• ”ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኩሉ አጽናፈ ዓለም ” ማቴ 28፤19

  • "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በኩል ሲካሄድ በቆየው በ39ኛው አገር አቀፍ ስምሪት ላይ በችግሮችና በመፍትሔዎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

በቀን 23/2013 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ የመ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን፣ የመ/ፓ/ጠቅላይ […]

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት እየተሰጠ የቆየው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ!!

መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ሥር ለሚገኙ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች በክፍለ ከተማው የትምህርትና ስልጠና ክፍል አስተባባነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብሰባ አዳራሽ ለሁለት ቀናት እየተሰጠ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ መመሪያ ሰጭነት በዛሬው ተጠናቋል፡፡በዕለቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበብ ምናሴ ወልደ ሐና […]

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና ክፍል አስተባባነት በክፍለ ከተማው ሥር ለሚገኙ አገልጋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተሰጠ!!

መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም የክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅ መ/ብ ሩፋኤል የማነ ብርሃንን ጨምሮ የክፍለ ከተማው እና የገዳማትና አድባራቱ ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብሰባ አዳራሽ በሁለት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡የስልጠና መርሐግብሩን በጸሎት የከፈቱትየአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እንደዚህ ዓይነቱ የመተናነፅና እርስ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሰባቱም ክፍላተ ከተሞች ሲካሄድ የነበረው የ39ኛው የሰበካ ጉባኤ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ!!!

መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል አዘጋጅነትና በሰባቱ ክፍላተ ከተሞች አስተባባሪነት በሁሉም ክፍላተ ከተሞቹ ለሰባት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኘውን የCovid-19 በሽታ ለመግታት የወጣውን መመሪያ መሠረት በማድረግ በክፍለ ከተማው ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት የሥራ […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች በቪድዮ ኮንፈረንስ የታገዘ የቴክኖሎጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ!!

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማ፣ የሀገረ ስብከቱና የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ቴክኖሎጅ ተኮር ግንዛቤ ማስጠበጫ በቪድዮ ኮንፈረንስ (video conference) በመታገዝ ተሰጥቷል፡፡የቪድዮ ኮንፈረንስ ሥልጠናውን የሰጡት በኖርዌይ ሀገር የሚገኘው የተክሌ ኮንሰልቲግ ባለቤት ኢ/ር ኪዳኔ መብራቱ እና በሳይበር ደኅንነት ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ […]

ሰበር_ዜና:- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ራሱን ችሎ በሊቀ ጳጳስእንዲመራ ከተደረገ በኀላ ለመጀመሪያ ጊዜ እጅግ በርካታ የሥራ ኃላፊዎች ማለትም የሠላሳ ዘጠኝ (39) ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን ዝውውር አደረገ(መጋቢት 17 ቀን /2013)

የዝውውር አሠራሩም ከኢፍትሐዊነት እና አድሎዊነት፡ ከዘርና ከመድሎ እንዲሁም ከግለሰባዊነት በጸዳ መልኩ በአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ የተፈጸመ መሆኑን ተገልጿል፡፡ከዚህም ጋር ተያይዞ የተወሰኑ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የጡረታ መብታቸው ተከብሮ ጡረታ ሲወጡ ጥቂት የሚባሉ የገዳማትና አድባራት ዋና ጸሐፊዎች ደግሞ ወደ አስተዳዳሪነት ማድጋቸውን ጽ/ቤቱ አሳውቋል፡፡የዝውውር ቦታውን እንደሚከተለው ቀርቧል1.ከአየር ጤና ረጲ ኪዳነ ምህረት ወደ ካራ ሥላሴ ቤ/ክ ከከራ ሥላሴ ወደ ረጲ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከትናንት እስከ ዛሬ ለሀገር ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽኦ የማይተካ ሚና እንዳለው የሚገልጽና መልካም አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚያትት ሥልጠና በልደታ፥ ቂርቆስና አዲስ ክፍለ ከተማ ተሰጠ!

በአራዳና በአቃቂ ክፍላተ ከተማ በተከታታይ ሲካሄድ የቆየው የ39ኛው የሰበካ ጉባኤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከትናንት እስከ ዛሬ ለሀገር ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽኦ የማይተካ ሚና እንዳለው የሚገልጽና መልካም አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚያትት ስልጠና ዛሬም በልደታ፥ ቂርቆስና አዲስ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አስተባባሪነት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ቀጥሎ ውሏል።በዛሬው ዕለት መጋቢት 15 […]

ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ በሚል መሪ ቃል በCMC ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ4 ቀናት የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በተገኙበት በዛሬው ተጠናቀቀ !!!

መጋቢት 14 ቀን /2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳሰ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ኃላፊ መ/ም በቃሉ ወርቅነህ፡ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽባሕ አባ ጥዑመልሳን አድነውና የደብሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዕዝራ ነዋይ እንዲሁም የደብሩ ካህናትና መምህራን የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት ወርኃዊውን የቅዱስ […]

የዛሬው የ39ኛው የሰበካ ጉባኤ ስልጠና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት አስተባባሪነት በሳሪስ ም/ቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተካሄደ

በዛሬው ዕለት መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም የመ/ፓ/ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ላዕከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ብርሃን ሳሙኤል ደምሴ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በአቃቂ […]

የሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበር ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የምስጋና ምስክር ወረቀት አበረከተ

የሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበር በአሁኑ ሰዓት 450 ሴቶችንና 650 ሕጻናትን የሚንከባከብና የሚያስተምር የበጎ አድራጎት ማኅበር ነው።የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ይህንን በእግዚአብሔርም ሆነ በሰው ፊት መልካም የሆነውን የማኅበሩን ሥራ ለማበረታታትና የድርሻውን ለመወጣት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተሰበሰቡ የትምህርት ቁሳቁሶችንና የተለያዩ አልባሳትን ከአንድም ሁለት ጊዜ ለማኅበሩ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።የሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበርም […]

ማስታወቂያ

በቅርብ የተለቀቁ

በፌስቡክ ያግኙን

ግጻዌ

©2019 Copyright - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት