በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምሁርና አክሊል ወረዳ ሥር የሚገኘው የሴባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምሁርና አክሊል ወረዳ ሥር የሚገኘው የሴባ አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል።

የሴባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም መሠረተ ድንጋይ በወቅቱ የጉራጌና የሀድያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በብፁዕ አቡነ ቀለሜንጦስ ተቀምጦ ከ9 ዓመታት የግንባታ ቆይታ በኋላ እንደተጠናቀቀ ተገልጿል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ ምክትል ዲን ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ፣የሀገረ ስብከቱና የወረዳ ቤተክህነቱ የሥራ ኃላፊዎች: የገዳማት እና የአድባራት፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምእመናን ተገኝተዋል ሲል የኢኦተቤ ቲቪ በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-

 1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
 2. ፌስ ቡክ ገጽ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese
 3. ቴሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese

4.ትዊተር :-www.Twitter.com/AddisDiocese

ገዳማትና አድባራት

ካቴድራል(የካቴድራል ቤተክርስትያን)

ካቴድራል ማለት ቃሉ ግዕዝ ወይም አማርኛ ሳይሆን ጥሬ ቃሉ ግሪክ ሲሆን ወደ ላቲን ሲተረጎም (cathedra) ካቴድራል ይላል፡፡  ይህም የጳጳስ መቀመጫ (ዙፋን) ማለት ሲሆን በጥንታዊያን ክርስቲያኖች አመለካከት ካቴድራል ማለት የሥልጣን ምልክት ማለት ነው፡፡  የካቴድራል ሕንጻዎች መሠራት ያለባቸው በትልልቅ ከተማዎች ነው እንጂ በአነስተኛ መንደር መሠራት የለበትም፡፡  የካቴድራል ቤተክርስቲያን በጣም ትልቅ ግዙፍ ሕንጻ ነው፡፡ 

ጥንታዊያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ተብሎ የተሰጣቸው ስያሜ የለም፡፡  ይህም ቃሉ ያልተለመደ የባዕድ ቃል በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1924 ዓ.ም የተሰራውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እጅግ በሥፋቱ ትልቅ በመሆኑና ውበትን የተላበሰ ዘመናዊ ሕንጻ በመሆኑ ይህን በማየትና በማድነቅ በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ቤተክርስቲያኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የካቴድራል ስም ተሰጠው፡፡

ከላይ እንደተገለፀው ካቴድራል ሲባል ብዙ ምዕመናን የሚይዝ ትልቅና ውበት የተላበሰ በሕንጻ አሠራሩም ካሉት ሦስት ዓይነት የቤተክርስቲያን አሠራር ውስጥ ከምኩራብ (አራት መአዘን)፤ ከክብ ቤተንጉሥ ከዋሻ አሠራር ዓይነቶች ውስጥ ካቴድራል የምኩራብ ከኦሪቱ ትውፊት የተወሰደውን ዓይነት ቅርፅ የያዘ ነው፡፡  ካቴድራል ተብሎ የሚሰየመው ይህ ታላቅ ቤተክርስቲያን ብዙ ምዕመናንን አካቶ ከመያዙም በላይ ሦስት መንበር በቤተ መቅደሱ ወስጥ ሊኖረው ይገባል፡፡  ይህም በክብረ በዓል ጊዜ በሦስቱ መንበር የቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት ተከናውኖ ምዕመናን በሥርዓት እንዲስተናገዱ ይረዳቸዋል፡፡ በተለይ የካቴድራል ቤተክርስቲያን ስያሜ መጥቶ በከተማችን ውስጥ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ የመጣውን የምዕመናን ቁጥር በሥርዓት ለማስተናገድ የቤተክርስቲያኑ ስፋት ታላቅ ድርሻ አለው፡፡     በአጠቃላይ በጥንት ጊዜ የሌለው እና አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የመጣው ካትድራል ብሎ ቤተክርስቲያንን መሰየም ዛሬ እየተለመደና ጠቃሚነቱ እየታወቀ በመምጣቱ በከተማችን በአዲስ አበባ በርካታ ታላላቅ ዘመናዊ ካቴድራሎች ታንፀዋል፡፡

ደብር(የደብር አብያተ ክርስቲያን)

ደብር ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙን ስንመለከት ተራራ ማለት ሲሆን ይህም ደብረሲና ደብረ ታቦር በሚለው ቃል በትርጓሜ ይዘቱ የሲና ተራራ፤ የታቦር ተራራ ብለን እንረዳለን፡፡  ቤተክርስቲያን በተሠራው ሕንጻና በሕንጻው ወሰን ደብሩ እንዲህ ነው ተብሎ ውስጣዊና ውጫዊ ይዘቱን ለመግለጽ ይቻላል በሌላም መልኩ ቤተክርስቲያን በተራራ ትመሰላለች፡፡  ይህም ተራራ ከሌሎች ሥፍራ ይልቅ ጎልቶ ስለሚታይ ነው፡፡  ቤተክርስቲያንም ከሌሎች ሕንጻዎች ሁሉ ጎልታ፣ ተለይታ ትታያለች፡፡  ይህም የክርስቲያኖች የጋራ ቤት ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት የቅድስና ስፍራ በመሆኗ ነው፡፡

ደብረ ማለት ቃሉ ዐቢይ በማለት ሲተረጎም ምሥጢሩ ያስኬዳል ይህም ደብር ተብለው የሚሰየሙት አብያተ ክርስቲያናት ባላቸው የአገልጋይ ካህናት ብዛት ቦታው ዘወትር ስብሃት እግዚአብሔር የማይለይበት ታላቅ የረድኤተ እግዚአብሔር መግለጫ በመሆኑ ታላቅ ቦታ ተብሎ ይጠራል፡፡  ለአበያተ ክርስቲያናት የሚሰጠው ስያሜ የተቀረጸው የቃል ኪዳን ጽላት በቅዱሳን፣ በጻድቃን፣ በመላዕክት፣ በስመ እግዚአብሔር ከሆነ ስማቸው ተጠቅሶ ባላቸው የነጠላ ስም ብቻ ለምሳሌ፡- የቅዱስ ሚካኤል ከሆነ ደብረ ሚካኤል ተብሎ ብቻ አይሰየምም፡፡  ግብራቸውና የሥራ ድርሻቸውን የተገባላቸውን የማይቃጠፍ የዘለዓለም ቃል ኪዳን በመግለፅ ቅዱስ ሚካኤል የምሕረት መልአክ ነውና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ተብሎ ይሰየማል፡፡  እንደዚህ ሁሉ እያንዳንዱ ባለው የቃልኪዳን ስያሜ ደብረ እገሌ ገዳም  እገሌ ገዳም እገሌ በማለት እየተገለፀ አብያተ ክርስቲያናቱ ስያሜ ያገኛሉ፡፡  በስመ እግዚአብሔር ስም የታነጹ ደብሮች የአምላክን ስም በመግለጽ በስያሜዎች ይጠራሉ፡፡  ይህም ለምሳሌ ደብረ ምጽላል እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሲል ምጽላል ማለት መጠጊያ፣ መሸሸጊያ ማለት ነው፡፡  እግዚአብሔር አምላካችን ለዓለሙ ሁሉ መጠለያ፣ መሸሸጊያ ጋሻችን ነውና፡፡   

ገዳም (የገዳም አብያተክርስቲያናት)

ገዳም ማለት ምድረ በደ ማለት ነው፡፡  በገዳም የእኔ የገሌ የሚሉት ንብረት የሌለበት ሁሉ በማህበር በአንድነት በጸሎት በሥራ እየተጉ ፍጹም የዓለምን ኃላፊነት ተረድተው የማታልፍ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዳለች በመገንዘብ ዘወትር በቀኖና ተወስነው የሚኖሩባት የቅዱሳን መኖሪያና ጸጋ እግዚአብሔር የማይለይበት ሲሆን በአንፃሩም ከሁሉ የከበደ የአጋንንት ጸር የሚበዛበት ቦታ ነው፡፡  ገዳምና ገዳማዊ ሕይወት አስፈላጊ በመሆኑ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አርአያ ሆኖን በመገዳመ ቆሮንቶስ(በምድረ በዳ) ከዲያብሎስ የፈተን ዘንድ ተቀመጠ(ማቴ.4፡1-11)ፈታኝ ዲያቢሎስንም ድል አደረገው ገዳማዊ ሕይወትና ገዳም አስፈላጊ ሆኖ የመሠረተልን አምላካችን አርአያችን ኢየሰስ ክርስቶስ ነው፡፡  እኛም እርሱን በመከተል ገዳማዊ ሕይወት ለትሩፋት መሥሪያ፣ ለንስሐ ሕይወት መቆያ ለበረከት ለረድኤት አስፈላጊነቱን አምነን እንጠቀምበታለን፡፡

እንደ ቤተክርስቲያን ሥርዓት አብያተ ክርስቲያናት ገዳም፣ ደብር፣ ካቴድራል ገጠር ተብለው ተሰይመው ይጠራሉ፡፡  ይህ ስያሜ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚሰጠው ካላቸው ይዘት አኳያ ተጠንቶና ተመዝኖ ነው፡፡ በመሆኑም ገዳም የሚባለው ስያሜ የሚሰጠው ቤተክርስቲያኑ መነኮሳት ብቻ የሚኖሩበት ሁሉም በፀሎት በማህሌት፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት በሕብረት የማይነጣጠሉበት በመቁነን፣ በድርጎ፣ ተወስኖ በመነኮሳት ብቻ የሚተዳደር ቦታ ነው፡፡ በገዳም ወንድና ሴት በአንድነት የማህበራዊ አገልግሎት አይገናኙም፡፡ የሴት ገዳምና የወንድ ገዳም ተለይቶ በመወሰን የተከፈለ ነው፡፡  በወንዶች ገዳም የወንዱ ገዳም አስተዳዳሪ፣ አባ ምኔት (የገዳም አባት) ተብሎ ሲጠራ የሴቶች ገዳም ደግሞ እመ ምኔት (የገዳም እናት) ተብለው ይጠራሉ፡፡  በከተማችን ውስጥም በዚህ በአዲስ አበባ ያሉት ከፊል አብያተ ክርስቲያናት ልክ ከከተማ ውጪ እንዳሉት ትላልቅ ገዳማት በሥርዓት የተስተካከሉና በመጠኑም ቢሆን ገዳማዊ ይዘት ስላላቸው ገዳም ተብለው  የተሰየሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡   

ቤተ ክርስትያን

ቤተክርስቲያን ማለት ሁለት ትርጉም ይዞ በዘርፍና በባለቤት የተቀመጠ ስም ነው፡፡ አንደኛው ትርጉም ቤተክርስቲያን ሲል የክርስቲያን ቤት የክርስቲያን መሰብሰቢያ የክርስቲያን መገናኛ ማለት ነው፡፡  ይህም ክርስቲያኖች በአንድነት በመሰብሰብ ወደፈጣሪያቸው ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚፀልዩበት የመድኃኒታቸው የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋ ክቡር ደም የሚቀበሉት የሚሰግዱበት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት የፀሎት ቤት ማለት ነው፡፡  ኢሳ. 56፡7፣ኤር. 7፡10-11፣ ማቴ 21-12፣ ማር 11፡17፣ ሉቃ 1946

ሁለተኛው ትርጉም ቤተክርስቲያን ሲል የክርስቲያን ወገን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ይህም ምሳሌ ትውፊቱ የመጣው ቤተያዕቆብ፣ ቤተ አሮን፣ ቤተ እስራኤል (የያዕቆብ ወገን የአሮን ወገን፣ የእስራኤል ወገን ማለት እንደሆነ ሁሉ ቤተክርስቲያን ሲል የክርስቲያን ወገን የሚለውን ያመለክታል) መዝ 117፡3 113፡1፡1 ማቴ 16፡18፡18፡17፣ የሐዋ 18 የመጀመሪያዋ ቤተክርስትያን በፊልጵስዮስ ሀገር እንደተሠራች የቤተክርስቲያን ታሪክ ቢያስረዳም ሐዋርያትና ሌሎች ክርስቲያኖች በሐዋርያው በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እየተሰበሰቡ ለአመልኮ እንደ ቤተክርስቲያን ይገለገሉበት ነበር፡፡ የሐዋ 12፡12 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ሦስት ዓይነት የቤተክርስቲያን አሠራር እንዳለ እንረዳለን፡፡  

 1. አራት መአዘን (ከምኩራብ የተወሰደ) Cote from Jewish sinagogi
  የአሠራሩ ይዘትን በተመለከተ የአራት መዓዘን ቅርፅ (የምኩራብ ዓይነቱ) የተወረሠው ከአይሁድ ምኩራብና በዘመነ ክርስትናም የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት እሌኒ በኢየሩሳሌም ካሠራችው ቤተክርስቲያን የተቀዳ ነው፡፡
 2. ክብ ቅርፅ ባለሦስት ዙሪያ ክፍል (ቤተ ንጉሥ) Circel cote from king palace
  ዙሪያ ክብ አሠራር (ቤተንጉሥ) ውስጡ በሦስት ግድግደ የተከፈለ ሲሆን ስያሜው የተወረሰው ከግብሩ ከሚሠጠው አገልግሎት የተወረሰ ነው፡፡
 3. የዋሻ ቤተክርስቲያን አሠራር ናቸው (በመጋረጃ የተከፈለ) The cave churchs 
  ዋሻ ሥራ ይህ አሠራር ውስጡ በመጋረጃ ብቻ የተከፈለ ሆኖ ራሱን ችሎ በዘመነ ሐዲስ መናንያን በበረሃ የሚገለገሉበት ቤተክርስትያን ነው፡፡

ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው በሰዎች አስተያየትና ፈቃድ  ወይም በትግል ጥረት የተመሠረተች ተቋም ሳትሆን አምላክ በደሙ  የመሰረታት መታደስ መለወጥ የሌለባት አምሳያዋም ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ነው፡፡ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን ማለት ስብሃተ እግዚአብሔር የሚደርስበት አማናዊ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚቀርብበት በማህበር ፀሎት የአምልኮተ እግዚአብሔር ሥርዓት የሚየርስበት የቃል ኪዳን ጽላቱ የሚገኝበት ክርስቲያኖች የሚሰበሰቡበት ቤት ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶኮክስ ትምህርት፤ እምነትና ትውፊት መሰረት ታቦት የሌለበት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አይባልም፡፡
                          

ማኀበራዊ ጉዳይ

የኢትዮጵያ ቤት ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተዋጽኦ የሚመነጨው ከዐሥርቱ ሕግጋት እና ከስድሰተቱ ቃላተ ወንጌል ነው፡፡ ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪት እና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል በመተባበር ማኅበራዊ ሕግጋትን ያስተምራሉ፡፡ ማኅበራዊ ሕጎች በአንድ የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ የእረስ በእርስ ትስስር እና መተሳስብን ፍቅርንና አብሮ በሰላም የሚኖርበት አንድነትን የሚያጠብቁ መሠረቶች ናቸው፡፡ በመልካም መሠረት ላይ የሚኖር የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ በጊዜ ሂደት የራሱ የሆነ ባህል ይፈጥራል፡፡ ባህል ደግሞ የማንነቱ መገለጫ ከሌላ የኅብረተሰብ ክፍል የሚለይበት ኦርቶዶክሳዊ ማንነቱ የሚታወቅበት አንዱ መንገድ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከተሉትን ማኅበራዊ አሰተዋጽኦዎች አድርጋለች እያደረገችም ነው፡፡ 

ማኅበራዊ አስተዋጽ

፩∙ በበጎ አድራጎት አገልግሎት መሳተፍ

የበጎ አድራጎት መነሻው ቅድሳት መጻሕፍት ሲሆኑ በኅብረተሰብ መካከል መተሳሰብን እና ሰብአዊ ርህራሄን ከማጎልበት ባሻገር ለነፍስ ዋጋ የሚያሰጡ ትምህርቶችንም የያዙ ናቸው፡፡
ስለሆነም የመንፈስዊ አገልግሎት ዋጋ ከመስጠቱም ባሻገር በህብረተሰቡ ዘንድ የመተሳሰብና የሰብአዊ ርኅራኄ መንፈስ ለማዳበር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የህንንም ለማድረግ ጠቃሚ የሆኑት ስልቶች ሕዝቡን ማስተማር፤ ማደራጀት፤ ማስተባበር እና ተቋማትን መክፈት ናቸው፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መነሻውም ሃይማኖት ነው፡፡

እግዚአብሔር ራሱ ያለምንም ከፍያ /በጸጋ/ ፍጥረትን ሁሉ መልካም መሆናቸውን እያረጋገጠ ከመፍጠር የዕለት ተዕለት ፈላጎታቸውን እሰከ መስጠት ድረስ መሠረት ሆአኖል፡፡ አምላካቸውን የተከተሉ ሰዎችም ከአምላካቸው ተምረው ይህንኑ የበጎ ፋቃድ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ያለምንም ክፍያ መንገደኞችን ማብላቱንና ማጠጣቱ ዋና ማስረጃ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅድስ ውስጥ የተዘረዘሩ ብዙ አገልግሎቶች በበጎ ፈቃድ የተከናወኑ ናቸው፡፡ ሰው የተቸገረ ወገኑን እንዲሁም እንግዶችን እየተቀበለ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት ያለውን ለሌለው መርዳትና ማገዝ ይጠበቅበታል፡፡ ደጉ ሳምራዊ ተጎድቶ፣ ቆስሎ ያየውን ሰው፤ ማንም ሳያስገድደው በፈቃዱ አንስቶ፤ ቁስሉን በዘይት ቀብቶ፤ ለሚረዱት ሌሎች ሰዎች ገንዘብ ሰጥቶ፤ ተመልሶ እንደሚረዳው ቃል ገብቶ መሄዱ የሚታወስ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ አሁንም በቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ ዲያቆናት፤ ምእመናን ብዙ ነገሮችን በበጎ ፈቃድ የሠራሉ፡፡
የሕፃናት ማሳደጊያ እና የአረጋውያን መጦሪያ ተቋማት መከፈት

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲየን ድሆችን የመርዳት የቆየ ባህል አላት፡፡ ምጽዋት ከመሥዋዕት ይበልጣል እንዲል፡፡ /ማቴ ፱፥፲፩፤ሆሴ ፮፥፮፤ አረጋዊ መንፈሳዊ/፡፡ ብራብ አበልችሁኝ፤ ብጠማ አጠጣችሁኝ፤ ብታረዝ አለበሳችሁኝ፤ የሚለው የምጽዋት ዋጋ በቅዱስ መጽሐፍ፣ በብዙ ገድላትና ድርሳናት ጎልቶ ስለተሰበከ ምጽዋትን ለተቸገሩ መስጠት በጠቅላላ የኢትዮጵያውያን ታላቅ መንፈሳዊ እሴት ነው፡፡ ትናንትም ሆነ ዛሬ የማኅበረሰባችን ማኅበራዊ ዋስትና ይኸው ክርስቲያናዊ ባህላችን ነው፡፡ የቀድሞው፣ የዛሬውም የቆሎ ተማሪ የተማረው እና እየተማረ ያለው ቤተ ክርስቲያን በዘረጋችውና በሺሕ በሚቆጠሩ ዓመታት በዘለቀው በዚሁ ተቋም አካል ጽኑ ሃይማኖታዊ ባህል እንጂ በመንግሥት ወይም በሌሎች ድጋፍ አይደለም፡፡ በአጠቃለይ ቤተ ክርስቲያን ለተራቡት ቀለብ፣ ለታረዙት ልብስ፣ ለሕሙማን ፈውስ፣ ለአረጋውያን መጦሪያና ለእጓለምውታን ማሳደጊያ የሆነ ማኅበራዊ ዋስትና ለማረጋጥ በማስተባበር የተቻላትን ሁሉ ስታደርግ ቆይታለች፡፡
እነዚህ መኅበራዊ ተቋማት እንደዘመናችን ዓይነት መዋቅር ባይኖራቸውም በስንበቴና በጡት ልጅ እና በመሳሰሉት ማኅበራዊ መጠሪያዎች የሚታወቁ ማኅበራዊ ዋስትናዎች ነበሩ፡፡ ዘመናዊ የማኀበራዊ ዋስትና በኢትዮጵያ እሰከሚጀመርበት ድረስ ጧሪ የሌላቸው ሰዎች እና አሳዳጊ ያጡ ሕፃናት በዚህ መንገድ ሲረዱ ኑረዋል፡፡
እነዚህ ተቋማት ከተመሠረቱም በኋላ ቤተ ክትስቲያን አዲሶቹን ተቋማት መሥርታ የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎቷን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡
በድርቅ ጊዜ ርዳታን በማስተባበር ስደተኞችን መርዳት
ቤተ ክርስቲያን የተቸገሩትን መርዳት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባሯ በመሆኑ ተግባሩን ስታከናውነው ኖራለች፡፡ ዛሬም በዘመናዊ መልክ ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን በማቋቋም ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት እህል ዘይት እና ሌሎች ምግቦችን በማቅረብ የሰብአዊ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ተግባር አከናውናለች እያከናወነችም ትገኛለች፡፡
መንፈሳዊ ማኀበራትን መደራጀት
ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምሳሌ የሚሆኑ ዝክሮች፣ ሰንበቴዎችና ማኅበሮች ወዘተ በስፋት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የተቀደሱና ጠናካራ ትውፊቶች የበጎ አገልግሎት ለመሰጠት አመቺ ናቸው፡፡ በገጠሩ አካባቢ በስፋት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በድንገት ሀብት ንብረቱ ቢቃጠልበት ርዳታ ያደርጉለታል፡፡ እንዲሁም ጧሪ ዘመድ ሳይኖረውና የሚሠራ ጉልበቱ ሲደክም ከቤታቸው በማስቀመጥ ተፈራርቀው የጦሩታል፡፡ ይህም ተግባር መጽሐፍ ቅድሳዊ ተግባር በመሆኑ በሕዝቡ አኗኗር ላይ በጎ ተጽዕኖ በማሳደሩ ለዚህ ድርጊት የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ክፍተኛ ነው ::

፪ መልካም ዜጋን በማፍራት

ሰው ሁሉ ለሚኖርባት ዓለም ነጻና ክቡር ዜጋ ነው፡፡ዜግነት የተፈጥሮ ሲሆን መልካም ዜግት ግን የመልም ጠባይና ምግባር ውጤት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛና ቅድስት በመሆኗ ዜጎች ሁሉ በሃይማኖትና በምግባር ለሀገራቸውና ለሰማያዊት ርስታቸው መልካምና ታማኝ እንዲሆኑ ከማስተማርና ከመምከር የተቆጠበችበት አፍታ ጊዜ የለም፡፡ ምንም እንኳን በሥልጣኔ ስም የሚመጡ ጉዳዮች የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ ቢፈታተኑትም ቤተክርስቲያን ግን ከጥንት ጀምሮ ልጆቿ በሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው የሀገርና የወገን አለኝታዎች እንዲሆኑ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርታለች፡፡

፫ የሥራ ባህልን በማዳበር

ሥራ የኑሮ መሠረት መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡የምትመራባቸው ቅዱሳት መጻሕፍትም የሥራን ጠቃሚነት በስፋት የሚተነትኑና የሥራን ባህል የሚያዳብሩ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአባታችን አዳም ገነትን ያበጃት ይጠብቃትም ዘንድ ሓላፊነትን ሰጥቶት ነበር፡፡ አዳም ከተሳሳተም በኋላ ጥሮ ግሮ በወዙ እንዲበላ፣ በስንፍና ተዘልሎ እንዳየቀመጥ፣ በወገኖቹ ላይ ጥገኛ ሆኖ እንዳይከብድባቸው ይልቁንም የድካሙን ፍሬ ቢመገብ መልካም እንደሚሆንለት ተነግሮታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት መሠረት በማድረግ ልጆቿ ዘወትር በሥራ የተጠመዱ እንዲሆኑ ይህ ካልሆነ ግን አእምሮአቸው የዲያብሎስ ተገዥ እንደሚሆን ታሰተምራለች፡፡ ከዚህ አኳያ ቤተ ክርስቲያን የሕዝቡን ሁለንተናዊ እድገት በማጽናት ለኢኮኖሚ ጤናማ እድገት፣ ለሕዝቡ ልማትና ደኅንነት መጠበቅ የበኩሏን ድረሻ እየተወጣች ነው፡፡

፬∙ሥነምግባርን በማሰተማር

ሥነምግባር የሚለው ቃል በሥራ ማማር፣ የሥራ መልካምነት ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ክርሰቲያኖች በጎ ሥራን እንዲሠሩ፣ ሰዎችን ያለምንም ልዩነት እንዲወዱ፣ የራስን ሰውነት ሕይወትና ክብር ከሚጎዱ ዲርጊቶች እንዲረቁ ሕይወታቸውን በቅድስና መንፈሳቸውን በንጽሕና እዲያዙ ታሰተምራለች፡፡ ከዚህም ትምህርቷ የተነሣ ምእመኖቿ በጎ ሕሊና እንዲኖራቸው፣ ከአንደበታቸው መልካም ቃል እንዲወጣ ንግግራቸው ሁሉ ከቁጣና ከትዕቢት የራቀ ጠብን ከመጫር ይልቅ ሰላምና እርቅ አንድነት እንዲያወርድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ከእርሱ ጋር ሊያኖር የሚችል መልካም ሥራን መሥራትን የሚፈልጉ እንዲሆኑ አድረጋለች፤ እያደረገችም ነው፡፡ በማኅበራዊ ሕይወትም የሌላውን ድካምና ስሕተት ለቅመው ከመክሰስና ከመተቸት ይልቅ ባለማወቅ ያጠፋነውን ወደ ማወቅ አድርሰው ያርሙታል፣ የደከመውን ያበረቱታል፡፡ ክፉውን ወደ መልካም ይለውጡታል፡፡ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት የተገለጠ ሰለሆነ በኅብረተሰቡም ፊት መልካም የሆነውን የፈጽማሉ፡፡ ‘’ስለምናገለግለው ስለዚህ ለጋስ ስጦታው ማነም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ  ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና’’ ፡፡ በአጠቃለይ ቤተ ክርስቲያን ባላት የሥነ ምግባር ትምህርቷ ኅብረተሰቡ ለእግዚአብሔር እንዲሁም ለሀገሩና ለባልንጀራው ታማኝ እንዲሆንና ሓላፊነቱን፤ ተጠያቂነቱን በአግባቡ እንዲወጣ፤ ያለ እድልዎ ሥራን እንዲያከናውን በማሰተማር ሙስናን በመከላል ለሀገር ዕድገት አስተዋጽኦ ስታበረክት ቆይታለች እያበረከተችም ትገኛለች፡፡
ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ፤ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ፤መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡ በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ መሠረት ቤተ ክርስቲያን የእንግዚአብሔር የሆነውን አሥራት በኩራት ለቤተክርሰቲያን ግብርን ደግሞ ለመንግሥት በወቅቱ እንዲከፍሉ ለማድረግ የማይናቅ ድርሻ ተወጥታለች፡፡ ይህን ማለት የሚያሰደፍረውም፡-

 • አስተምህሮዋ አንዱ ለአንዱ እንዲታዘዝ፤ በትሕትና እንዲኖሩ ፈረሃ እግዚአብሔር እንዲኖረው ከሱስ ከባዕድ ተግባር ራሱን እንዲጠብቅ እና መልካም ዜጋ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ ነው፡፡
 • ለረጅም ዘመናት በቄስ ትምህርት ቤት ትውልድን በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ለሓላፊነት የሚበቃ እና ጠንካራ ዜጋ ለምድረግ ከሥር ኮትኩታ በማስደግ ያደረገችው እሰተዋኦም የሚዘነጋ አይደለም፡፡
 • እሰከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የግብረ ገብ ትምህርት ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን እንዲሰጥና በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎች እንዲኖሩ ያደረገችው አሰተዋኦ  ከፍተኛ ነው፡፡

በተለይም በዚህ በዘመነ ሉላዊነት /Globalization/ በተለያየ መልኩ የሥነ ምብናር ችግር እየገጠመው ያለውን ትውልድ፣ በተሻለ መለኩ ለመቅረጽ መንግሥት በኮሚሽን ደረጃ አቋቁም የሚታገልበትን ሙስና ከሥሩ የሚነቅል ሥራ ለመሥራት ቤት ክርስቲያን ካለባት ሓላፊነት አኳያ እያደረገችው ያለው ትውልድን በሥነ ምብባር የማነጽ ሥራ የሃይማኖቱ ግዴታ እንደሆነ ያመለክታል፡፡

፭∙ በጤና ጥበቃ ዘርፍ በመሳተፍ

ጤና ማለት የበሽታ አለመኖር ብቻ ሳይሆን የአንድ ሰው /ማኅበረሰብ/፣ አካላዊ /physical/፣ ሥነ ልቡናዊ /psychological/ ማኀበረሰባዊ /social/ አእምሮአዊ /mental/ እና ሃይማኖታዊ ደኅንነት / Spritual wellbeing /  ነው፡፡ አስከፊ በሆነ ድህነትና ችግር ውስጥ ላለ ኅብረተሰብ የጤና ችግር ትልቁን ቦታ የሚይዝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ከሥጋ ሕመም ባሻገር የሚፈጥረው የአእምሮ ጭንቀት የአንድ ኀብረተሰብ ክፍልን ምርታማነትና ውጤታማነት እጅጉን ይጎዳል፡፡ ቤተ ክፍስቲያን የጤናውን ችግር ለመቅረፍ ያላትን አስተዋጽኦ የሚከተሉትን መዘርዘር/መጥቀስ ይቻላል፡፡

 • መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ደኀንነትን በመስጠት
 • አዕምሮአዊ ጤንነት እንዲኖር በማድረግ
 • ሥነ ልቡናዊ ጤንነት በመስጠት
 • ዘመናዊ ጤና ተቋማት ማስፋፋትና የመሳሰሉትን  

፮∙ በትምህርት ዘርፍ 

ባለአእምሮ ሰው በደማዊነት አእምሮው እያዘገመ እንዳይኖር በትምህርት ድንቁርናን አርቆ፣ ክፉና ደጉን ለይቶ በዕውቀት ዓለም እንዲኖር ልቡናን የሚያጠራና የሚወለውል፣ ማኅበራዊ ነጻነትን የሚጎናጽፍ ዕውቀት ማግኘት ያስፈልገዋል፡፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ ዕውቀት በሰው ልጆች አእምሮ ተቀርጾ ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚዊ ሕይወታቸውን ጥበብ በተሞላበት የአኗኗር ዘይቤ እንዲመሩ የዕውቀት በር መክፈቻ ቁልፍ ነው፡፡

የዚህም ዓላማ፣

ጊዜውን የሚዋጅ ንቃተ ኅሊናው የዳበረ ትውልድ ወይም ዜጋ ለመፍጠር ከቄስ ትምህርት ቤት እስከ ከፍተኛ ተቋማት ሥርዓተ ትምህርትን መቅረጽ እና መረጃ መሳሪያዎች ማዘጋጀት የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ ፊደልን ከነአገባቡ ይዛ የዓለም የራሳቸው ፊደላት ካሏቸው ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን መገለጫዋም የግእዝ ፊደላት ባለቤት መሆኗ ነው፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ውጭ ሀገራት የግእዝ ትምህርት በፋኩልቲ ደረጃ መቋቋም ለጥናትና ምርምር ዓይነተኛ እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ዘመናዊ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ከ1930ዎቹ በኋላ እንደ ትምህርት ሚኒስቴርነ ስታገለግል የቆየችው ቤተ ክርስቲያን የዘመናዊ ትምህርት ቤት በሀገራችን መስፋፋት ከጀመረበት ጊዜ በኋላም ቢሆን የራሷ ዘመናዊ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ልጆችና ወጣቶች በሥነ ምግባር እየታነጹ፤ ለሕዝብና ለመንግስት የሚያገለግል አገር ወዳድ ዜጎችን በማፍራት በዘማናዊው ትምህርት ድርሻዋን እየተወጣች ትገኛለች፡፡

፯. ታረክን እና ጥበብን በመመዝገብ

ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ መነሻው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ ብዙው ዓለም ገና የጽሕፈትን ጥበብ ገንዘብ ባላደረገበት ዘመን የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ከበግ፣ ከፍየልና ከልዩ ልዩ እንሰሳት ቆዳ ብራና ፍቀው፣ ቀለማትን በጥብጠው ብርዕ ቀርጸው የኢትዮጵያ ብሎም የውጭ ሀገራትን ታሪክ በመመዝገብ ለጥናትና ምርምር መነሻ ሆነዋል ማለት ይቻላል፡፡

፰.  የባህል አስተዋጽኦ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን መሰረቷ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ የምትሰብከውም ሃይማኖትን ከትውፊት፣ ትውፊትን ከሥርዓት፣ ሥዓትን ከባህል ጋር በማቀናጅት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲን በሥነ ምግባር ትምህርቷ በኢትዮፕያ ውስጥ ለሚደረግ መልካም ባህሎች መነሻ ናት፡፡ በዚህ መሰረት ቤተ ክርስቲያን ያላትን ባህላዊ አስተዋ    ጽኦ ለመመልከት ያህል እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

 • በአንድ ማዕድ የመመገብ ባህል /የአመጋገብ ሥርዓት/፣
 • የአነጋገር ሥርዓት፣
 • የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣
 • አለባበስ/ ነጭ ልብስ፣ ወንድ የወንድን ሴት የሴት ወ.ዘ.ተ/፣
 • ጋብቻን የማክበር ባህል
 • የጀግንነት እና የሀገር ፍቅር ባህል፣
 • ተከባበሮ የመኖር  እና የአብሮነት ባህል፣ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

 

ሰበካ ጉባኤ እና ዓላማው

ሰበካ ጉባኤ፡- በተለይ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመናዊ መዋቅር ያላት ሆና እንድትተዳደር በተደነገገው ህግ ቃለ ዓዋዲ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው፡፡
ሰበካ ጉባኤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ 5 መሰረት የሚከተሉት አለማዎች አሉት፡፡

 • ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ፤
 • የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ሐዋርያዊ ተግባር ለማደራጀትና እንደዚሁም ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ለማሻሻል፤
 • ምዕመናንን ለማብዛት እንደዚሁም በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ፤
 • የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ለማሻሻልና በማናቸውም ጉዳይ ራሷን ለማስቻል ነው፡፡

                  ከዚህ በተጨማሪ በቃለ ዓወዲው አንቀጽ 6 ላይ ሰበካ ጉባኤው የሚከተሉትን ተግባራት እንደሚያከናውን ተደንግጎ ይገኛል፡፡

 • የእግዚአብሔርን ወንጌል መንግስት ለመስበክና ትምህርቱንም ለማስፋፋት፤
 • መንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርት ቤትን ለማቋቋምና ለማደራጅት፤
 • መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎትን ለምዕመናን ሁሉ ለማደረስ፤
 • ሰንበት ትምህርት ቤትን ለማቋቋምና ለማጠናክር ፤
 • የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ለምዕመናን ሁሉ ለማድረስ፤
 • ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ሁሉ ለማሟላት፤
 • የቤተክርስቲያን አስተዳደርና አገልግሎት በቅዱሳት መጻህፍት መሰረት በህግና በሥነ-ሥርዓት ለመምራት፤
 • ቤተ ክርስቲያንን በሀብትና በንብረት በኩል ራሷን ለማስቻል፤
 • የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት እዳይባክን፣ እየተመዘገበ እንዲጠበቅ፣ እንዲለማና እንዲያድግ ለማድረግ፣
 • ህገ ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው መሰረት ከበላይ የሚሰጡትን ህግጋት፣ ደንቦች፣ መመሪዎች፣ ትዕዛዞችና ውሳኔዎች ለመፍጸምና ለማስፈጸም፤
 • በቅርብም ሆነ በሩቅ የሚገኙ ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት በማናቸውም ጉዳይ እርስ በእርሳቸው ተባብረውና ተረዳድተው እንዲሰሩ የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ፣
 • ልዩ ልዩ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን ለማቋቋምና አገልግሎታቸውን ለማሟላት፣
 • የህንፃ ሥራ፣ እድሳት፣ ጥገናና የመሳሰሉት ሥራዎች ሁሉ ወቅቱን ጠብቀው የሚፈጸሙበት እቅድና መርሃ ግብር ማዘጋጀት በተግባር መዋላቸውንም ለመቆጣጠር፣
 • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችን ብዛት ፣የሰበካውን ገንዘብና ንብረት ገቢና ወጪ የመሳሰሉትንም እስታቲስቲካዊ መረጃዎችን በወቅቱ እየመዘገቡ በሪፖርት እንዲገለጽ ለማድረግ፤
 • በዚህ ቃለ ዓዋዲ መሰረት ማናቸውንም ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም፤
 • በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ 4 እስከ 14 የተዘረዘሩትን ተግባሮች በቅድሚያ እያጠና ተገቢውን ለማድረግና አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር እየተነጋገረ ለማስፈጸም፡፡

አስተዳደራዊ መዋቅር (አደረጃጀት)

{gallery}pic-orgstructure{/gallery}

አስተዳደራዊ መዋቅር (አደረጃጀት)

ሀገረስብከቱበሊቀጳጳስየሚመራሲሆንከዚህቀጥሎያሉትካላትይኖሩታል
1.    ሊቀጳጳስ ፡-ጠቅላላየሀገረስብከቱንአስተዳደርበኃላፊነትይመራል፤በሀገረስብከቱሥርለሚገኙካህናትናምዕመናንአባታዊቡራኬይሰጣል፤የቤተክርስቲያኒቱእምነትእንዲስፋፋየተቻለውንሁሉያደርጋል    

2.    ሥራአስኪያጅ
ሊቀጳጳሱበሌሉበትጊዜአስተዳደርጉባኤውንይመራል፣የቅዱስሲኖዶስመመሪያዎችንለሚመለከታቸውያስተላልፋል፣ የጽ/ቤቱንሥራይመራል፣ ያስተባብራል፣በሀገረስብከቱሲፈቀድሠራተኛይቀጥራል፣የሀገረስብከቱንየመጻጻፍሥራዎችይሠራል፣ጽ/ቤቱንወክሎከልዩልዩአካላትጋርይጻጻፋል፣ የሀገረስብከቱንዕቅድከየመምሪያዎችጋርበመሆንያዘጋጃል፣አፈጻጸሙንምይከታተላል፣የሲሦ፣መንፈቀዓመትእናየዓመትሪፖርትያቀርባል፣

3.    የስብከተወንጌልእናሐዋርያዊአገልግሎትመምሪያ  
ስብከተወንጌልንማስፋፋት፣መምህራንንማሠልጠን፣መምህራንንመመደብ፣የማስተማርያመሣርያዎችንማዘጋጀት፣ሐዋርያዊጉዞዎችንማዘጋጀት፣ጉባኤያትንማቀናጀትእንዲሁምመቀራረቢያመንገዶችእያዘጋጀወደእናትቤተክርስቲያንየሚመጡበትንመንገድማመቻቸት፤ዋናዋናተግባራቱናቸው፡፡
4.    የሰንበትትምህርትቤትመምሪያ
 ሰንበት ት/ቤቶችንማደራጀት፣የተደራጁትንበሕገቤተክርስቲያንመምራት፣ለወጣቶችመንፈሳዊሕይወትመጎልበትየሚረዱልዩልዩተግባራትንማከናወን፣ወጣቶችየሚዘምሩትንመዝሙርወጥነትእንዲኖረውማድረግ፣ወጣቶችየቤተክርስቲያንንየአብነትትምህርትተምረውወደክህነትእንዲቀርቡማድረግ፣እንዲሁለሕጻናትየሚሆኑፕሮግራሞችንማዘጋጀት፤የመማርያመሣርያዎችንማዘጋጀት፣ ሕፃናትሃይማኖታቸውንእንዲማሩ፤የሀገራቸውንቋንቋ፣ባሕልአውቀውእንዲያድጉሁኔታዎችንማመቻቸት፤እናቶችበቤተክርስቲያንአገልግሎትተገቢውንእንዲፈጽሙሁኔታዎችንማመቻቸትዋናዋናተግባራቱናቸው
5.    የፋይናንስእናበጀትመምሪያ
የገንዘብአገባብአወጣጥንእናመከታተል፤ የአብያተክርስቲያናትንመዋጮመሰብሰብ፣የገቢመንገዶችንመተለም፤  የተለያዩክፍያዎችንበሒሳብበህጉመሠረትመፈጸምናማከናወንዋናዋናተግባራቱናቸው      
6.    ቅርሳቅርስመምሪያ
ዐውደርእይማዘጋጀት፣ቋሚዐውደርእይመክፈት፣ጎብኝዎችኢትዮጵያንእናቤተክርስቲያንንእንዲጎበኙማበረታታትእናመንገድማመቻቸት፣ የየአብያተክርስቲያናቱታሪክእናቅርስእንዲመዘገብእናእንዲጠበቅማድረግ፤ዓመታዊበዓላትን፣ፌስቲቫሎችን ፣እናሌሎችባሕላዊዝግጅቶችንማዘጋጀት
7.    የሕግመምሪያ  ቤተክርስቲያንንበተመለከተለሚነሡየሕግጉዳዮችአስፈላጊውንማከናወን፤ ቤተክርስቲያንበሕግመብቷእንዲጠበቅማድረግ፣ የቤተክርስቲያንደንቦችእናሕጎችንከሀገሪቱሕጎችጋርማጣጣም
8.    ቁጥጥርመምሪያ፡-  ይህክፍልከተለያየአቅጣጫየተሰበሰበገንዘብናልዩልዩየሀገረስብከቱንብረትበአግባቡተመዝግቦበትክክልገቢናወጪመሆኑንየሚከታተልክፍልነው፡፡
9.    ገንዘብቤት፡- ይህክፍልከልዩልዩገቢዎችየተገኘውንገንዘብከሒሳብክፍልበሚሰጠውሰነድመሠረትአገናዝቦገንዘቡንባንክየሚያስገባእንዲሁምየሰራተኛደሞወዝናልዩልዩወጪችበሚመለከታቸውአካላትሲፈቀድከባንክገንዘብአውጥቶየሚከፍልነው፡፡
10.    ምግባረሠናይመምሪያ፡-ይህክፍልየተለያዩበጎአድራጊግለሰዎችንናድርጅቶችንኢያስተባበረችግረኞችንየሚረዳክፍልነው፡፡
11.    ንብረትክፍል፡- ይህክፍልበስጦታየሚገኘውንናበፊትየነበረውንንብረትየሚጠብቅ፣ ለወደፊትምየገንዘብምንጭየሚገኝበትንመንገድበሰፊውየሚያጠናናየተገኘውንምንብረትበአግባቡየሚጠብቅናየሚቆጣጠርክፍልነው፡፡
12.    የካህናትአስተዳደርመምሪያ፡- ይህክፍልክህነትነክያላቸውንጉዳዮችየሚመለከትናአገልግሎትየሚሰጥሲሆንታላላቅበዓላትእናየመሳሰሉትንጊዜውንጠብቆፕሮግራምበማውጣትካህናቱንየሚመራክፍልነው፡፡
13.    የሰበካጉበኤመምሪያ፡-ይህክፍልበቃለዓዋዲውመሠረትበጥቢያበተክርስቲያንሰበካጉባኤእንዲቋቋምናእንዲጠናከርከሚመለከታቸውአካላትጋርበመሆንየሚሠራክፍልነው፡፡
14.    ሪከርድናማህደርክፍል፡-ይህክፍልገቢናወጭደብዳቤዎችንእንዲሁምታሪካዊየሆኑሰነዶችንበጥንቃቄየሚይዝክፍልነው፡፡
15.    ጠቅላላአገልግሎትክፍል፡-
16.    የወረዳቤተክህነት፡- በሊቃነካህናትመሪነትየሚመራሲሆንዓላማቸውምበአንድየቅርብአካባቢያለውንአገልግሎትየሚያስተባብሩየሚመሩናቸው፡፡

የሀገረስብከቱ ሰራተኞች

{gallery}pic-diocese{/gallery}

የገዳማትና አድባራት ዝርዝር

ተ.ቁ የቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ ስም የቤተ ክርስቲያኑ መጠሪያ ሥም ቤተ ክርስቲያኑ የተመሰረተበት ዘመን ቤተክርስቲኑ የሚገኝበት አቅጣጫ /ወረዳ የቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ/አስተካይ ሙሉ ስም
1 ቀራንዮ ምድኃኒያለም  ደብር  1826 ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ምዕራብ  ሣህለሥላሴ የዳግማዊ ምኒሊክ አያት 
2 ሳሎ ደብረ ፀሀይ ቅ/ጊዮርጊስ /ቃሊቲ/ ደብር 1827 አቃቂ ክ/ከተማ ደቡብ ሣህለ ሥላሴ
3 ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሀይ እንጦጦ ማርያም ደብር  1873 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ዳግማዊ ሚኒሊክ 
4 ደብረ ጽጌ ቅድስ ዑራኤል ደብር  1875 ምስራቅ  ዳግማዊ ሚኒሊክ
5 ደብረ ኃይል ራጉኤል  ደብር  1877 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ዳግማዊ ሚኒሊክ
6 ጽርሃ አርያም ቅ/ሩፋኤል ደብር 1878 ጉለሌ ክ/ከተማ ምዕራብ ዳግማዊ ሚኒሊክ
7 ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ  ደብር 1869 አራዳ ክ/ከተማ አራዳ መሀል  ዳግማዊ ሚኒሊክ
8 ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክ /መካነ ሥለሴ ደብር 1883 አራዳ ክ/ከተማ ማዕከላዊ ዳግማዊ ሚኒሊክ
9 መንበረ መንግስት ቅ/ገብርኤል /ግቢ/ ደብር 1889 መሀል አ.አ ማዕከላዊ ዳግማዊ  ምኒሊክ
10 ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ደብረ አሚን ተክለኃማኖት ደብር 1898 ምዕራብ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ
11 መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ደብር 1899 ቂርቆስ ክ/ከተማ ደቡብ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ
12 ብርሃናተ ዓለም ጴትሮስ ወጳውሎስ  ደብር 1901 ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ምዕራብ ዳግማዊ ሚኒሊክ
13 ሐመረ ኖህ ኪዳነምህረት ገዳም 1903 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ግርማዊት እትጌ ጣይቱ
14 ደብረ ሠላም ቀጨኔ መድኃኒዓለም ደብር 1903 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ልጅ እያሱ
15 ደብረ ገሊላ አማኑኤል  ዳቴድራል  1905 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምዕራብ  ዳግማ አፄ ሚኒልክ
16 መካነ ሕይወት ገብረ ምንፈስ ቅዱስ  ደብር 1905 የካ ክ/ከተማ ሰሜን አፈንጉሥ ጥላሁን
 17 ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ደብር 1909 ቂርቆስ ክ/ከተማ ደቡብ ዳግማዊ ሚኒሊክ
18 ታዕካ ነገሥት በዓታ ማርያም ገዳም  1911 አራዳ ክ/ከተማ ምስራቅ ንግሥት ዘውዲቱ
19 ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ደብር 1910 ደቡብ ሰብዮን ኃ/ማርያም
20 ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ደብር 1950 አራዳ ክ/ከተማ ምዕራብ አፄ ኃ/ሥላሴ
21 ገነተ ኢየሱስ ገዳም 1915 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ልዑል ራስ ካሳ
22 መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ገዳም  1916 አራዳ ክ/ከተማ ሰሜን  አፄ ኃ/ሥለሴ
23 ማኅደረ ስብሐት ልደታ ደብር 1916 ልደታ ክ/ከተማ ደቡብ ብፁዕ አቡነ ሣዊሮስ
24 መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም ደብር 1919 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ንግሥት ዘውዲቱ
25 ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤለ /የካ/ ደብር 1823 የካ/ክ/ከተማ ምስራቅ የጥንቱ በአፄ ምኒሊክ ዳግማዊ የአሁኑ በንግስት ዘውዲቱ 
26 መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም 1922 አራዳ ክ/ከተማ ማዕከላዊ  ብፁዕ አቡነ ቂርሎስ 
27 መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካሬድራል 1924 አራዳ ክ/ከተማ ማዕከላዊ በቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ
28 ጸርሃ ንግሥት ፉሪ ሃና ማርያም ደብር 1926 ደቡብ ግርማዊት እግቴ መነን
29 ጽርሐ ፅዮን ሐዋርያት ቅዱስ ሚካኤል /ጎላ/ ደብር  1934 አራዳ ክ/ከተማ ማዕካላዊ  ወ/ሮ በቀለች ግዛው
30 ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ደብር 1935 ኮልፌ ክ/ከተማ ምዕራብ እቴጌ መነን
31 ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም 1935 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ
32 ረጲ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ደብር 1936 ደቡብ ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸውና ልዕልት ሻሼ ወርቅ
33 መንበረ ስብሐት ሥላሴ /እንጦጦ/ ደብር 1938 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን የቀድሞ አባ ኃ/ሥላሴ መገኑ
34 ደብረ ከዋክብት ገ/ክርስቶስ ወአቡነ አረጋዊ ደብር 1942 ደቡብ  አፄ ኃ/ሥላሴ
35 ደብረ ኃይል ቅ/ራጉኤል ደብር 1948 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደቡብ አፄ ኃ/ሥላሴ
36 ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ደብር 1948 ደቡብ የቀድሞ በወ/ሮ ደስታ ሞላ የአሁኑ በምዕመናን
37 ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል 1953 ምዕራብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፈቃድ በምእመናን 
38 መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል /ጎፋ/ ካሬድራል  1955 ደቡብ በፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ
39 መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ደብር 1955 አቃቂ ክ/ከተማ ደቡብ ዶ/ር በቀለ በየነ
40 ደብረ ብስራት ቅዱስ  ገብርኤል ደብር 1957 ደቡብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስከት ፍቃድ በምእማናን 
41 መካነ ሕይወት ኪዳነ ምህረት /ቃሊቲ/ ደብር 1958 አቃቂ ክ/ከተማ ደቡብ ወ/ሮ አቦነሽ አንበርብር
42 ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤለ /ቦሌ/ ደብር  1968 ቦሌ ክ/ከተማ ምዕራብ በአ/አ/ሀ/ስብከት ፈቃድ በምዕመናን 
43 አንቀፀ ምህረት ቅድስ ሚካኤል /ጭቁኑ/ ደብር  1968 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን  የራስ ካሳ ቤት የድሮ /የአሁኑ በምዕመናን /
44 ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅ/ማርያም ደብር 1969 ቦሌ ክ/ከተማ ምስራቅ በአ.አ ሀገረ ስብከተ ፈቃድ በምዕመናን 
45 ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ  ደብር 1969 ጉለሌ ክ/ከተማ  ››
46 ደብረ ገነት ቅ/ገብርኤል  ካቴድራል 1969 ምዕራብ ››
47 ዳግማዊ ቁልቢ ደብረ ልዑል ቅ/ገብርኤል ደብር 1969 የካ ክ/ከተማ ምዕራብ ››
48 ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ  ደብር  1972 ቦሌ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
49 ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም  ደብር  1972 ቦሌ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
50 ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት ገ/ቅዱስ  ገዳም 1974 ደቡብ ››
51 መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሃና ደብር 1976 የካ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
52 ደብረ ምጥማቅ ፊሊጶስ ደብር 1979 ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ምዕራብ ››
53 ደብረ መንክራት ተክለሃይማኖት ደብር 1979 ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ምዕራብ ››
54 ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር 1981 ደቡብ ››
55 ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል /ላፍቶ/ ደብር 1983 ምስራቅ ››
56 ደብረ ምህረት ኪዳነ ምሕረት ደብር  1983 የካ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
57 ገዳመ ኢየሱስ ገዳም 1983 ደቡብ ››
58 ደብረ ፀሀይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር 1983 ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን  ››
59 ቤዛ ብዙሃን ኪዳነ ምህረት ደብር 1984 ደቡብ ››
60 ደብረ ምፅላል እግዚአብሔር አብ ደብር 1985 ቦሌ ክ/ከተማ ምስረቅ ››
61 አንቀጸ ምህረት ኪዳነ ምህረት ደብር 1985 ደቡብ ››
62 ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ደብር 1985 ደቡብ ››
63 ደብረ ፅባህ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ ደብር 1986 የካ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
64 ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቃሊቲ ደብር 1986 ደቡብ ››
65 ደብረ ዕንቁ ልደታ ማርያም ደብር 1986 የካ ክ/ከተማ ሰሜን ››
66 ደብረ ገነት ፍሪ እንቁ ገብርኤል ደብር 1986 ደቡብ ››
67 ብሔረ ጽጌ ማርያም ደብር 1986 ደቡብ ››
68 ምስራቅ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ደብር 1986 ደቡብ ››
69 ወይቤላ ማርያም ደብር 1987 ምዕራብ ››
70 ደብረ ቅዱስ ደብረ ቀራሜሎስ ካራአሎ መድኃኔዓለም ወአቡነ ገሪማ ደብር 1988 የካ ክ/ከተማ ምስራቅ  ››
71 ሐመረ ወርቅ ማርያም  ደብር 1988 ደቡብ ››
72 ካራ ቆሬ ፋኑኤል ደብር ምዕራብ  ››
73 ደብረ ምህራት ወህኒ ሚካኤል ውጪ ደብር 1989 ››
74 ቦሌ ቡልቡላ ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ደብር 1990 ደቡብ ››
75 አዲስ አምባ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን  ደብር ጉለሌ ክ/ከተማ ደቡብ ››
76 ድልበር መድኃኔዓለም  ቤተክርስቲያን  ደብር ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን  ››
77 ማህበረ በኩር ደብረ አራራት አማኑኤል ገዳም 1988 የካ/ክ/ከተማ ምሥራቅ  ››
78 ቀበና መድኃኔዓለም ደብር 1993 አራዳ ክ/ከተማ ምስራቅ  ››
79 ላምበረት አቡነ አረጋዊ ደብር 1993 የካ ክ/ከተማ ምስራቅ  ››
80 ካራ ሥላሴ ደብር የካ ክ/ከተማ ምስራቅ ››
81 ካራ ምስራቀ ጸሐይ  ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ ደብር ምስራቅ ››
92 ሲኤምሲ ተክለሃይማኖት ደብር ምስራቅ ››
83 ቅድስት ሥላሴ(ሜሪ) ደብር ምስራቅ ››
84 መሪ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደብር ምስራቅ ››
85 መሪ ደብረ ታቦር ፋኑኤል ደብር ምስራቅ ››
86 ሀያት ኪዳነምህረት  ደብር ምስራቅ ››
87 ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ደብር ምስራቅ ››
88 የረር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ደብር ምስራቅ ››
89 ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ኡራኤል ደብር ምስራቅ ››
90 መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ደብር ምስራቅ ››
91 ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ደብር ምስራቅ ››
92 ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ደብር ምስራቅ ››
93 መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ደብር  ምስራቅ ››
94 ኆኅተ ምስራቅ ኪዳነ ምሕረት ደብር  ምስራቅ ››
95 ሎቄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ  ገዳም ምስራቅ ››
96 ደብረ  ገነት ቅዱስ ዑራኤል ደብር ምስራቅ ››
97 ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ምስራቅ ››
98 ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም ደብር ደቡብ ››
99  ጽርሃ አርያም ቅድስት ማርያም ደብር ምስራቅ ››
101 ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል  ደብር  ምስራቅ ››
102 ምስራቅ በር ቅዱስ ጊዮርጊስ  ገዳም ምስራቅ ››
103 መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ደብር ምስራቅ ››
104 ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ምስራቅ ››
105 አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደብር ምስራቅ ››
106 ደብረ ኢያሪኮ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ደብር ምስራቅ ››
107 ደብረ ቤቴል እግዚአብሔር አብ ደብር ምስራቅ ››
108 ወረገኑ ኪዳነ ምሕረት ደብር ምስራቅ ››
109 አያት መድኃኔዓለም ደብር ምስራቅ ››
110 ቤዛዊት ማርያም ደብር ምስራቅ ››
111 መልካ ቆራኒ አቡነ ተክለሃማኖት ደብር ምስራቅ ››
112 ጉለሌ አምባ ደብረ መድኃኒት ኪዳነምህረት ደብር ምዕራብ ››
113 ደብረ ብርሃን ሥላሴ ደብር ምዕራብ ››
114 ደብረ መንክራት ቅ/ጊዮርጊስ ደብር ምዕራብ ››
115 አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ምዕራብ ››
116 ጆሞ ሥላሴ ደብር ደቡብ ››
117 ደብረ ኢዮር ቅ/ሚካኤል ደብር ደቡብ ››
118 ደብረ ራማ ቅ/ገብርኤል ደብር ደቡብ ››
119 ደበረ በረከት ቅ/ገብርኤል ደብር ደቡብ ››
120 ሰፈረ ገነት ሥላሴ ደብር ደቡብ ››
121 ደብረ ጽዮን ቅ/ማርያም ደብር ደቡብ ››
122 ፃድቃኔ ማርያም ደብር ደቡብ ››
123 ፍኖተ ሎዛ ቅ/ማርያም ደብር መዕራብ ››
124 አንፎ ቅ/ዑራኤል ደብር ምዕራብ ››
125 ፈለገ ብርሃን ሥላሴ ደብር ደቡብ  ››
126 ደብረ ኢያሪኮ ምድኃኔዓለም ደብር ደቡብ ››
1127 ደብረ ታር በዓለ ወልድ ደብር ደቡብ ››
128 ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሀንስ ደብር ደቡብ ››
129 ደወለ አይነከርም ኪዳ ምሕረት ደብር  ደቡብ ››
130 እንቁ ገብርኤል  ደብር ደቡብ ››
131 ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ኡራኤል ደብር ደቡብ ››
132 ጋራ ኦዳ ቅዱስ ገብርኤል ደብር ደቡብ ››
133 ምስካበ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ደብር ደቡብ ››
134 በሻሌ ቅድስት ማርያም ደብር ደቡብ ››
135 ቦሌ ለሚ ተክለ ሃይማኖት ደብር ምስራቅ ››
136 አንቆርጫ ቅዱስ ገብርኤል ደብር ምስራቅ ››
137 ሰፈረ ሰላም ዑራኤል ደብር ምስራቅ  ››
138 አቃቂ ፈለገ ጊዮን ቅዱስ ገብርኤል ደብር ደቡብ ››
139 ገላን ጉራ አቃቂ ፈንታ ቅዱስ ሩፋኤል  ደብር ደቡብ ››
140 አበ ብዙሃን አብርሃም  ደብር ደቡብ ››

