• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ተፈጸመ !!!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዐሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና  ብፁዓን አበው  ክብርት ፕረዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ብዙ የአሃት አብያተክርስቲያናት ሊቃ ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መምህራን እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለቅዱስነታቸው የረጅም ጊዜ […]

“ምኩራብ”

“እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዓኒ፤ የቤትህ ቅንዓት በላኝ።” (መዝ. 68፥9፤ ዮሐ. 2፥17) የዐቢይ ፆም ሦስተኛው ሰንበት (እሑድ) ምኩራብ ይባላል፦ ስያሜውን ያገኘው ጌታችን በአይሁድ ቤተ-መቅደስ ተገኝቶ ቤተ-መቅደስ ንጹህ የእግዚአብሔር ቤት፣ የጸሎት ቤት፣ ሃይማኖትና ጽድቅ  የሚነገርበት የተቀደሰ/የተለየ ቦታ መሆኑን ያረጋገጠበት ስለሆነ ነው። ሊቁም “ቦአ ኢየሱስ ምኩራቦሙ ለአይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት” በማለት ጌታችን  ወደ ቤተመቅደሱ የገባ ክህደትና ዓለማዊነትን አስወግዶ […]

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።

የቅዱስነታቸው አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በክብር ታጅቦ መስቀል አደባባይ ከደረሰ በኋላ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መርሐ ግብሩን በጸሎት አስጀምረዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 9 ዓመት በጵጵስና፤ 34 ዓመት ደግሞ በፓትርያርክነት እንዳገለገሉ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመርሐ […]

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌልን በተመለከተ ሥልጠና  እየተሰጠ ይገኛል!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪዎች፣ ሰባክያነ ወንጌልና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ስብከተ ወንጌልን አስመልክቶ እየተሰጠ ያለውን ሥልጠና እየተከታተሉ ይገኛሉ። ሰልጣኞቹ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ክቡር ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት […]

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የደብረ እንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!!!

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን እየተሰራ ያለውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እና 64 ሜትር የሚረዝመውን የመስቀል ፕሮጀክት ግንባታን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ለብፁዕነታቸው ከሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ እና ከአካባቢው  ምዕመናን ስለገጠማቸው አጠቃላይ ተግዳሮት አስረድተዋል። ብፁዕነታቸው በበኩላቸው ወቅቱ ዓብይ ጾም በመሆኑ ምዕመናን ጾሙን በተረጋጋ መንፈስ መጾም እንዳለባቸው […]

ቅድስት ( የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት )

ትርጉም የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል፤ ትርጓሜውም የተቀደሰች የተለየች ማለት ነው። ስያሜውም የተገኘው ከቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቅድስና በሰፊው ትምህርት ይሰጣል፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴው በሚካሄድበት ጊዜም የሚሰበከው ምስባክ፣ የሚነበቡ መልዕክታት፣ የሐዋርያት ሥራና ወንጌል ስለ ቅድስና የሚያስተምሩና የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ በዚህ ሳምንት፦ ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና፣ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር […]

“ቤተክርስቲያናችን ከውስጥም ከውጭም እየተፈተነች ለመሆኗ ከሜዳው ተነሥቶ ፓትርያርክ ነኝ፣  ጳጳስ ነኝ  የሚለው መብዛቱ ትልቅ ማሳያ ነው”….ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  በዓለ ሢመታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትእና በርካታ የመንግሥት ባለ ስልጣናት: አምባሳደሮች  የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ተከብሯል። ለበዓለ ሢመቱ የተዘጋጁ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ  ካቴድራል መምህራን ወረብ እና ቅኔ አቅርበዋል። የካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተዋበ ክርሲቲያናዊ አለባበስ ደምቀው ዝማሬ አቅርበዋል። […]

“በሀገራችንም ሆነ በዓለም ላይ ሰላም እንዲሰፍን ሁላችንም በአንድ መንፈስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት ልንተጋ ይገባል” … ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የ2014 ዓ.ም የዐቢይ ጾም መግቢያን አስመልክተው ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና ከወሰነቻቸው አጽዋማት መካከል አንዱ የዐቢይ ጾም መሆኑን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል። ዐቢይ የሚለው ቃል ትርጉሙ ትልቅ ማለት ሲሆን የጾሙን ታላቅነት ይገልጻል ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት ጌታችን […]

በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምሁርና አክሊል ወረዳ ሥር የሚገኘው የሴባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በምሁርና አክሊል ወረዳ ሥር የሚገኘው የሴባ አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ እና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። የሴባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም መሠረተ ድንጋይ በወቅቱ የጉራጌና የሀድያ አህጉረ ስብከት ሊቀ […]

የቴክኖሎጂ ጥቅም በኦርቶዶክሳዊ ክርስትና እይታ

የሰው ልጆች በምድራውያኑ ፍጥረታት ውስጥ ካሉት ድርሻዎች ውስጥ መሪነት እና ገዢነት ይጠቀሳሉ፡፡ “ምድርን ሙሏት … ግዟትም” የሚለው ቃል ለሰው ልጅ የተሰጠውን ኃይል፣ ዕውቀትና ሥልጣን የሚገልጥ ነው፡፡ (ዘፍ. ፩፥፳፰)፡፡ ይህ ገዢነትና በእነዚህ ፍጥረታት ላይ የተሰጠው ሥልጣን በምን ይገለጣል? ሰው ይህን ለማድረግ የሚያበቃ ምን ነገር አለው? እንዲገዛቸውና እንዲጠቀምባቸው ከተፈጠሩት ፍጥረታት መካከል ከእርሱ የሚበረቱ፣ የሚፈጥኑ እና የሚገዝፉ ፍጥረታት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን