት ነው። እንደዚህ ያለ ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሌላው ፍጥረት ቅዱስ ቢባል ቅድስና ከእግዚአብሔር ስለሚሰጠው ነው። እግዚአብሔር ግን ከሌላ የሚያገኘው፣ የሚጨመርለት ወይም የሚቀነስበት አንድም ነገር ፈጽሞ የለም።

ፍጡርንና ፈጣሪን በአንድ ዓይነት አገላለጽ «ቅዱስ» እያልን ስንጠራ የቋንቋ እጥረት ሊሆን ይችላል እንጂ ባሕርየ ፈጣሪ ከባሕርየ ፍጡር ፈጽሞ የተለየ በመሆኑ የእግዚአብሔር ቅድስናም ከፍጡር ቅድስና ልዩ ነው። የተሻለ ስፋት ያላቸው አንዳንድ ቋንቋዎችም በፍጡርና በፈጣሪ መካከል ያለውን የቅድስና ልዩነት ለይተው ይጠቀማሉ።

ባጭር አገላለፅ ባሕርየ ፍጡር /የፍጡር ባሕርይ/፦
•    ጽድቅና ኃጢአት
•    እውነትና ሐሰት
•    ትሕትናና ትዕቢት
•    ክፋትና ደግነት
•    ሕይወትና ሞት
•    ሹመትና ሽረት
•    ፍትሐዊነትና ፍትሕ አልቦነት
•    ርኅራኄና ጭካኔ
•    ፍቅርና ጥላቻ
•    ቁጣና ትዕግሥት ወዘተ… እየተፈራረቁበት ሲወድቅ ሲነሳ የሚኖር ሕይወት ነው። ፍጡር በአብዛኛው ጊዜ በእግዚአብሔር ቸርነትና መግቦት የሚኖር በመሆኑ ቅድስናው የእግዚአብሔር ምሕረት ታክሎበት የሚገኝ ካልሆነ አስቸጋሪ ይሆናል።

«ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው? እነሆ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?» ኢዮ ፲፭፥፲፬-፲፮።

ማስረጃ

«ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር። አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበር።» ኢሳ ፮፥፩-፫።

«እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ እቅዱሳን ሁኑ።» ዘሌ ፲፱፥፩-፪።

«ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።» ፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፮።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም በቅዱሳን አባቶች በቅዱስ ያሬድና በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አማካይነት ከእግዚአብሔር ባገኘችው ጸጋና በረከት በማሕሌትዋ፣ በሰአታትዋና በቅዳሴዋ እንደ መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር… እያለች ዘወትር ፈጣሪዋን ታመሰግናለች።

ማስረጃ

•    «ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት።»
•    «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉእ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።»
•    «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ ወይሄሉ እስከ ለዓለም።»
•    «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘይሴባሕ እምትጉሃን ወይትቄደስ እምቅዱሳን።»
•    «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ዘወትር /ሁልጊዜ/ በሰማይና በምድር ያለ፤ የሚኖር።»

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ዓይነቱ የማያቋርጥ ምስጋናዋ ከቅዱሳን መላእክት ተርታ ሊያሰልፋት ችሏል።

እግዚአብሔር ፍጹም ነው

ፍጹምነት የእግዚአብሔር ልዩ የባሕርይ ገንዘብ ነው። ፍጹም ማለትም በሁሉ ዘንድ በሁሉ አቅጣጫ የሚገኝ ሕፀፅ /ጉድለት/ የሌለበት፣ ነውር የማይገኝበት፣ በሁሉም የመላ፣ የተካከለ፤ መሳይ፣ ተመሳሳይ፣ አምሳያ የማይገኝለት፤ ኃያል፣ አሸናፊ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ ሁሉን የሚገዛ፣ ወዘተ….. ማለት ነው።

የባሕርይ ፍጹምነት የእግዚአብሔር የግል ገንዘቡ በመሆኑ እንደ እግዚአብሔር ያለ በፍጹምነት የሚገኝ ማንም የለም።

«እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ምስጉን ነው። የአማልክት አምላክ ፍጹም አሸናፊ ነው። የሌለበት ጊዜ የለም፤ የታጣበትም ጊዜ የለም። በመለኮቱ ግን ፈጽሞ የታየበት ጊዜ የለም። እርሱን ማየት የሚችል የለም። አነዋወሩም እንደምን እንደሆነ የሚያውቅ /ማወቅ የሚችል/ የለም።» እንዳሉ ፫፻፲፰ አበው ርቱዓነ ሃይማኖት /ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት/።

«አነሆ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም [መርምረን አንደርስበትም]። የዘመኑም ቁጥር አይመረመርም።» ኢዮ ፴፮፥፳፮።

ማእምር

ማእምር ማለት ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉን የሚረዳ፣ ድርሱን፣ ርግጡን፣ ልኩን የሚያውቅ ወይም ያወቀ ማለት ነው።
 
ዕውቀት ከባሕርይና ከትምህርት ይገኛል። የትምህርት ዕውቀት ማለትም ያልለመዱትን ነገር መልመድ፣ መረዳት፣ መገንዘብ ማለት ነው። ከትምህርት የሚገኝ ዕውቀት ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ግልጽ ከሆነ መነሻና መድረሻ ወደማይገኝለት ወይም ፍጻሜ ወደ ሌለው ውስብስብ ነገር አያደገ፣ እየመጠቀና እየረቀቀ የሚሔድ ልምድ ነው። ሌላው ማወቅ የሚባለው ደግሞ አንድን ነገር ከመሆኑ በፊት፣ በሆነ ጊዜና ከሆነም በኋላ ያለውን ነገር ያመለክታል።

እንዲህ ያለው ዕውቀት ፍጡር ከፈጣሪ በተሰጠው አእምሮ መሠረት የሚያገኘው ክሂሎት /ችሎታ/ ይባላል። ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው የእግዚአብሔር ሰዎችም መጻእያትንና ሐላፊያትን አውቀው ትንቢት ይናገራሉ፣ ያስተምራሉ።

ከባሕርይ የሚገኝ ዕውቀት ደግሞ አስተማሪ፣ መካሪ፣ አዘካሪ ወይም አስታዋሽ ሳያስፈልግ በተፈጥሮ ማለትም በአእምሮ ጠባይዕ የሚገኝ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው። በአጠቃላይ ፍጡር የሆነውን ነገር አይቶ ሰምቶ፣ ተምሮ ተመራምሮ ያውቃል፤ ሐላፊያትን መጻእያትንም እንደ ቅዱሳን ነቢያት መንፈስ እግዚአብሔር ገልጾለት /አናግሮት/ ያውቃል ይናገራል ይመሰክራል። ኢሳ. ፯፥፲፬፣ ፱፥፮። የፍጡር ዕውቀት ሁሉም በዓረፍተ ዘመን የተገደበ ነው፤ ገደብ የሌለው የፍጡር ዕውቀት ፈጽሞ የለም። መገኛውም እግዚአብሔር ነው።

የእግዚአብሔር ዕውቀት ከዚህ ሁሉ ፈጽሞ የተለየ ነው። ነገሮች ሁሉ ከመታሰባቸው፣ ፍጥረታት ሁሉ ከመፈጠራቸው፣ መጻእያት ሁሉ ከመድረሳቸው /ከመሆናቸው/፣ ሓላፊያት ሁሉ ካለፉ ከጠፉ በኋላ በሕሊና አምላክ አሉ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃሉ። የእግዚአብሔርን ዕውቀት ሊገድብ የሚችል ምንም ዓይነት ምክንያት የለም።

ማስረጃ

«ውእቱሰ የአምር ሕሊና ሰብእ እምቅድመ ኵነታ።»

«ልብንና ጥልቅንም መርምሮ ያውቃቸዋል ምክራቸውንም ሁሉ ያውቃል እግዚአብሔር የልቡና አሳብን ሁሉ ያውቃል… ያለፈውንም የሚመጣውን እሱ ይናገራል የተሠወረውንም ምሥጢር ይገልጣል። ከእግዚአብሔር ምክር ሁሉ የሚያመልጥ የለም ከነገሩ ሁሉ አንዲት ቃል ስንኳ የሚሰወረው የለም።» ሲራ ፵፪፥፲፰-፳።

«አቤቱ መረመርኸኝ፥ አውቅኸኝም። አንተ መቀመጤንና መነሳቴን አወቅህ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ። ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥… አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ… እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።» መዝ ፻፴፰፥፩-፮።

«ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።» ዮሐ ፪፥፳፭፣፮፥፷፬፤ ማቴ ፱፥፬።

 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የቤተክርስቲያን ታሪክ

ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ

“ነገሥተ ሳባ ወዐረብ ጋዳ ያመጽኡ” “የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ” /መዝ.71,10/

ነቢዩ ዳዊት “ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ ወጸላእቱሂ ሐመደ ይቀምሑ፤ ነገሥተ ተርሲስ ወደስያት አምኃ ያበውኡ፤ ነገሥተ ሳባ ወዐረብ ጋዳ ያመጽኡ፤ ወይሰግዱ ሎቱ ኲሎሙ ነገሥተ ምድር ኢትዮጵያውያን በፊቱ ይሰግዳሉ፤ ጠላቶቹም ዐመድ ይቅማሉ፤ የጠርሲስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያመጣሉ፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታትም እጅ መንሻ ያቀርባሉ፤ ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል” ብሎ /መዝ.71 9-10/በተናገረው ትንቢት መሠረት ሄሮድስ በነገሠበት ዘመን የይሁዳ ክፍል በምትሆን በቤተልሔም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ጥበበኞች ሰዎች ከምሥራቅ መጡ ” ወደ ቤት ገብተው ሕጻኑን ከእናቱ ጋር አይተው ከፈረስ ከሠረገላ ወርደው ሰገዱለት፤ ሳጥናቸውን ከፍተው ኮረጁዋቸውን ፈትተው ወርቁን ዕጣኑንና ከርቤውን ግብር አገቡለት” /ማቴ.2 1-11/ ብሎ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ እንደጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ተወልዶ ሳለ ወርቅ ዕጣን ከርቤ ከገበሩለት ሦስት ነገሥታት አንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባዜን እንደነበረ ይተረካል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ “የግመሎች ብዛት፣ የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ” /ኢሳ.60.6/ ብሎ በትንቢት እንደተናገረው የወርቅ እጅ መንሻ ያቀረበው ኢትዮጵያዊው ንጉሥ እንደነበር ይነገራል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ክርስቶስን ያወቀችውና መባ በማቅረብ ልደቱን ያከበረችው ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ስለሆነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀዳማዊት ቤተ ክርስቲያን መባሉዋ በትክክል ነው፡፡

ከ1ኛ – 4ኛ ክፍለ ዘመን

“ነዋ ማይ ወመኑ ይከልአኒ ተጠምቆ ” “እነሆ ውሃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ማን ነው” /የሐ.ሥ.8፣36/

የጌታም መልአክ ፊልጶስን ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደሆነ መንገድ ሂድ አለው፤ ተነሥቶም ሔደ፤ እነሆም “ህንደኬ” የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘቡዋም ሁሉ የሰለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር፤ መንፈስም ፊልጶስን ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተገናኝ አለው፤ ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና “በእውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው፤ እርሱም “የተረጐመልኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው፤ ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው፤ ያነብበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፡- እንደ በግ ወደመታረድ ተነዳ፣ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል እንዲሁ አፉን አልከፈተም፤ በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል” ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ እባክህ ነቢዩ ይህን ስለማን ይናገራል ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለሌላ አለው፤ ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት፡፡

በመንገድም ሲሔዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም እነሆ ውሀ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?” አለው፡፡ፊልጶስም “በፍጹም ልብህ ብታምን ተፈቅዶአል” አለው፤ መልሶም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” አለ፡፡ ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፤ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውሀ ወረዱ፤ አጠመቀውም፤ ከውሀውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፤ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና” /የሐ.ሥ.8፡26-39/ በማለት ወንጌላዊው ሉቃስ እንደተረከው የክርስትና እምነትና ጥምቀት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ34 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ንግሥት በሕንደኬ ጃንደረባ በባኮስ አማካይነት ነው፡፡ ያጠመቀውም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ወንጌላዊው ፊልጶስ ነው፤ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ” የሚለውን የእምነት ፎርሙላ በመናገር የጀመረና ለዓለም ያበረከተ ኢትዮጵያዊው ባኮስ ነው፡፡

አይሁድና ተንባለት እስከ ዛሬ ድረስ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ” መሆኑን ለማመን አቅቶዋቸው የተቸገሩበትንና ዓለምን የሚያስቸግሩበትን ክህደትና ኑፋቄ ሳይከተል “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አውቆና አምኖ በማሳመን ለወገኖቹ ትክክለኛውን እምነት ስለ ሰበከ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እስከዛሬ ድረስ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ታምናለች፣ ትሰብካለች፤ ታሳምናለች፡፡ በዘመነ ሐዋርያት የክርስትና እምነትን በመቀበል የመጀመሪያው የወንጌል አዝመራ የሆነው ባኮስ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የእምነትና ሥርዐተ አምልኮ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ነው፡፡ ለሐዲስ ኪዳን ኢትዮጵያም ዓለም ዐቀፍ እውቅና ያገኘ የቤተ ክርስቲያናችን መሥራች ነው፡፡ ባኮስ በዚህ ሃይማኖታዊ ጒዞው የሕገ ኦሪትንና የሕገ ወንጌልን ጽድቅ በአንድ ጒዞ በመፈጸም የራሱንና የአገሩን ስም በቅዱስ መጽሐፍ ለማስጠራት በቅቱአል፡፡

ባኮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ከቅዱስ ፊልጶስ ስለ ክርስቶስ የሰማውንና የተረዳውን ለወገኖቹ ኢትዮጵያውያን እንደ አስተማረ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሓፊ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ ጽፎአል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችውም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ፊልጶስ የክርስትና አባቷ ስለሆነ በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንፃ ጽላት ቀርፃ ታከብረዋለች፡፡ በጸሎቱና በአማላጅነቱም ትታመናለች፤ ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ቅዱስ ማቴዎስ፣ ቅዱስ ናትናኤል፣ ቅዱስ በርተሎሜዎስ፣ ቅዱስ ቶማስ በኑብያና በኢትዮጵያ አውራጃዎች እየተዘዋወሩ ወንጌልን እንደ ሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እነሩፊኖስና እነ ሶቅራጥስ መስክረዋል፡፡

በ4ኛው መቶ ዓመት “ቅዱስና ያለ ተንኰል የሚኖር ነውርም የሌለበት ከኀጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል” /ዕብ.7፣26/ ብሎ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ሊቀ ካህናትነት እንደተናገረው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሾማቸው ከሐዋርያት ሐረገ ክህነት ተያይዞ የመጣ የሐዋርያት ተከታይ የሆነ ሊቀ ካህናት ማግኘት ይገባኛል ብላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እንዲያስመጣላት ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማን ወደ እስክንድርያ ላከች፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያ ፓትርያርክም ራሱኑ ሾሞ ላከው፡፡

ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በመጀመሪያው ምዕት ዓመት ይሁን እንጂ በሲኖዶስ ሕግ የኤጲስ ቆጶስ መንበር የተሰጣት በአራተኛው ምዕት ዓመት በ330 ዓ.ም. ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ተልኮ ሔዶ ከእስክንድርያው ፓትርያርክ ከቅዱስ አትናቴዎስ ዘንድ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሾሞ በመጣው በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መምህርነት በአብርሃና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥት ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት በዐዋጅ ተሰብኩዋል፡፡

ቅዱስ አባ ሰላማ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መንበረ ጵጵስናውን አክሱም ላይ አድርጎ በሀገራችን የወንጌልን ብርሃን በሰፊው ስለገለጠ ከሣቴ ብርሃን ተባለ፡፡ በዚሁ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የታወቀች ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን ለመሆን መብቃቷን ታሪክ ያስረዳል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በምልዓት መፈጸም ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያ ግዛት በሙሉ የወንጌልን ትምህርት ለማዳረስ የሚረዱት ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመ፡፡

ይልቁንም በዚያ ጊዜ ሊቀ ካህናት የነበረውን አንበረምን ሕዝበ ቀድስ ብሎ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው በሕዝበ ቀድስም ስብከት የኖባና የሳባ፣ የናግራንና የትግራይ፣ የአማራና የአንጎት፣ የቀጣ፣ የዘበግዱር ሕዝብ በክርስቶስ አምነውና ተጠምቀው ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስት፣ ከዕብራይስጥና ከፅርዕ ወደ ግዕዝ ቋንቋ መለሰ፡፡ የሳባውያንን የፊደል አቀማመጥ የለወጠውና አዲሱንም ከግራ ወደቀኝ የመጻፍና የማንበብ ዘዴ የፈጠረ እሱ ነው፡፡ ይልቁንም ድምፁን በመከተል 6ቱን የፊደል ድምፆች የጨመረ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እንደሆነ ታሪክ ይናገራል፡፡

ከቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ሢመተ ጵጵስና ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ጵጵስና ደረጃ ታወቀች፡፡ከዚያም ጊዜ አንሥቶ እስከ 20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ከግብጻውያን ብቻ ጳጳሳት እየተሾሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ቈይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከኢትዮጵያውያን መካከል ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጳጳስ፣ አቡነ ፊልጶስ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው እንደተሾሙ ታሪክ ይናገራል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከጥንታዊት የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ጋር የሥርዐተ እምነት አንድነትና የእህትማማችነት ህብረት ስለነበራት ግብፃውያን ጳጳሳት ሥልጣነ ክህነት በመስጠት ብቻ ተወስነው የቀረው የአስተዳደሩና የውስጥ አመራሩ ይዞታ ግን በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይካሄድ እንደነበር ታሪክ የማይክደው ሐቅ ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በሥርዐተ ትምህርትና በባህል ራሱን የቻለ አቋም የነበራትና ያላት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡

ሰንበት ት/ቤት – ታሪክ

በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ታሪክ የወጣቶች ሰንበት ት/ቤት ማቋቋም የተጀመረው ከ1936 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ የኸውም ከብዙ ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሃይማኖት ትምህርት ይከታተሉ የነበሩ ወጣቶች “የሥላሴ ማህበር” ተብሎ የሚጠራ አንድ ማህበር መሠረቱ፣ ይህ ማህበር ለወንዶች ብቻ የተቋቋመ ነበር ይሁንና ከጥቂት ዓመታት በኋላ የካቴድራሉ አስተዳደር ወጣት ልጃገረዶችም የራሳቸውን ማህበር መመሥረት እንዳለባቸው አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ለጸሎትና ለአምልኮ ወደ ካቴድራሉ የሚመጡ ልጃገረዶችን ሰብስቦ እነርሱም የራሳቸውን ማህበር እንዲያቋቁሙ አበረታታቸው በመሆኑም “ማህበረ ክርስቶስ” በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ማህበር መሠረቱ፡፡

የእነዚህ ማህበር አባላት የተሻለ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምህርት ማግኘት ሲጀምሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት እየተማሩና እያወቁ በመምጣታቸው በተለይም ልጃገረዶች የቤተክርስቲያንን ዜማ በማጥናት በቤ/ክ ውስጥ ከቁርባን በኋላ መዘመር ጀመሩ፡፡ ይህም እንደ አዲስ ክስተት ታይቶ በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ የሚወደድ ሆኖ ተገኘ የእነዚህ ማህበራት ዓላማቸውም የሚከተሉት ነበሩ፡-

 1. የክርስትና ሃማኖትን መሰረታዊ ዓላማዎች መማርና ማስተባበር ፣
 2. ሰብአዊ ተግባራትን ማካሄድ፣
 3. የክርስቲያንን ብሔራዊ ባህል መጠበቅ፣
 4. ወጣት ልጃገረዶች ያለፍርሃት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉና ለህበረተሰቡ አገልግሎት የሚስፈልገውን የሥራ አመራር ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ናቸው፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው በቅዳሴ ጊዜ የወጣት ልጃገረዶች ተሰጥዎ መቀበልና ከቅዳሴም በኋላ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎችን ማስማታቸው እንደ አዲስ ነገር በመታየቱ ተግባሩ በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ቀጥሎ ተስፋፍቷል፡፡

የምስካየ ኅዙናን ቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የተፈሪ መኮንን እና የእቴጌ መነን ት/ቤት ተማሪዎችን በብዛት መሳብ በመቻሉ በየሳምንቱ እሑድ ተማሪዎች በብዛት ወደ ቤ/ክ እየመጡ በመንፈሳዊ አገልግሎት ተሳታፊ ከሆኑ በኋላ ብዙዎች በቤ/ክ እንዳንድ ሥራዎች በፈቃደኝነት መሳተፍ ጀመሩ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎችና በገዳሙ መካከል አንድነትን መፍጠር የሚችልና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ወጣቶቹ በመጠየቃቸው  “ተምሮ ማሰተማር” የተባለው ታዋቂው ሰንበት ት/ቤት በ1939 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡

የተምሮ ማሰተማር ማህበር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለማህበሩ አባላትና ለህብረተሰቡ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከዚያ በመቀጠል በ1942 ዓ.ም የተቋቋመው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሲሆን የወንጌል መልዕክተኞችና የእሑድ ት/ቤት ማህበር ተመሠረተ፣ በዚሁ ጊዜም ነበር የአሥመራው ማህበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት ማህበር የተቋቋመው፡፡

ቀጥሎም ወደ ታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል፣ ወደ ገነተ ጽጌ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስና ወደ ሌሎች የአዲስ አበባ ታላላቅ ገዳማትና አድባራት ተስፋፋ ከዚያም አልፎ ወደ ዋና ዋና (በጊዜው አጠራር ጠቅላይ ግዛት) ከተሞችና ታላላቅ አውራጃዎች የተቋቋሙበት የደብሩን መለያ ስም በመያዝ በልዩ ልዩ የቅጽል ስም የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራት እየተባሉ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ተጓዙ፡፡ የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር የቀድሞ አመሠራረቱ ከላይ እንደተጠቀሰው በወጣቶችና ልጃገረዶች ግላዊ ተነሳሽነት ፤በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአንዳንድ ዓላማው በገባቸው የአድባራት አለቆችና ሰባክያነ ወንጌል በጎ ፈቃድና ድጋፍ ነበር፡፡ 

በተለይም በ1936 ዓ.ም በወቅቱ የመንበረ ጸባኦት ቅዱስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ የመጀመሪው ሊቀሥልጣናት ሆነው የተሾሙት ሊቀ ሥልናናት አባ መልዕክቱ በኋላም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ ተብለው የተሸሙት ማህበሩ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥረት ከማድረጋቸውም በላይ ማህበሩ በአገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ማህበራት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ቀስ በቀስ በሁሉም ገዳማትና አድባራት ተቋቁሞ ስለነበር ከቤተ ክህነቱ ጋር የሚያገኛኘው መስመር የግድ ስለነበር በጊዜው በስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ መምሪያ ስር የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበራት አንድነት ማእከላዊ ጽ/ቤት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተቋቁሞለት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ ይህ ማዕካላዊ ጽ/ቤት እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ በመጠኑም ቢሆን የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራትን ሲያስተባብር ቆይቷል፡፡ ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ ግን ወደ ወጣቶች ጉዳይ መምሪያነት አደገ፡፡

ይህ በዚህ እንዳለም በ1966 ዓ.ም  በመላው አዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የተቋቋሙት የወጣቶች መንፈሳውያን ማህበራት የለውጡን ሂደት ተጠቅመው በራሳቸው ውሳኔ አጠቃላይ ጉባኤን መሰረቱ ይህ የወጣቶች መንፈሳውን ማህበራት አጠቃላይ ጉባኤ በዚያ ክፉ የደርግ ዘመን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እጅግ ብዙ ቁም ነገሮችን ለቤተ ክርስቲያኒቷ በቆረጥነት አበርክቷል መምሪያውንም ያጠናከረው አጠቃላይ ጉባኤው ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤውና በመምሪያው የተጠናከረ ትብብር የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት እንደቀድሞው የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር እየተባለ በ1970 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው ቃለ ዓዋዲ የቤተ ክርስቲያኒቱ ህጋዊ አካልነቱ ተረጋግጦ ሙሉ በሙሉ ዐውቅና አገኘ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ስያሜው ቀጥሎ በመላ ኢትዮጵያ በስፋት ተስፋፋ፡፡

ይሁን እንጂ ከ1974 ዓ.ም ካቲት ወር ጀምሮ የደርግ  መንግስት “ከአኢወማ” ጋር በስም ይሞካሻል፣ ይመሳሰላል ብሎ በውስጥ በደረገው ተጽዕኖ ምክንያት ሁሉም የወጣቶች መንፈሳውያን ማህበራት በቅዱሳት ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ብልህነት የተመላው ውሳኔ ነበሩ ስማቸው ተለውጦ ይኸውና ከዕለቱ በመነሳት የሰንበት ት/ቤት ተብሎ እስከ አሁን ሊደርስ ችሏል፡፡ መምሪያውም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተባለው ከዚያን ወዲህ ጀምሮ ነው፡፡