ቤተ መዛክርት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ማዕከል ብቻ ሳትሆን የምጣኔ ሀብታዊ፤ማህበራዊ፤ሥነ ጥበባዊ፤የሥልጣኔ እና የነገሥታት ገድሎች ዜና መዋዕሎች መረጃ መዕክል ናት፡፡ለምሳሌ ያህል ፡-የኩሱም፤ላሊበላ፤ደብረ ብርሃን ሥላሴ ፤ጣና ሀይቅ እና  የመሳሉትን ከብዙ በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡በአዲስ አበባም ታሪካዊና አስደናቁ የሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች በብዛት የገኛሉ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉም ታሪካዊ ሙዜሞች ቢሆኑም ሙዜዬም  ሠርተው በሙዜየም ደረጃ ከሚያስጎበኙ ገዳማትና አድባራት መካከል፡-

 

 1. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሙዜም፤
 2. የገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሙዜም፤
 3. የርዕስ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም ቤ/ክ ሙዜም ፤
 4. የታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያም ቤ/ክ ሙዜምና ወዘተ መጥቀስ ይቻላል

በእነዚህ ሙዜሞች ወስጥ ደረጃቸውን በጠበቀ በዘመናዊ  አደረጃጀትና ጥበቃ ተይዘው በመጎብኘት ላይ ያሉ በርካታ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ውድና ማራኪ የሆኑ ቅርሶች በዋጋ ሊተመኑና በምንም ሁኔታ ሊተኩ የማይችሉ ናቸው የተሰጡትም ከቀድሞ ነገሥታት፣ ከእቴጌዎቹ፣ ከብፁዓን አባቶች፣ ከቤተ መንግሥት ልዑላንና ልዕልቶች፣ ከቀድሞ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖችና ከ5ቱ አኅት አቢያተ ክርስቲያናትም ጭምር ሲሆን ደኅንነታቸውም ለረጅም ዘመናት በሚባ ተጠብቆላቸው ከዚህ ትውልድ ደርሰዋል፡፡
የተሠሩትም ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስና ከመሳሰሉት ማዕድናት ሲሆን የወርቅና የብር ቅቦችንም ያጠቃልላል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከጥልፍ (ሙካሽ) ሥራ የተዘጋጁ የቤተ መቅደስ አልባሳት፣ ድባብ ጥላዎችና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ይልቁንም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በተለያዩ ጸሐፍትና አርእስት በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ በርካታ ሃይማኖታዊ የብራና ቅዱሳት መጻሕፍትም በእነዚህ ሙዜሞች ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህም ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል በ6ኛው መ/ክፍለ ዘመን በቅ/ያሬድ በ8 የዜማ ምልክቶችና በ3 የዜማ ቅኝቶች ከተደረሱት አምስቱ የዜማ መጻሕፍት ውስጥ አንዱና ከ5ዐዐ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆረጠው ድጓ ተብሎ የሚታወቀው መጽሐፍ በይዘቱም ሆነ በጣዕመ ዜማው በእጅጉ ከሚመስጡትና ከሚያስደንቁት ዋነኛው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ከእነዚህ ከ3ቱ ቅኝቶች ውጭ የሆኑ የዜማ ስልቶች የሏትም አትጠቀምም፡፡ ቅኝቶቹም ዘመን የማይሽራቸው ጊዜ የማይገድባቸውና የማይሰለቹ ሰማያዊ ስጦታዎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመንፈሳዊው ምንጭ የተቀዳ የራሷ የሆነ ፊደል፣ አኃዝ (ቁጥር)፣ ቀናትና አዝማናት መቁጠሪያ (ካላንደር) ያላት በመሆኗ ከሌላው የዓለም ክፍል ይልቅ በዚህ መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበቧ የተለየች ያደርጋታል፡፡

የሙዚየሞቹ ዋና ዓላማ

 

 • ሃይማኖታዊና ታሪካዊ የሆኑትን የቤተክርስቲያን ቅርሶች በሙዚየም ውስጥ በማደራጀት በልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ይዞ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጐብኝዎች በማስጐብኘት የቤተክርስቲያኒቱን ታሪካዊ ገጽታ በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ማድረግ፣
 • እነዚሁ አስደናቂ ታሪኮችንና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን በጥንቃቄ ጠብቆ በመያዝ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡

ከእነዚህም መካከል ለአብነት ያህል በየክፍላቸው መድበን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

1ኛ. ከታሪካዊ ቅርሶች

 

 • የነገሠታቱ የቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክብር ዙፋኖች፣
 • የነገሥታቱ የአርበኝነት አልባሳት፣
 • በሞዛይክ ቅርፅ የተዘጋጀ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ምስል (ፖርትሬት) እና ሌሎችም፣ 

2ኛ. ከሃይማኖታዊ ቅርሶች

 

 • በተለያየ ዲዛይን የተሠሩ መስቀሎች፣
 • ልዩ ልዩ ጽዋዎችና ጻሕሎች ከነእርፈ መስቀሎታቸው፣
 • የተለያዩ ወርቀ ዘቦና የብር ጥልፍ (ሙካሽ) ሥራ ካባዎችና ድባብ ጥላዎች፣
 • የተለያዩ የብራና ቅዱሳት መጻሕፍት ገበታቸው በወርቅና በብር የተለበጡ ጭምር፣
 • ከዕንቀ፣ ከብርና ከሞዛይክ የተሠሩ ቅዱሳት ሥዕላት፣ ሥነ-ስቅለትና የመሳሰሉት ይገኛሉ፣

የሰጭዎቹም ዘርዝር

 

 • ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ከሌሎችም አባቶች፣
 • ከዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ፣
 • ከቀ አፄ ኃይለ ሥላሴ፣
 • ከንግሥት ዘውዲቱ፣
 • ከእቴጌ ጣይቱ፣
 • ከእቴጌ መነን፣
 • ከልዑላትና ከልዕልቶቹ፣
 • ከቀድሞ ቤተ መነግሥት ባለሥልጣናት፣
 • ከበጎ አድራጊ ክርስቲያኖች፣
 • ከአኀት አብያተ ክርስቲያናትና ከሌላም

እነዚህ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ይልቁንም ባለሀብቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ጠብቆና ተንከባክቦ ለቱሪዝም ሴክተሩ እንቅስቃሴ ቢጠቀምባቸው በብዙ መልኩ ከፍ ያለ ሀገራዊ ፋይዳ ይኖራቸዋል እንላለን፡፡ሙሉውን መረጃ ለማግኘት መጥታችሁ ትጐበኙ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን በአክብሮት ትጋብዛችኋለች፡፡

 

yared

ኦሮቶዶክሳዊ ዜማዎችና መዝሙሮች

yared
ኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እና አጼ ገብረመስቀል

የዜማ አጀማመር

በንቡረ ዕድ ኤልያስ አብረሃ

ዜማ ማለት ጣዕም፣ ለዛና ስልት ባለው ተከታታይ ቅንቀና የሚያሰሙት ድምፅ ማለት ነው፤ ወይም በልዩ ልዩ ሥነ ድምፅ ተቀነባብሮ፣ ተደራጅቶና ተስማምቶ ልዩ ስሜትና ተመስጦ ሊሰጥ በሚችል መልኩ የሚያሰሙት ቅንቀና ነው፡፡ ዜማ የተጀመረው በጥንተ ፍጥረት በመላእክት አንደበት ነው፤ መላእክት እንደተፈጠሩ ወዲያውኑ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን በጣዕመ ዜማ አመስግነዋል ኢዮ.38፣6፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ እግዚአብሔር ሰውንና መላእክትን መፍጠሩ ስሙን አመስግነው ክብሩን እንዲወርሱ ነውና በጣዕመ ዜማ ማመስገንን በባሕርያቸው ውስጥ እንደ አንድ መሠረታዊ ፍላጎት አድርጎ ፈጥሮላቸዋል፤ ከዚህም የተነሣ ዜማን የመውደድ ዝንባሌ ተፈጥሮአዊ ሆኖ ይገኛል፤ ዜማን የመውደድ ዝንባሌ በመላእክትና በሰዎች ይበልጥ ጐልቶ ይታይ እንጂ ሕይወት ባላቸው በሌሎች ፍጡራንም በብዛት የሚታይ ነው፤ ለምሳሌ “አዕዋፍ ዘሠናይ ዜማሆሙ” ተብሎ የተመሰከረለትን የአዕዋፍ ዜማ መጥቀስ ይቻላል፤ እንግዲህ ይህንን ሁሉ ስንመለከት የስጦታ ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ፍጡራንን በባሕርያቸው በዜማ የማመስገን ፍላጎትና ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጎ በመፍጠሩ የዜማ መገኛውና ምንጩ እርሱ ራሱ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ በጣዕመ ዜማ ማመስገን በሰማያውያን ፍጡራን ዘንድ የማያቋርጥ መደበኛ ሥራ ነው፤ ራእ.4፣9፣ ኢሳ.6፣2-4፡፡

እንደዚሁም ዜማ በተፈጥሮ የተገኘ ተወዳጅ ስጦታ እንደመሆኑ መጠን ሁሌም የመንፈስ ምግብ ነውና ሰዎች ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ ሲጠቀሙበት ኖሮዋል፤ ዘፍ.4፣21፤ ከዚህም የተነሣ ጣዕሙ፣ ይዘቱና ስልቱ ይለያይ እንደሆነ ነው እንጂ ሰዎች ከተፈጠሩበት ጊዜ አንሥቶ ከጣዕመ ዜማ የተለዩበት ጊዜ የለም፤ በመሆኑም በየትኛውም ክፍለ ዓለም የሚገኝ ሕዝብ የራሱ የሆነ ዜማ አለው፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ዜማ በአምስት ዓይነት ተከፍሎ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፤ እነዚህም፡-

 

 1. እግዚአብሔር የሚመሰገንበት መንፈሳዊ ዜማ /ማህሌት/
 2. ሕዝብ በደስታ ጊዜ የሚጠቀምበት የደስታ ዜማ /ዘፈን/
 3. ሕዝብ በኀዘን ጊዜ የሚጠቀምበት የኀዘን ዜማ /ልቅሶ/
 4. ነዳያን በችግር ጊዜ የሚለምኑበት የልመና ዜማ /ልመና/
 5. በሰልፍ ጊዜ ለመቀስቀሻ የሚጠቀሙበት የፉከራ ዜማ /ቀረርቶ/ ናቸው፡፡

ዜማ ለእነዚህ ሁሉ የጋራ መጠርያቸው ነው፤ ሆኖም የዜማዎቹ ድምፀ ቃና፣ ሥነ ቃልና እንቅስቃሴ የአንዱ ከሌላው የተለያዩ ናቸው፡፡ እንግዲህ ስለ ዜማ አጀማመርና አመጣጥ በአጭሩ ይህን ያህል ካልን በኋላ የዚህ ጽሑፍ ዋና ርእስ ወደሆነው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ጸዋትወ ዜማ” ወደሚለው ዝርዝር ገለጻ እንገባለን፡፡

1.    ቅድመ ክርስትና የነበረ ዜማ

በሊቀ ሥዩማን ራደ አስረስ

የኢትዮጵያ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ከአምልኮተ እግዚአብሔር የተለዩበት ጊዜ የለም፤ በመሆኑም ዜማ ተፈጥሮአዊ ስጦታ እንደመሆኑ መጠን በተፈጥሮ ያገኙትና የራሳቸው የሆነ የእግዚአብሔር ማመስገኛ ጣዕመ ዜማ አልነበራቸውም ማለት አይቻልም፡፡

ኦሪት ገና ወደኢትየጵያ ከመግባቱ በፊት ስብሐተ እግዚአብሔር፣ አምልኮተ እግዚአብሔርና ፈሪሀሃ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ እንደነበረ ይታወቃል፤ አምልኮት ካለ ምስጋና አለ፤ ምስጋናም ካለ ዜማም አብሮ አለ፤ ከዚህ ሁኔታ ስንመለከት ከሕገ ኦሪት መምጣት በፊት በኢትዮጵያ በዜማ ማመስገን ነበረ ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህም በኋላ በኢትዮጵያ ዘመነ አበው አልፎ ዘመነ ኦሪት ሲተካና በቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን ታቦተ ጽዮንና ሌዋውያን ሲመጡ የመዝሙራት መጻሕፍት አብረው ስለመጡ የዜማው መልክ በመሣርያ፣ በዓይነትና በአጠቃቀም ተጨማሪ መልክ መያዙ አልቀረም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ /መዝ.150፣1-5፣ ዜና መዋ.ቀዳ.15፣16፤ 16፣4-37/ እንደሚያስረዳው በዳዊትና በሰሎሞን ጊዜ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በከበሮ፣ በጸናጽል፣ በመሰንቆ፣ በበገና፣ በዕንዚራ፣ በቀንደ መለከት፣ በዕልልታና በሆታ እግዚአብሔር በዜማ ይመሰገን እንደነበረ ነው፡፡

ይህ ዓይነቱ ምስጋናና የምስጋና መሣርያ በዋነኛነት ይጠቀሙ የነበሩ የታቦተ ጽዮን አገልጋዮች የነበሩ ሌዋውያን ካህናት መሆናቸውንም መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል /ዕዝ.3፡10/፡፡
በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሌዋውያንም አብረው ስለመጡ ዜማቸው፤ ማሌታቸውና የማሌት መሣርያቸው ሁሉ በዚያን ጊዜ አብሮ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶአል፤ አገሪቱም ይህንን የዜማ ስልት ከነመሣርያው እስከ ዘመነ ክርስትና ስትገለገልበት ቈይታለች፤ የዚህ ዓይነቱ ጣዕመ ዜማ አገልጋዮችም ታቦተ ጽዮን በምትኖርበት ድንኳን ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት ያለማቋረጥ የሚያገለግሉ ስለነበሩ “ካህናተ ደብተራ” ይባላሉ፤ ትርጓሜውም ታቦተ ጽዮን በምትኖርበት ድንኳን ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት ማለት ነው፤ ይህ ስም ከጥንት ጀምሮ የቈየ የመዓርግ ወይም የሙያ ስም ነው፤ ስያሜው እስከ ቅርብ ጊዜ ትልቅ የመዓርግ ስም ሆኖ ለቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ይሰጥ ስለነበረ ሊቃውንቱ ደብተራ እገሌ እየተባሉ ይጠሩበት ነበር፡፡
እነዚህ በዘመነ ኦሪት የመጡ የዜማ መሣርያዎች፣ አለባበሶችና የመዝሙር አጠቃቀም ስልቶች እስከዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ስትገለገልባቸው ትገኛለች፡፡

ለምሳሌ ከዜማ መሣርያዎች መካከል፡- ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መለከት፣ መሰንቆ፣ በገና ወዘተ ይገኙበታል መዝ.150፣1-5፤ ከአለባበስም ረጅም ቀሚስ፣ ጥምጥም፣ መጐናጸፊያ /ጋቢ/ እና ካባ ወዘተ ይገኙባቸዋል ዘሌ.8፣7-9 ፡፡

ከመዝሙር ስልት ደግሞ የቅዱስ ያሬድ የምዕራፍ ዜማ ምዕዛል ስልት ይገኝበታል ዕዝ.3፣11፡፡

2. ዜማ በክርስትና ምሥረታ ጊዜ፡-

ኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመርያ አካባቢ የክርስትና ሃይማኖትን በብሔራዊ ደረጃ ስትቀበል ለምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ማስፈጸምያ የሚሆን ክርስቲያናዊ ዜማ ነበራት፤ ይህ ዜማ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት እንደሚታየው ለአገልግሎት ማስፈጸሚያ ያህል በመጠኑ ያገለግል የነበረ ዜማ እንጂ እንደ አሁኑ ጥልቀት፣ ምጥቀትና ርቀት ያለው፣ የተደራጀና የተቀነባበረ ዜማ አልነበረም፤ ከ330 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ አምስት መቶ ዐርባ ዓ.ም. በዚሁ ዜማ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሲሰጡ፣ እግዚአብሔርም ሲመሰገን ኖሮአል፤ ከአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ግን እግዚአብሔር ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሰዎች በፊቱ ይሰግዳሉ /መዝ.71፣9/ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ታደርሳለች /መዝ.67፣31/ ሲል በዳዊት አንደበት የመሰከረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖትና አምልኮተ እግዚአብሔር በልዩ ጣዕመ ዜማ እንዲታጀብ በመፈለጉ ከአኲስም ጽዮን ካህናተ ደብተራ መካከል አንዱን ካህን ለታላቅ ሰማያዊ ጣዕመ ዜማ መገለጥ መረጠ “ቅዱስ ያሬድ”፡፡